Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሚክያስ 6:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ሕዝቤ ሆይ! የሞአብ ንጉሥ ባላቅ ምን እንደ ዐቀደብህና የቢዖር ልጅ በለዓም ምን እንደ መለሰለት አስታውስ፤ ከሺጢም ተነሥተህ ወደ ጌልጌላ በምትሄድበት ጊዜ በመንገድ ላይ የሆነውን ሁሉ አስታውስ፤ ይህን ሁሉ ብታስታውስ አንተን ለማዳን ያደረግኹትን ሁሉ ታውቃለህ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ሕዝቤ ሆይ፤ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፣ የቢዖር ልጅ በለዓም የመለሰለትንም እስኪ አስቡ፤ የእግዚአብሔርን የጽድቅ ሥራ ታውቁ ዘንድ፣ ከሰጢም እስከ ጌልገላ የተጓዛችሁትን ዐስቡ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ያቀደውን፥ የቤዖር ልጅ በለዓም የመለሰለትን፥ የጌታን ጽድቅ እንድታውቅ ከሺጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ የሆነውን እባክህን አስታውስ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፥ የቢዖርም ልጅ በለዓም የመለሰለትን አሁን አስብ፥ የእግዚአብሔርንም የጽድቅ ሥራ ታውቅ ዘንድ ከሰጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ አስብ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፥ የቢዖርም ልጅ በለዓም የመለሰለትን አሁን አስብ፥ የእግዚአብሔርንም የጽድቅ ሥራ ታውቅ ዘንድ ከሰጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ አስብ።

Ver Capítulo Copiar




ሚክያስ 6:5
37 Referencias Cruzadas  

የእስራኤል ሕዝብ በሺጢም ሸለቆ ሰፍሮ በነበረበት ጊዜ ወንዶቹ እዚያ ከነበሩበት ሞአባውያን ሴቶች ጋር አመነዘሩ፤


እነሆ አድምጡ! ውሃ በሚቀዳባቸው ጒድጓዶች ዙሪያ የሚሰማው የብዙ ሰዎች ድምፅ፥ የእግዚአብሔርን ድል ያበሥራል፤ የእስራኤልንም ሕዝብ ድል አድራጊነት ይናገራል። ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ሕዝብ፥ ከከተሞቻቸው ተሰልፈው ወረዱ።


ሕዝቡ የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን፥ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረው ከኢያሪኮ በስተምሥራቅ በኩል በሚገኘው በጌልገላ ሰፈሩ።


ነገር ግን የምነቅፍብህ አንዳንድ ነገሮች አሉኝ፤ ይኸውም የበለዓምን ትምህርት የያዙ አንዳንድ ሰዎች በመካከላችሁ አሉ፤ ይህ በለዓም የእስራኤል ሕዝብ ለጣዖት የተሠዋውን ምግብ በመብላትና ዝሙት በማድረግ እንዲሰናከሉ ባላቅን የመከረ ነው።


በቃየል መንገድ ስለ ሄዱ፥ ለገንዘብ ብለው በበለዓም ስሕተት ስለ ወደቁ፥ ቆሬም እንደ ተቃወመ በመቃወማቸው ስለ ጠፉ ወዮላቸው!


ኃጢአታችንን ለእግዚአብሔር ብንናዘዝ እርሱ ታማኝና ጻድቅ ስለ ሆነ ኃጢአታችንን ሁሉ ይቅር ይልልናል፤ ከበደላችንም ሁሉ ያነጻናል።


እነርሱ የቀናውን መንገድ ትተው ጠፍተዋል፤ ክፉ በመሥራት የሚገኘውን ገንዘብ የወደደውን የቢዖርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከትለው ተሳስተዋል።


እግዚአብሔር ሆይ! ስለ ክብርህ ሕይወቴን ጠብቅ፤ በእውነተኛነትህም ከችግሬ ሁሉ ነጻ አውጣኝ።


ያንንም ራት በምትመገብበት ጊዜ እርሾ የነካው እንጀራ አትብላ፤ በዚያ ዐይነት አስቸኳይ ሁኔታ ግብጽን ለቀህ በወጣህበት ጊዜ እንዳደረግኸው ሰባት ቀን ሙሉ እርሾ ያልነካው ቂጣ ትበላለህ፤ ይህን ቂጣ ብላ፤ እርሱም የሥቃይ እንጀራ ተብሎ ይጠራል፤ ይኸውም በምትኖርበት ዘመን ሁሉ ብዙ ሥቃይ ከተቀበልክበት ከግብጽ ምድር የወጣህበትን ቀን ታስታውሳለህ።


“እግዚአብሔር አምላክህን በበረሓ እንዴት እንዳስቈጣኸው ከቶ አትርሳ፤ የግብጽን ምድር ለቀህ ከወጣህበት ቀን ጀምሮ እዚህ እስከ መጣህበት እስከ አሁን ድረስ በእርሱ ላይ ዐምፀሃል።


ባለጸጋ እንድትሆን ኀይልና ብርታት የሰጠህ እግዚአብሔር አምላክህ መሆኑን አስታውስ፤ እርሱ ይህን የሚያደርግበት ምክንያት ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ነው።


ስለዚህ እናንተ ቀድሞ በትውልዳችሁ አሕዛብ የነበራችሁ፥ አይሁድ በሰው እጅ በመገረዛቸው እየተመኩ እናንተን ያልተገረዙ እያሉ ይሰድቡአችሁ እንደ ነበር አስታውሱ።


አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህን ትእዛዞች ስለ መጠበቅህ በልብህ ያለውን ሐሳብ ያውቅ ዘንድ አንተን ለመፈተን በዚህ በረሓ አርባ ዓመት ሙሉ በመከራ ውስጥ በማሳለፍ እንዴት እንደ መራህ አስታውስ።


በፔዖር ሳለን የበለዓምን ምክር ተቀብለው ሕዝቡ በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነት እንዲተዉ ያደረጉ ሴቶች መሆናቸውን ዘነጋችሁን? በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ የአባር ቸነፈር መቅሠፍት ያመጣም ያ ስሕተት ነበር።


አምስቱንም የምድያም ነገሥታት ኤዊን፥ ሬቄምን፥ ጹርን፥ ሑርንና ሬባዕን ገደሉ፤ የቢዖርን ልጅ በለዓምንም ገደሉት።


ባላቅም “ና ወደ ሌላ ቦታ እንሂድ፤ ምናልባት ከዚያ ሆነህ ይህን ሕዝብ እንድትረግምልኝ እግዚአብሔር ይፈቅድልህ ይሆናል” አለው።


በማግስቱ ጠዋት ባላቅ በለዓምን የእስራኤልን ሕዝብ በከፊል ለማየት ወደሚቻልበት ወደ ባሞትበዓል አወጣው።


እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ ነው፤ በአስደናቂ ሥራውም የገነነ ነው።


አምላክ ሆይ! ጽድቅህ እስከ ሰማይ ይደርሳል፤ ታላላቅ ነገሮችን አድርገሃል፤ አምላክ ሆይ! አንተን የሚመስል ማን ነው?


ለሚያውቁህ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ አይቋረጥባቸው፤ አዳኝነትህም ለልበ ቅኖች ይቀጥል።


እንግዲህ ተነሥታችሁ ባላችሁበት ቁሙ፤ የቀድሞ አባቶቻችሁንና እናንተን ለማዳን እግዚአብሔር ያደረገላችሁን ድንቅ ሥራዎች ሁሉ በማስታወስ እነሆ እኔ በእግዚአብሔር ፊት እፋረዳችኋለሁ፤


በዮርዳኖስም አጠገብ በሞአብ ሜዳ ላይ ከቤትየሺሞት እስከ አቤል ሹቲም ድረስ ሰፈሩ።


ከዚህ በኋላ የነዌ ልጅ ኢያሱ ከሺጢም ሰፈር ሁለት ሰላዮችን ላከ፤ እነርሱም የከነዓንን ምድር በተለይም የኢያሪኮን ከተማ በምሥጢር ሰልለው እንዲመለሱ አዘዛቸው፤ ወደ ከተማይቱ በመጡ ጊዜ “ረዓብ” ተብላ ወደምትጠራ ወደ አንዲት ሴትኛ ዐዳሪ ቤት ገብተው ዐደሩ።


በማግስቱ ኢያሱና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ማልደው ተነሡ፤ የሺጢምን ሰፈር ለቀው ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሄዱ፤ ከመሻገራቸውም በፊት በዚያ ሰፈሩ፤


ለመሆኑ አንተ የሞአብ ንጉሥ ከነበረው ከጺጶር ልጅ ከባላቅ ትበልጣለህን? እርሱ እንኳ እስራኤልን ከቶ አልተቋቋመም፤ እኛንም ይወጋ ዘንድ ወደ ጦርነት ለመውጣት አልደፈረም።


እግዚአብሔር እውነተኛ ስለ ሆነ ጽዮንን በፍርድ ያድናታል፤ በውስጥዋ ከሚኖሩት መካከል ንስሓ የሚገቡትን ይታደጋል።


እነዚያም ሴቶች ለሞአብ ጣዖት የተሠዋውን መሥዋዕት እንዲመገቡ ጋበዙአቸው፤ እስራኤላውያንም የመሥዋዕቱን ምግብ በልተው ፔዖር በሚባለው ተራራ ላይ ለሚገኘው በዓል ለተባለውም ጣዖት ሰገዱ፤


በምትኖርበት ዘመን ሁሉ እነዚህ ሕዝቦች ባለጸጎች ሆነው በሰላም እንዲኖሩ አትርዳቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios