ለእርሱ ለራሱ እንዲሆን ሕዝብን ያድን ዘንድ፥ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ፥ ተአምራትንና ድንቅ ነገሮችን ያደርግ ዘንድ፥ ሕዝቦችንና አማልክቶቻቸውን በፊታቸው ያስወግድ ዘንድ እግዚአብሔር ከግብጽ ባርነት እንዳዳነው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ምን ሕዝብ አለ?
ሚክያስ 6:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከግብጽ አወጣሁህ፤ ከባርነት ምድርም ታደግኹህ፤ ሙሴን፥ አሮንንና ማርያምን በፊትህ መሪዎች አድርጌ ሰጠሁህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከግብጽ አወጣሁህ፤ ከባርነት ምድርም ተቤዠሁህ፤ እንዲመሩህ ሙሴን፣ አሮንንና ማርያምን ላክሁልህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከግብጽ ምድር አውጥቼሃለሁ፥ ከባርነት ቤትም ተቤዥቼሃለሁና፤ በፊትህም ሙሴን፥ አሮንንና ማርያምን ላክሁልህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከግብጽ ምድር አውጥቼሃለሁ፥ ከባርነት ቤትም ተቤዥቼሃለሁ፥ በፊትህም ሙሴንና አሮንን ማርያምንም ልኬልህ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከግብጽ ምድር አውጥቼሃለሁ፥ ከባርነት ቤትም ተቤዥቼሃለሁ፥ በፊትህም ሙሴንና አሮንን ማርያምንም ልኬልህ ነበር። |
ለእርሱ ለራሱ እንዲሆን ሕዝብን ያድን ዘንድ፥ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ፥ ተአምራትንና ድንቅ ነገሮችን ያደርግ ዘንድ፥ ሕዝቦችንና አማልክቶቻቸውን በፊታቸው ያስወግድ ዘንድ እግዚአብሔር ከግብጽ ባርነት እንዳዳነው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ምን ሕዝብ አለ?
ሙሴ ግን እንዲህ አለ፤ “እባክህ ጌታ ሆይ፥ ወደዚያ አትላከኝ፤ ቀድሞም ሆነ ወይም አሁን አንተ ከእኔ ጋር መነጋገር ከጀመርክበት ጊዜ አንሥቶ የመናገር ችሎታ የለኝም፤ እኔ አንደበቴ የሚኮላተፍና አጥርቼ ለመናገር የማልችል ነኝ።”
እስራኤላውያን በየነገዳቸው ተከፋፍለው በሙሴና በአሮን መሪነት ከግብጽ ከወጡ በኋላ በየጊዜው የሰፈሩባቸውን ቦታዎች የሚያስረዳው ታሪክ ይህ ነው፦
አንተም በግብጽ ምድር ባሪያ እንደ ነበርክና እግዚአብሔር አምላክህ ነጻ ያወጣህ መሆኑን አስታውስ፤ እኔም ዛሬ ይህን ትእዛዝ የማዝህ በዚህ ምክንያት ነው።
እናንተም በግብጽ ባርያዎች እንደ ነበራችሁና አምላካችሁ እግዚአብሔር ነጻ እንዳወጣችሁ አስታውሱ፤ እኔም ይህን ትእዛዝ የምሰጣችሁ በዚህ ምክንያት ነው።
እናንተ ግን እሳት እንደሚነድበት የብረት ምድጃ ከሆነችው ከግብጽ መንጥቆ እግዚአብሔር ያወጣችሁ ዛሬ እንደ ሆናችሁት ሁሉ ለራሱ የተለያችሁ ወገኖቹ እንድትሆኑ ነው።
ወይስ በፈተና፥ በተአምራትና በድንቅ ነገሮች፥ በጦርነት፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በሚያስፈራ ኀይል፥ በዐይናችሁ እያያችሁት እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተን ከግብጽ ምድር እንዳወጣችሁ ያለ አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ መካከል ወስዶ የራሱ ሕዝብ ለማድረግ የሞከረ ሌላ አምላክ አለን?
ነገር ግን እግዚአብሔር እናንተን ስለ ወደደ ለቀድሞ አባቶቻችሁ የሰጠውን የተስፋ ቃል መጠበቅ ፈለገ፤ በታላቅ ኀይሉ ያዳናችሁና የግብጽ ንጉሥ ባርያዎች ከመሆን ነጻ ያወጣችሁም በዚህ ምክንያት ነበር።
ሳሙኤልም የሚናገረውን ቃል በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “ሙሴንና አሮንን የመረጠ፥ የቀድሞ አባቶቻችሁንም ከግብጽ ምድር ያወጣ እግዚአብሔር ነው፤