Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ዘኍል 33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም


ከግብጽ እስከ ሞአብ የነበረው ጒዞ

1 እስራኤላውያን በየነገዳቸው ተከፋፍለው በሙሴና በአሮን መሪነት ከግብጽ ከወጡ በኋላ በየጊዜው የሰፈሩባቸውን ቦታዎች የሚያስረዳው ታሪክ ይህ ነው፦

2 በየጊዜው የሰፈሩባቸውን ቦታዎች ስሞች ሙሴ በእግዚአብሔር ትእዛዝ መሠረት ጻፈ።

3 የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር የወጡት የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን ማለትም በመጀመሪያው የፋሲካ በዓል ማግስት ነበር። ግብጻውያን ሁሉ ፊት ለፊት እያዩአቸው በእግዚአብሔር ጠባቂነት የራምሴን ከተማ ለቀው ወጡ፤

4 ግብጻውያን በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር መቅሠፍት የሞቱትን የበኲር ልጆቻቸውን ይቀብሩ ነበር፤ እግዚአብሔርም በአማልክታቸው ላይ እንኳ ፈርዶአል።

5 እስራኤላውያን ከራምሴ ተነሥተው በመጓዝ በሱኮት ሰፈሩ፤

6 ከዚያም ተነሥተው በበረሓው ጫፍ በምትገኘው በኤታም ሰፈሩ፤

7 ከኤታም ተነሥተው በባዓልጸፎን በስተምሥራቅ ወደ ፒሃሒሮት በመመለስ በሚግዶል ፊት ለፊት ሰፈሩ፤

8 ከፒሃሒሮት ተነሥተው ቀይ ባሕርን በመሻገር ወደ ሱር በረሓ መጡ፤ ከሦስት ቀን ጒዞ በኋላ በማራ ሰፈሩ፤

9 ከዚያም ተነሥተው ዐሥራ ሁለት የውሃ ምንጮችና ሰባ የተምር ዛፎች ወደሚገኙባት ወደ ኤሊም ሄደው በዚያ ሰፈሩ።

10 ከኤሊም ተነሥተው በቀይ ባሕር አጠገብ ሰፈሩ፤

11 ከቀይ ባሕር ተነሥተው በሲን ምድረ በዳ ሰፈሩ፤

12 ከሲን ምድረ በዳ ተነሥተው በዱፍቃ ሰፈሩ፤

13 ከዱፍቃም ተነሥተው በአሉሽ ሰፈሩ፤

14 ከአሉሽ ተነሥተው የመጠጥ ውሃ በሌለበት በረፊዲም ሰፈሩ።

15 ከሬፊዲም ተነሥተው በመጓዝ በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ።

16 ከሲና ምድረ በዳ ተነሥተው በመጓዝ በኪብሮት ሃትአዋ ሰፈሩ።

17 ከኪብሮት ሃትአዋ ተነሥተው በመጓዝ በሐጼሮት ሰፈሩ።

18 ከሐጼሮት ተነሥተው በመጓዝ በሪትማ ሰፈሩ።

19 ከሪትማ ተነሥተው በመጓዝ በሪሞንፔሬዝ ሰፈሩ።

20 ከሪሞንፔሬዝ ተነሥተው በመጓዝ በሊብና ሰፈሩ

21 ከሊብና ተነሥተው በመጓዝ በሪሳ ሰፈሩ።

22 ከሪሳ ተነሥተው በመጓዝ በቀሄላታ ሰፈሩ።

23 ከቀሄላታ ተነሥተው በመጓዝ በሼፈር ተራራ ሰፈሩ።

24 ከሼፌር ተራራ ተነሥተው በመጓዝ በሐራዳ ሰፈሩ።

25 ከሐራዳ ተነሥተው በመጓዝ በማቅሔሎት ሰፈሩ።

26 ከማቅሔሎት ተነሥተው በመጓዝ በታሐት ሰፈሩ፤

27 ከታሐት ተነሥተው በመጓዝ በታራ ሰፈሩ።

28 ከታራ ተነሥተው በመጓዝ በሚትቃ ሰፈሩ።

29 ከሚትቃ ተነሥተው በመጓዝ በሐሽሞና ሰፈሩ።

30 ከሐሽሞና ተነሥተው በመጓዝ በሞሴሮት ሰፈሩ።

31 ከሞሴሮት ተነሥተው በመጓዝ በቤኔያዕቃን ሰፈሩ።

32 ከቤኔያዕቃን ተነሥተው በመጓዝ በሖርሃጊድጋድ ሰፈሩ።

33 ከሖርሃጊድጋድ ተነሥተው በመጓዝ በዮጥባታ ሰፈሩ።

34 ከዮጥባታ ተነሥተው በመጓዝ በዓብሮና ሰፈሩ።

35 ከዓብሮና ተነሥተው በመጓዝ በዔጽዮንጋብር ሰፈሩ።

36 ከዔጽዮንጋብር ተነሥተው በመጓዝ በጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ፤ ይህችም ቃዴስ ነች።

37 ከቃዴስ ተነሥተው በመጓዝ በኤዶም ምድር ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ ሰፈሩ።

38 ካህኑ አሮን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፤ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ።

39 አሮንም በሖር ተራራ በሞተ ጊዜ ዕድሜው 123 ዓመት ነበር።

40 በደቡብ ከነዓን በምትገኘው በዐራድ አገር የሚኖረው ከነዓናዊው የዐራድ ንጉሥ እስራኤላውያን መምጣታቸውን ሰማ።

41 ከሖር ተራራ ተነሥተው በመጓዝ በጸልሞና ሰፈሩ።

42 ከጸልሞና ተነሥተው በመጓዝ በፉኖን ሰፈሩ።

43 ከፉኖን ተነሥተው በመጓዝ በኦቦት ሰፈሩ።

44 ከኦቦት ተነሥተው በመጓዝ፥ በሞአብ ዳርቻ ባለው በዓባሪም ሰፈሩ።

45 ከዓባሪም ተነሥተው በመጓዝ በዲቦንጋድ ሰፈሩ፤

46 ከዲቦን ጋድ ተነሥተው በመጓዝ በዓልሞንዲብላታይም ሰፈሩ።

47 ከዓልሞንዲ ብላታይም ተነሥተው በመጓዝ በናባው ፊት ባሉት በዓብሪም ተራራዎች ላይ ሰፈሩ።

48 ከዓብሪም ተራራዎች ተነሥተው በመጓዝ በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት ባለው በሞአብ ሜዳ ሰፈሩ።

49 በዮርዳኖስም አጠገብ በሞአብ ሜዳ ላይ ከቤትየሺሞት እስከ አቤል ሹቲም ድረስ ሰፈሩ።


እስራኤላውያን ዮርዳኖስን ከመሻገራቸው በፊት የተሰጣቸው መመሪያ

50 በኢያሪኮ ትይዩ ከዮርዳኖስ ማዶ በሞአብ ሜዳ ላይ ሳሉ ለእስራኤል ሕዝብ ይነግራቸው ዘንድ እግዚአብሔር ለሙሴ የሚከተለውን መመሪያ ሰጠው፤

51 ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ “ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ወደ ከነዓን ምድር ስትገቡ፥

52 በምድሪቱ ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ አስወጡአቸው፤ ከድንጋይና ከብረት የተሠሩትን ጣዖቶቻቸውንም ሰባበሩ፤ በኮረብታ ላይ ያሉ መስገጃዎቻቸውንም አፈራርሱ።

53 ለእናንተ የሰጠኋት ስለ ሆነ፥ ምድሪቱን ወርሳችሁ በእርስዋ ኑሩ።

54 ምድሪቱንም በተለያዩት ነገዶችና ጐሣዎች መካከል በዕጣ ተከፋፈሉ፤ የጐሣው ቊጥር ከፍ ላለው ሰፊ መሬት ይሰጠው፤ የጐሣው ቊጥር አነስተኛ ለሆነው ደግሞ ጠበብ ያለ መሬት ይሰጠው። እያንዳንዱ ሁሉ ዕጣው እንደ ወጣለት በዚያ ርስቱ ይሆናል፤ በየአባቶቻችሁ ነገዶች ምድሪቱን በርስትነት ትረከባላችሁ።

55 በምድሪቱ ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ አሳዳችሁ ካላጠፋችሁ ግን ያስቀራችኋቸው ለዐይናችሁ እንደ ስንጥር ለጐናችሁም እንደ እሾኽ በመሆን ያስቸግሩአችኋል፤ በምትቀመጡባትም ምድር ዘወትር ጦርነት በማስነሣት ያስጨንቁአችኋል።

56 ያለበለዚያ እነርሱን ለማጥፋት እንዳቀድኩት ሁሉ እናንተን አጠፋለሁ።”

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos