እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና “ለዘርህ የምሰጠው ምድር ይህ ነው” አለው፤ ከዚህ በኋላ አብራም ለተገለጠለት አምላክ በዚያ ቦታ መሠዊያ ሠራ።
ኢያሱ 21:43 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው ሊሰጣቸው በመሐላ ቃል የገባላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤላውያን ሰጠ። ምድሪቱንም ከወረሱ በኋላ በዚያ ተደላድለው ኖሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው ይሰጣቸው ዘንድ የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ እነርሱም ምድሪቱን ወረሱ፣ መኖሪያቸውም አደረጓት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ለአባቶቻቸው ለመስጠት የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ይሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ይሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸው ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፥ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም። |
እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና “ለዘርህ የምሰጠው ምድር ይህ ነው” አለው፤ ከዚህ በኋላ አብራም ለተገለጠለት አምላክ በዚያ ቦታ መሠዊያ ሠራ።
አብርሃምን እንደ ባረከ አንተንና ዘርህን ይባርክ! ይህንንም ለአብርሃም ሰጥቶት የነበረውንና አንተም ስደተኛ ሆነህ የኖርክበትን ምድር ርስት አድርጎ ይስጥህ!”
ልጆቻቸው የከነዓንን ምድር ድል አድርገው ያዙ፤ በዚያ ይኖሩ የነበሩትንም ሕዝብ በፊታቸው ሆነህ አንተ ድል ነሣህላቸው፤ በነገሥታትና በዚያች የከነዓን አገር ሕዝብ ላይ የፈለጉትን ሁሉ ያደርጉባቸው ዘንድ ኀይልን ሰጠሃቸው።
እርሱም ለአንተ ታማኝ እንደ ሆነ ተመልክተህ፥ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳንን አደረግህ፤ ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ኢያቡሳውያንና ጌርጌሳውያን የሚኖሩባትንም የከነዓንን ምድር ለዘሮቹ መኖሪያ ርስት አድርገህ ልትሰጠው ቃል ገባህለት፤ አንተ ታማኝ ስለ ሆንክ ቃል ኪዳንህን አጽንተህ ጠብቀሃል።
እነርሱ ምድርን የወረሱት በሰይፋቸው አይደለም፤ ድል አድርገው የወሰዱትም በራሳቸው ኀይል አይደለም፤ ይህን ሁሉ ያደረጉት አንተ ስለ ወደድካቸውና ከእነርሱም ጋር በመሆን በኀይልህና በብርታትህ ስለ ረዳሃቸው ነው።
እነርሱንም ከግብጻውያን እጅ ለማዳን ወርጃለሁ፤ ከግብጽም አውጥቼ አሁን ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን፥ የሚኖሩባትን፥ በማርና በወተት የበለጸገችውን ሰፊና ለም የሆነችውን ምድር እሰጣቸዋለሁ።
ነገር ግን ወደዚህች ምድር መጥተው ከወረሱአት በኋላ ለቃልህ መታዘዝንና በአስተማርካቸው ሕግ ጸንተው መኖርን እምቢ አሉ፤ ያዘዝካቸውንም ነገር ሁሉ አልፈጸሙም፤ ከዚህም የተነሣ ይህን ሁሉ ጥፋት አመጣህባቸው።
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለዘሮቻቸው አወርሳት ዘንድ ለአብርሃም ለይስሐቅና ለያዕቆብ በመሐላ ቃል የገባሁላቸው የተስፋ ምድር ይህች ናት፤ እነሆ፥ እርስዋን በዐይንህ እንድታያት አድርጌአለሁ፤ ወደዚያች መግባት ግን አይፈቀድልህም።”
ያዕቆብና ቤተሰቡ ወደ ግብጽ ወርደው በዚያ ሲኖሩ ግብጻውያን የጭቈና ቀንበር ጫኑባቸው፤ የቀድሞ አባቶቻቸውም ርዳታ ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን ላከላቸው፤ እነርሱም ከግብጽ መርተው በማውጣት በዚህች ምድር እንዲሰፍሩ አደረጉአቸው፤