ሕዝቅያስም መልእክተኞቹን በደስታ ተቀበላቸው፤ በቤተ መንግሥቱም የዕቃ ግምጃ ቤት ያለውን ሀብት በሙሉ፥ ብሩንና ወርቁን፥ ቅመማ ቅመሙንና ሽቶውን፥ የጦር መሣሪያውንም ሁሉ አሳያቸው፤ በቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤትም ሆነ በመንግሥቱ በማንኛውም ስፍራ ካለው ሀብት ሁሉ ሕዝቅያስ ያላሳያቸው አንድም አልነበረም።
ኤርምያስ 9:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰው ሬሳ የትም እንደሚጣል ቈሻሻ በየስፍራው ተበትኖአል፤ አጫጆች ቈርጠው እንደ ጣሉትና ማንም እንደማይሰበስበው ቃርሚያ ሆኖአል፤ እግዚአብሔር እንድናገር ያዘዘኝ ይህ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህ በሉ፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘የሰዎች ሬሳ፣ በሜዳ እንደ ተጣለ ጕድፍ፣ ማንም እንደማይሰበስበው፣ ከዐጫጅ ኋላ እንደ ተተወ ቃርሚያ ይወድቃል።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተናገር፥ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘የሰውም ሬሳ እንደ ጉድፍ በእርሻ ላይ፥ ማንምም እንደማይሰበስበው ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ይወድቃል።’ ” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰዎቻችሁም ሬሳ እንደ ጕድፍ በእርሻ ላይ፥ ማንም እንደማይሰበስበው ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ይወድቃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰውም ሬሳ እንደ ጕድፍ በእርሻ ላይ፥ ማንምም እንደማይሰበስበው ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ይወድቃል። |
ሕዝቅያስም መልእክተኞቹን በደስታ ተቀበላቸው፤ በቤተ መንግሥቱም የዕቃ ግምጃ ቤት ያለውን ሀብት በሙሉ፥ ብሩንና ወርቁን፥ ቅመማ ቅመሙንና ሽቶውን፥ የጦር መሣሪያውንም ሁሉ አሳያቸው፤ በቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤትም ሆነ በመንግሥቱ በማንኛውም ስፍራ ካለው ሀብት ሁሉ ሕዝቅያስ ያላሳያቸው አንድም አልነበረም።
ኢሳይያስም “በቤተ መንግሥቱ ምን አዩ” ሲል ጠየቀው። ሕዝቅያስም “ሁሉን ነገር አይተዋል፤ በግምጃ ቤቱ ካለው ሀብት ሁሉ ለእነርሱ ያላሳየኋቸው አንድም ነገር የለም” አለ።
ከሬሳውም የሚተርፈው እንደ ፍግ በዚያ ይበተናል፤ ስለዚህም ማንም እርስዋነትዋን ለይቶ በማወቅ፦ ይህች ኤልዛቤል ናት፥ ሊል አይችልም’ ያለው ነው።”
እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ በጣም ተቈጥቶአል፤ በኀያልነቱም ይቀጣቸዋል፤ ተራራዎች ይናወጣሉ፤ የሞቱ ሰዎችም አስከሬን እንደ ጥራጊ በየመንገዱ ዳር ይወድቃል፤ ይህም ሁሉ ሆኖ የእግዚአብሔር ቊጣ አይበርድም፤ እንደገናም ሊቀጣቸው ተዘጋጅቶአል።
ሁሉም በአሠቃቂ በሽታ ያልቃሉ፤ የሚያለቅስላቸውም ሆነ የሚቀብራቸው እንኳ አያገኙም፤ ሬሳቸው እንደ ጒድፍ በሜዳ ላይ ይከመራል፤ በጦርነትና በራብ ያልቃሉ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ምግብ ይሆናል።
በዚያን ቀን እግዚአብሔር በሞት የሚቀጣቸው ሰዎች ሬሳ ከምድር ዳርቻ እስከ ምድር ዳርቻ ይረፈረፋል፤ የሚያለቅስላቸውም ሆነ ሰብስቦ የሚቀብራቸው አያገኙም፤ ስለዚህ እንደ ጥራጊ በሜዳ ላይ ተጥለው ይቀራሉ።
ዐፅሞቻቸው ተሰብስበው በመቀበር ፈንታ፥ እንደ ጒድፍ የትም ይጣላሉ፤ እነርሱም፥ ሕዝቡ በማምለክና ምክር በመጠየቅ በፍቅር ያገለግሉአቸው በነበሩት በፀሐይ፥ በጨረቃና በከዋክብት ፊት ይበተናሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ኃጢአት በመሥራት እኔን ስለ በደሉ እንደ ዕውሮች እስኪደናበሩ ድረስ በሰዎች ላይ ታላቅ መከራ አመጣለሁ፤ ደማቸው እንደ ትቢያ ይፈስሳል፤ ሬሳቸውም እንደ ጒድፍ የትም ይጣላል።”