Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ጢሞቴዎስ 3:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የሚጠቅመውም የእግዚአብሔር ሰው ፍጹም እንዲሆንና ማንኛውንም መልካም ሥራ ለመሥራት ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ይኸውም የእግዚአብሔር ሰው ለመልካም ሥራ ሁሉ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በዚህም የእግዚአብሔር ሰው በችሎታው ፍጹም እንዲሆንና ለመልካም ሥራ ሁሉ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ይጠቅማል።

Ver Capítulo Copiar




2 ጢሞቴዎስ 3:17
12 Referencias Cruzadas  

ቀጠል አድርጌም እግዚአብሔር ከእኔ ጋር መሆኑንና እንዴትም እንደ ረዳኝ፥ ንጉሠ ነገሥቱም የነገረኝን ሁሉ ገለጥሁላቸው። እነርሱም “እንደገና መሥራቱን እንጀምር!” ካሉኝ በኋላ፥ ይህን በጎ ሥራ ለመጀመር ተዘጋጁ።


በኢዮጴም ጣቢታ የምትባል አንዲት አማኝ ነበረች፤ የስሟም ትርጒም በግሪክኛ ዶርቃ ትርጒሙም ሚዳቋ ማለት ነው፤ እርስዋ መልካም ነገር ማድረግና ለድኾች መለገሥ የምታዘወትር ሴት ነበረች፤


ሁልጊዜ በሁሉ ነገር ራሳችሁን ችላችሁ ለመልካም ሥራ ሁሉ ለማዋል እንዲበቃችሁ እግዚአብሔር በብዛት በረከቱን ሊሰጣችሁ ይችላል።


እኛ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጃቸውን መልካም ሥራዎች እንድንሠራ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እንደገና የተፈጠርን የእግዚአብሔር ፍጡሮች ነን።


የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! አንተ ግን ከዚህ ሁሉ ሽሽ፤ ጽድቅን፥ መንፈሳዊነትን፥ እምነትን፥ ፍቅርን፥ በትዕግሥት መጽናትን፥ ገርነትን ተከታተል።


ከእነዚህ ክብር ከሌላቸው ነገሮች ተለይቶ ንጹሕ ሆኖ የሚኖር ሰው ለተከበረ አገልግሎት እንደሚውል ዕቃ ይሆናል፤ ለማንኛውም መልካም አገልግሎት የተዘጋጀ ለጌታው የተቀደሰና ጠቃሚ መገልገያ ይሆናል።


“እግዚአብሔርን እናውቃለን” ይላሉ፤ በሥራቸው ግን ይክዱታል፤ እነርሱ አጸያፊዎች፥ የማይታዘዙና ምንም መልካም ሥራ ማድረግ የማይችሉ ናቸው።


ክርስቶስ ከዐመፃ ሁሉ ሊያድነንና መልካም ሥራ ለመሥራት ትጉሆችና ለእርሱ የተለየን ንጹሕ ሕዝብ እንድንሆን ያነጻን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።


ሰዎች ሁሉ ለገዢዎችና ለባለሥልጣኖች በትሕትና እንዲታዘዙ፥ መልካም ሥራን ሁሉ ለመሥራት ዝግጁዎች እንዲሆኑ፥


በፍቅርና በመልካም ሥራ ነቅተን እንድንኖር አንዱ ሌላውን ያሳስበው፤


ፈቃዱን ለመፈጸም እንድትበቁ በመልካም ነገር ሁሉ ያስታጥቃችሁ፤ ደስ የሚያሰኘውንም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእኛ ያድርግ፤ ለኢየሱስ ክርስቶስም ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos