ሉቃስ 21:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በመብልና በመጠጥ ብዛት በስካርም በመባከንና ስለ ዓለማዊ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝል ተጠንቀቁ! አለበለዚያ ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይይዛችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንግዲህ በገደብ የለሽ ሕይወት፣ በመጠጥ ብዛትና ስለ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝልና ያ ቀን እንደ ወጥመድ ድንገት እንዳይደርስባችሁ ተጠንቀቁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ነገር ግን ልባችሁ በመጠጥ ብዛትና በስካር፥ ስለ ኑሮም ማሰብ እንዳይዝል፥ ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ራሳችሁን ጠብቁ፤ በመብልና በመጠጥ፥ በመቀማጠልና የዓለምን ኑሮ በማሰብ ልባችሁን አታደንድኑ፤ ያቺ ቀንም በድንገት ትደርስባችኋለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ልባችሁ በመጠጥ ብዛትና በስካር ስለ ትዳርም በማሰብ እንዳይከብድ፥ ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ |
ስለዚህ በዚያን ምሽት አባታቸውን እንደገና የወይን ጠጅ አጠጥተው አሰከሩት፤ ታናሽቱ ልጁም ከእርሱ ጋር ግንኙነት አደረገች፤ አሁንም እጅግ ሰክሮ ስለ ነበር ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም።
ይሁን እንጂ እያንዳንዱ ሰው ይህ መጥፎ ዕድል መቼ እንደሚገጥመው አያውቅም፤ ወፍ በራ በወጥመድ ውስጥ እንደምትገባ፥ ዓሣም በመጥፎ አጋጣሚ በመረብ እንደሚያዝ እንዲሁም የሰው ልጅ ሁሉ ሳያስበው ድንገት በሚደርስበት በክፉ አጋጣሚ ይጠመዳል።
ነቢያቱና ካህናቱ እንኳ ሰክረው ይንገዳገዳሉ፤ ብዙ ወይን ጠጅና የሚያሰክርም ጠንካራ መጠጥ ስለ ጠጡ አእምሮአቸው ታውኮ ይሰናከላሉ፤ ነቢያቱ ሰክረው ከመደናበራቸው የተነሣ እግዚአብሔር የገለጠላቸውን ራእይ አያስተውሉም፤ ካህናቱም እጅግ ስለሚሰክሩ ለሚቀርብላቸው ጉዳይ ተገቢውን ውሳኔ መስጠት አይችሉም።
“አንተና ልጆችህ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ ጠጥታችሁ ወደ መገናኛው ድንኳን እንዳትገቡ ተጠንቀቁ፤ ይህን ብታደርጉ ትሞታላችሁ፤ ይህም ሕግ ከእናንተ በኋላ በሚነሣውም ትውልድ ዘንድ ሁሉ ተጠብቆ መኖር አለበት።
በእሾኻማ ቊጥቋጦ መካከል የተዘራው የሚያመለክተው፥ ቃሉን ለጊዜው የሚሰማውን ሰው ነው፤ ይሁን እንጂ የዚህ ዓለም ሐሳብና የሀብት ፍቅር ወደ ልቡ ገብቶ ቃሉን ስለሚያንቀው ያለ ፍሬ ይቀራል።
“እናንተም ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ሰዎች ለፍርድ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በየምኲራቡም ይገርፉአችኋል፤ ምስክር እንድትሆኑኝ በእኔ ምክንያት በገዢዎችና በነገሥታት ፊት ለፍርድ ትቆማላችሁ።
ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እንዳትሳሳቱ ተጠንቀቁ! ብዙዎች ‘እኔ ክርስቶስ ነኝ! እነሆ፥ ጊዜው ቀርቦአል!’ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ እነርሱን አትከተሉአቸው።
በእሾኽም ቊጥቋጦ መካከል የወደቀው ዘር የሚያመለክተው ቃሉን ለጊዜው የሚሰሙትን ሰዎች ነው፤ ነገር ግን የዚህ ዓለም ሐሳብና ሀብት፥ የምድራዊ ኑሮ ምቾትም አንቆ ያለ ፍሬ ያስቀራቸዋል።
እኔ ግን የጻፍኩላችሁ ክርስቲያኖች ተብለው ከሚያመነዝሩ፥ ወይም ከሚስገበገቡ፥ ወይም ጣዖት ከሚያመልኩ፥ ወይም የሰውን ስም ከሚያጠፉ፥ ወይም ከሚሰክሩ፥ ወይም ከቀማኞች ጋር አትተባበሩ ብዬ ነው። እንደእነዚህ ካሉት ሰዎች ጋር፥ መብል አብራችሁ አትብሉ።
እንደዚህ ያለው ሰው የዚህን ርግማን ቃላት ሰምቶ ምንም እንኳ በራሴ መንገድ ብቀጥል እኔ እድናለሁ ብሎ በልቡ ቢያስብ በደጎችና በክፉዎች ሰዎች ላይ ጥፋትን ያመጣል።
ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጐድልበት ተጠንቀቁ፤ እንዲሁም ምንም መራራ ፍሬ የሚያፈራ ሥር በመካከላችሁ እንዳይበቅልና እንዳያስቸግራችሁ ብዙዎችንም እንዳያረክስ ተጠንቀቁ።
የጌታ ቀን ግን እንደ ሌባ በድንገት ይመጣል፤ በዚያን ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፤ ፍጥረት ሁሉ በእሳት ተቃጥሎ ይጠፋል። ምድርና በእርስዋም ላይ ያለው ነገር ሁሉ ይቃጠላል፤
ስለዚህ ወዳጆች ሆይ! ይህ ሁሉ የሚሆንበትን ቀን በመጠባበቅ ላይ ካላችሁ፥ ጌታ ያለ ነውር ወይም ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም እንዲያገኛችሁ በትጋት ኑሩ፤
እንግዲህ ምን ዐይነት ትምህርት እንደ ተቀበልክና እንደ ሰማህ አስታውስ፤ ጠብቀውም፤ ንስሓም ግባ፤ ባትነቃ ግን እንደ ሌባ በድንገት እመጣብሃለሁ፤ በምን ሰዓት ወደ አንተ እንደምመጣ አታውቅም።
አቢጌልም እንደ ቤተ መንግሥት ግብር ታላቅ ግብዣ በማድረግ ላይ ወደነበረው ወደ ናባል ተመልሳ ሄደች፤ እርሱም ሰክሮ በደስታ ይፈነድቅ ስለ ነበር እስከ ማግስቱ ጧት ድረስ ምንም ቃል አልነገረችውም፤