Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ነህምያ 12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


የካህናትና የሌዋውያን ስም ዝርዝር

1 ከሰላትያል ልጅ ከዘሩባቤልና ከኢያሱ ጋር የወጡት ካህናትና ሌዋውያን እነዚህ ናቸው፤ ሥራያ፥ ኤርምያስ፥ ዕዝራ፥

2 አማርያ፥ ማሉክ፥ ሐጡሽ፥

3 ሽካንያ፥ ርሁም፥ ምሬሞት፥

4 ዒዶ፥ ጊንቶይ፥ አቢያ፥

5 ሚያሚን፥ ማዓድያ፥ ቢልጋ፥

6 ሽማዕያ፥ ዮያሪብ፥ ይዳዕያ፥

7 ሳሉ፥ ዓሞቅ፥ ሒልቂያ፥ ይዳዕያ፤ እነዚህ በኢያሱ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቻቸው መሪዎች ነበሩ።

8 ሌዋውያኑም፦ ኢያሱ፥ ቢኒዊ፥ ቃድሚኤል፥ ሼሬብያ፥ ይሁዳና ከወንድሞቹ ጋር በመሆን የምስጋና መዝሙር ኃላፊ የነበረው ማታንያ።

9 ወንድሞቻቸው ባቅቡቅያና ዑኖ በአገልግሎቱ ጊዜ በፊት ለፊታቸው ይቆሙ ነበር።

10 ኢያሱም ዮያቂምን ወለደ፥ ዮያቂም ኤልያሺብን ወለደ፥ ኤልያሺብ ዮያዳዕን ወለደ፥

11 ዮያዳዕ ዮናታንን ወለደ፥ ዮናታን ያዱዓን ወለደ።

12 በዮያቂም ዘመን የአባቶች መሪዎች ካህናቱ እነዚህ ነበሩ፦ ከሥራያ ቤተሰብ ምራያ፥ ከኤርምያስ ሐናንያ፥

13 ከዕዝራ ምሹላም፥ ከአማርያ ይሆሐናን፥

14 ከምሉኪ ዮናታን፥ ከሽባንያ ዮሴፍ፥

15 ከሐሪም ዓድና፥ ከምራዮት ሔልቃይ፥

16 ከዒዶ ዘካርያስ፥ ከጊንቶን ምሹላም፥

17 ከአቢያ ዚክሪ፥ ከሚንያሚን፥ ከሞዓድያ፥ ፒልጣይ፥

18 ከቢልጋ ሻሙዓ፥ ከሽማዕያ ይሆናታን፥

19 ከዮያሪብ ማትናይ፥ ከይዳዕያ ዑዚ፥

20 ከሳላይ ቃላይ፥ ከዓሞቅ ዔቤር፥

21 ከሒልቂያ ሐሻብያ፥ ከይዳዕያ ናትናኤል።

22 ከሌዋውያኑም በኤልያሺብ፥ ዮያዳዕ፥ ዮሐናን፥ ያዱዓ ዘመን የአባቶች መሪዎችና ካህናቱ በፋርሳዊው በዳርዮስ ዘመነ መንግሥት ተመዝግበው ነበር።

23 የሌዊ ልጆች የአባቶች መሪዎች እስከ ኤልያሺብ ልጅ እስከ ዮሐናን ዘመን ድረስ በታሪክ መጽሐፍ ተመዝግበው ነበር።

24 የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሻብያ፥ ሼሬብያ፥ የቃድሚኤል ልጅ ኢያሱና ወንድሞቻቸው ደግሞ ከፊት ለፊታቸው ሆነው የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ክፍል በክፍል ትይዩ ሆነው ያወድሱና ያመሰግኑ ነበር።

25 ማታንያ፥ ባቅቡቅያ፥ አብድዩ፥ ምሹላም፥ ጣልሞን፥ ዓቁብ በበሮቹ አጠገብ የሚገኙትን ዕቃ ቤቶች የሚጠብቁ በር ጠባቂዎች ነበሩ።

26 እነዚህ በዮፃዳቅ ልጅ በኢያሱ ልጅ በዮያቂም ዘመንና በገዢው በነህምያና በጸሐፊው በካህኑ በዕዝራ ዘመን ነበሩ።


የከተማው ቅጥር የምረቃ በዓል መደረጉ

27 የኢየሩሳሌም ቅጥር ሲመረቅ ምረቃውን በደስታ፥ በምስጋና፥ በመዝሙር፥ በጸናጽል፥ በበገናና በክራር ለማክበር ሌዋውያኑን ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት በየሚኖሩበት ስፍራ ሁሉ ፈለጉ።

28 የመዘምራኑ ልጆች ከኢየሩሳሌም ዙሪያና ከነጦፋውያን መንደሮች፥ ተሰበሰቡ፤

29 መዘምራኑም በኢየሩሳሌም ዙሪያ መንደሮች ሠርተው ነበርና ከቤትጌልገላም፥ ከጌባና ከዓዝሞት እርሻዎች ተሰበሰቡ።

30 ካህናቱና ሌዋውያኑም ራሳቸውን አነጹ፤ ሕዝቡን፥ በሮቹንና ቅጥሩንም አነጹ።

31 የይሁዳንም አለቆች ወደ ቅጥሩ ላይ አወጣኋቸው፥ አመስጋኞቹንም በሁለት ታላላቅ ተርታ አቆምኋቸው፥ አንዱም ወደ ቀኝ በቅጥሩ ላይ ወደ ጉድፍ መጣያው በር ሄደ።

32 ከእነርሱም በኋላ ሆሻዕያና የይሁዳ መሪዎች እኩሌታ ሄዱ፥

33 አዛርያ፥ ዕዝራ፥ ምሹላም፥

34 ይሁዳ፥ ብንያም፥ ሸማዕያና ኤርምያስ፥

35 መለከት የያዙ ጥቂት የካህናቱ ልጆች፥ የአሳፍ ልጅ፥ የዛኩር ልጅ፥ የሚካያ ልጅ፥ የማታንያ ልጅ፥ የሸማዕያ ልጅ፥ የዮናታን ልጅ ዘካርያስ፥

36 ወንድሞቹም ሸማዕያ፥ ዓዛርኤል፥ ሚላላይ፥ ጊላላይ፥ መዓይ፥ ናትናኤል፥ ይሁዳና ሐናኒ የእግዚአብሔር ሰው የዳዊትን የዜማ መሣሪያ ይዘው ሄዱ፤ ጸሐፊው ዕዝራም በፊታቸው ነበረ።

37 “በምንጭ በር” አቅንተው ሄዱ፤ በዳዊትም ከተማ ደረጃ፥ በቅጥሩም መውጫ፥ ከዳዊትም ቤት በላይ እስከ ውኃው በር ድረስ በምሥራቅ በኩል ሄዱ።

38 ከፊት ይሄድ የነበረው ሁለተኛው የምስጋና መዘምራን ክፍል ነበር፤ እኔና የሕዝቡ እኩሌታ በስተ ኋላቸው ነበርን፤ በቅጥሩም ላይ፥ ከ “የእቶኑ ግንብ” በላይ እስከ “ሰፊው ቅጥር” ድረስ፥

39 ከ “ኤፍሬም በር” በላይ፥ ከ “አሮጌው በር” በላይ፥ በ “ዓሣ በር” በ “ሐናንኤል ግንብ”፥ በሃሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፥ በዘበኞችም በር አጠገብ ቆሙ።

40 ሁለቱ የምስጋና መዘምራን ክፍሎች በእግዚአብሔር ቤት ቆሙ፥ እኔና ከመሪዎቹ እኩሌታ በተጨማሪ፥

41 ካህናቱ ኤልያቂም፥ መዕሤያ፥ ሚንያሚን፥ ሚካያ፥ ኤልዮዕናዪ፥ ዘካርያስ፥ ሐናንያ መለከት ይዘው፥

42 መዕሤያ፥ ሽማዕያ፥ አልዓዛር፥ ኡዚ፥ ይሆሐናን፥ ማልኪያ፥ ዔላም፥ ዓዜር ቆምን። መዘምራኑም በዪዝራሕያ መሪነት በታላቅ ድምፅ ዘመሩ።

43 እግዚአብሔር በታላቅ ደስታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥዋዕት አቀረቡ፥ ደስም አላቸው፤ ሴቶቹና ልጆቹም ደግሞ ደስ አላቸው፤ የኢየሩሳሌምም ደስታ ከሩቅ ተሰማ።


የቤተ መቅደስ ኃላፊነቶች

44 በዚያን ቀን በይሁዳም በአገልጋዮቹ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ስላላቸው፥ የካህናቱንና የሌዋውያኑን እድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከተሞች እርሻዎች ያከማቹ ዘንድ ለእጅ ማንሣት ቁርባንና ለበኵራት ለአሥራትም በየዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎች ተሾሙ።

45 እነርሱም መዘምራኑና በረኞቹም የአምላካቸውን ሥርዓት የመንጻታቸውንም ሥርዓት እንደ ዳዊትና እንደ ልጁ እንደ ሰሎሞን ትእዛዝ ጠበቁ።

46 አስቀድሞም በዳዊትና በአሳፍ ዘመን እግዚአብሔርን በዜማ ለማመስገንና ለማክበር የመዘምራን አለቆች ነበሩ።

47 እስራኤልም ሁሉ በዘሩባቤልና በነህምያ ዘመን ለመዘምራኑና ለበረኞቹ እድል ፈንታቸውን በየዕለቱ ይሰጡ ነበር፥ የተቀደሰውንም ነገር ለሌዋውያን ሰጡ፥ ሌዋውያኑም ከተቀደሰው ነገር ለአሮን ልጆች ሰጡ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos