ዮሐንስ 17:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አባት ሆይ! ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድከኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ እነዚህ አንተ የሰጠኸኝም እኔ ባለሁበት ከእኔ ጋር እንዲኖሩ እወዳለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አባት ሆይ፤ እነዚህ የሰጠኸኝ እኔ ባለሁበት እንዲሆኑ፣ ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝንም ክብሬን እንዲያዩ እፈልጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባት ሆይ! ዓለም ሳይፈጠር በፊት ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ፥ የሰጠኸኝ እነርሱ ደግሞ እኔ ባለሁበት ከእኔ ጋር ይሆኑ ዘንድ እወዳለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባት ሆይ፥ የሰጠኸኝ እነዚህ እኔ ባለሁበት አብረውኝ ይኖሩ ዘንድና የሰጠኸኝን ክብሬን ያዩ ዘንድ እወድዳለሁ፤ ዓለም ሳይፈጠር ወድደኸኛልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ እኔ ባለሁበት የሰጠኸኝ እነርሱ ደግሞ ከእኔ ጋር ይሆኑ ዘንድ እወዳለሁ። |
ጌታውም ‘መልካም አደረግህ፤ አንተ ታማኝና ደግ አገልጋይ! በጥቂት ነገር ታማኝ ሆነህ ስለ ተገኘህ በብዙ ነገር ላይ እሾምሃለሁ፤ ና የጌታህን ደስታ ለመካፈል ግባ!’ አለው።
ጌታውም ‘መልካም ነው! አንተ ታማኝና መልካም አገልጋይ በጥቂት ነገር ታማኝ ሆነህ ስለ ተገኘህ በብዙ ነገር ላይ እሾምሃለሁ፤ ና የጌታህን ደስታ ለመካፈል ግባ!’ አለው።
በዚያን ጊዜ ንጉሡ በቀኙ በኩል ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ ‘እናንተ አባቴ የባረካችሁ! ኑ! ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ!
በአባቴ መንግሥት አዲሱን የወይን ፍሬ ጭማቂ ከእናንተ ጋር እስከምጠጣበት ቀን ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ ከዚህ የወይን ፍሬ ጭማቂ ዳግመኛ አልጠጣም እላችኋለሁ፤”
እነዚያ ጌታቸው ድንገት በመጣ ጊዜ፥ ነቅተው ሲጠብቁ የሚያገኛቸው አገልጋዮች እንዴት የተመሰገኑ ናቸው? በእውነት እላችኋለሁ፤ እርሱ ባጭር ታጥቆ በማእድ ያስቀምጣቸዋል፤ ቀርቦም ያገለግላቸዋል።
አሁን በመስተዋት እንደምናየው ዐይነት በድንግዝግዝ እናያለን፤ በዚያን ጊዜ ግን በግልጥ እናያለን፤ አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያን ጊዜ ግን እግዚአብሔር እኔን የሚያውቀኝን ያኽል ሙሉ ዕውቀት ይኖረኛል።
እኛ ሁላችን ባልተሸፈነ ፊት ሆነን በመስታዋት እንደሚታይ ዐይነት የጌታን ክብር እናንጸባርቃለን፤ እኛም መንፈስ የሆነውን የጌታን መልክ ለመምሰል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።
“ብርሃን በጨለማ ውስጥ ይብራ!” ብሎ የተናገረ እግዚአብሔር በክርስቶስ መልክ የሚያበራውን የእግዚአብሔርን ክብር የማወቅ ብርሃን እንዲሰጠን ብርሃኑን በልባችን ውስጥ እንዲበራ አደረገ።
በእነዚህ በሁለቱ ሐሳቦች መካከል ተይዤአለሁ፤ በአንድ በኩል ከክርስቶስ ጋር መሆን ከሁሉ የሚበልጥ ነገር ስለ ሆነ ከዚህ ሕይወት ተለይቼ ከክርስቶስ ጋር መሆንን እፈልጋለሁ ይኸውም ከክርስቶስ ጋር መኖር እጅግ የተሻለ ስለ ሆነ ነው።
ከዚህ በኋላ እኛ በሕይወት የምንገኘው ጌታን በአየር ላይ ለመገናኘት ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ ለዘለዓለምም ከጌታ ጋር እንሆናለን።
እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ በኢየሱስ አማካይነት እርሱን ከሞት ባስነሣውና ክብርን በሰጠው በእግዚአብሔር ትተማመናላችሁ።
ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ወደፊት ምን እንደምንሆንም ገና አልታወቀም፤ ነገር ግን ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እውነተኛ መልኩን ስለምናይ እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን።