ሉቃስ 24:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ከሙሴና ከነቢያት መጻሕፍት ጀምሮ በቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ ስለ እርሱ የተነገረውን እየጠቀሰ አስረዳቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ በቅዱሳት መጻሕፍት ስለ እርሱ የተጻፈውን አስረዳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን አብራራላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ከሙሴና ከነቢያት፥ ከመጻሕፍትም ሁሉ ስለ እርሱ የተነገረውን ይተረጕምላቸው ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው። |
በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በአንተ ዘርና በእርስዋ ዘር መካከል ጠላትነት እንዲኖር አደርጋለሁ። የእርስዋ ዘር የአንተን ራስ ይቀጠቅጣል፤ አንተም የእርስዋን ዘር ተረከዝ ትነክሳለህ።”
‘ሴሎ’ ተብሎ የሚጠራው፥ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለትና ለዘለዓለም የሚነግሠው እስኪመጣ ድረስ፥ በትረ መንግሥት (የገዢነት ሥልጣን) ከይሁዳ እጅ አይወጣም።
መሪዎችሽ ዐመፀኞችና የሌቦች ግብረ አበሮች ሆኑ፤ እያንዳንዱ ሁልጊዜ ገጸ በረከትና ጉቦ ይቀበላል፤ አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች መብት አይጠብቁም፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውንም ሴቶች አቤቱታ አይሰሙም።
እነዚያ የተሠቃዩት ግን ዳግመኛ ችግር አይደርስባቸውም። በቀድሞ ዘመን የዛብሎንና የንፍታሌም ምድር ተዋርዳ ትኖር ነበር፤ በኋለኛው ዘመን ግን ከሜዲቴራኒያን ባሕር ምሥራቅ ጀምሮ እስከ ዮርዳኖስ ማዶ ያለው በተለይም አሕዛብ ሰፍረውበት የነበረው የገሊላ ምድር ክብርን ይጐናጸፋል።
ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠሁትና የቀድሞ አባቶቻቸውም በኖሩባት ምድር ይኖራሉ፤ በዚያችም ምድር እነርሱና ልጆቻቸው ዘሮቻቸውም ሳይቀሩ ለዘለዓለም ይኖራሉ፤ እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት ያለ ንጉሥ በእነርሱ ላይ ለዘለዓለም ይነግሣል።
የናምሩድ ግዛት የነበረችውንም በሠራዊታቸው ኀይል አሦርን ድል ነሥተው ይይዛሉ፤ አሦራውያን አገራችንን ቢወሩና ድንበራችንን ቢረግጡ እርሱ ከእጃቸው ያድነናል።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ሰይፍ ሆይ! ተባባሪዬ በሆነው በእረኛዬ ላይ ንቃ! በጎቹ ይበተኑ ዘንድ እረኛውን ምታ! እኔም በታናናሾቹ ላይ እጄን አነሣለሁ።
ጽዮን ሆይ! ደስ ይበልሽ! ኢየሩሳሌም ሆይ! በደስታ እልል በይ! እነሆ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ፥ በአህያይቱ ማለትም በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ፥ በድል አድራጊነት ወደ አንቺ ይመጣል።
ከዚህም የተነሣ በእግዚአብሔር መሪነት ስለ ተደረገው ጦርነት በሚናገር የታሪክ መጽሐፍ እንዲህ ተብሎአል፦ “በሱፋ ክልልና በሸለቆዎች ውስጥ የሚገኘው ዋሄብ፥ የአርኖን ወንዝ፥
ኢየሱስም፥ “ከእናንተ ጋር በነበርኩ ጊዜ ለሙሴ በተሰጠው ሕግ፥ በነቢያትና በመዝሙር መጻሕፍት ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ መፈጸም አለበት ብዬ የነገርኳችሁ ቃል ይህ ነው” አላቸው።
ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ፥ “ሙሴ በሕግ መጽሐፍ፥ ነቢያትም በትንቢት መጻሕፍት ስለ እርሱ የጻፉለትን አገኘነው፤ እርሱም የዮሴፍ ልጅ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነው” አለው።
ሙሴም እንዲህ ብሎአል፦ ‘ጌታ አምላክህ እኔን እንዳስነሣኝ እንዲሁ ከወንድሞቻችሁ መካከል ነቢይ ያስነሣላችኋል፤ እርሱ የሚነግራችሁን ሁሉ ስሙ፤
‘ጌታ አምላካችሁ እኔን እንዳስነሣኝ እንዲሁ ከወንድሞቻችሁ መካከል ነቢይ ያስነሣላችኋል’ ብሎ ለእስራኤላውያን የተናገረው ይኸው ሙሴ ነበር።
እኔም ለመልአኩ ልሰግድለት በእግሩ ሥር በግንባሬ ተደፋሁ፤ እርሱ ግን “ተው! ይህን አታድርግ! እኔም ከአንተና የኢየሱስን ምስክርነት ከያዙት ወንድሞችህ ጋር አገልጋይ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ! የኢየሱስ ምስክርነት የትንቢት መንፈስ ነው” አለኝ።