አንተ በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ የአገልጋዮችህን የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፤ ቅን የሆነውንም ነገር ማድረግ ይችሉ ዘንድ አስተምራቸው፤ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሆይ፥ ለዘለዓለም ርስት አድርገህ ለሕዝብህ በሰጠሃቸው በዚህች ምድር ዝናብ እንዲዘንብ አድርግ።
ኤርምያስ 6:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “በየጐዳናው ቆማችሁ ተመልከቱ፤ ጥንታዊና መልካም የሆነችው መንገድ የትኛዋ እንደ ሆነች ጠይቃችሁ ተረዱ፤ ባገኛችኋትም ጊዜ በእርስዋ ሂዱ፤ በሰላምም ትኖራላችሁ።” ሕዝቡ ግን “በእርስዋ አንሄድም!” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “መንታ መንገድ ላይ ቁሙ፣ ተመልከቱም፤ መልካሟን፣ የጥንቷን መንገድ ጠይቁ፤ በርሷም ላይ ሂዱ። ለነፍሳችሁ ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እናንተ ግን፣ ‘በርሷ አንሄድም’ አላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ይላል፦ “በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርሷም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እነርሱ ግን፦ ‘አንሄድባትም’ አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፤ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች ዕወቁ፤ በእርስዋም ላይ ሂዱ፤ ለነፍሳችሁም መድኀኒትን ታገኛላችሁ፤” እነርሱ ግን፥ “አንሄድባትም” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፥ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፥ እነርሱ ግን፦ አንሄድባትም አሉ። |
አንተ በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ የአገልጋዮችህን የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፤ ቅን የሆነውንም ነገር ማድረግ ይችሉ ዘንድ አስተምራቸው፤ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሆይ፥ ለዘለዓለም ርስት አድርገህ ለሕዝብህ በሰጠሃቸው በዚህች ምድር ዝናብ እንዲዘንብ አድርግ።
በመንፈሳዊ ጉዳይ ሁሉ ወሳኝ ሥልጣን የሚኖረው ሊቀ ካህናቱ አማርያ ነው፤ በሌላው ጉዳይ ሁሉ ወሳኝ ሥልጣን የሚኖረው የይሁዳ አስተዳዳሪ የሆነው የእስማኤል ልጅ ዘባድያ ነው፤ ሌዋውያን በፊታችሁ እንደ ባለሥልጣን ሆነው ያገለግላሉ፤ ያለ ፍርሀት በድፍረት ሥሩ! እግዚአብሔርም መልካም ሥራ ከሚሠሩት ጋር ይሁን!”
ከመንገድ ወጥታችሁ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ብትባዝኑ ከበስተኋላችሁ “ትክክለኛው መንገድ ይህ ነው! በዚህ ሂድ” የሚለውን ድምፅ ትሰማላችሁ።
እኔ ብቻ አምላክ መሆኔንና ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ዕወቁ፤ በቀድሞ ዘመን የተደረጉትን የጥንቱን ነገሮች አስታውሱ፤ እኔ አምላክ ነኝ፤ እኔንም የሚመስል ሌላ የለም።
የሕዝቤን አካሄድ በሙሉ ልባቸው ተቀብለው እነርሱ ከዚህ በፊት ሕዝቤን በባዓል ስም መማል እንዳስተማሩአቸው ዐይነት ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው የሚምሉ ከሆነ በሕዝቤ መካከል እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ፤
እነርሱም ‘ስለምን ብለን ይህን እናደርጋለን? እንዲያውም ያቀድነውን ሁሉ በመፈጸም ከምንጊዜውም ይልቅ እልኸኞችና ዐመፀኞች መሆን እንችላለን’ ብለው ይመልሱልሃል።”
ሕዝቤ ግን እኔን ረስተዋል፤ ከንቱ ለሆኑ ጣዖቶችም ዕጣን ያጥናሉ፤ እነርሱም ባልታወቀ መንገድ እንዲሄዱ አድርገዋቸዋል፤ ተሰናክለውም የቀድሞውን መንገድ ትተዋል።
እስራኤል ሆይ! ከሌሎች አማልክት ጋር ለማመንዘር በየስፍራው በመዞር ጫማሽን አትጨርሺ፤ ጉሮሮሽም በውሃ ጥም አይድረቅ፤ አንቺ ግን ‘እኔ ባዕዳን አማልክትን ስለ ወደድኩና እነርሱን ለመከተል ስለ ቈረጥኩ ወደ ኋላ አልመለስም!’ ” ብለሻል።
በብልጽግና በምትኖሩበት ጊዜ እግዚአብሔር ተናገራችሁ፤ እናንተ ግን ማዳመጥ እምቢ አላችሁ፤ ከመጀመሪያ ጀምሮ የምታደርጉት ይህንኑ ነው። እግዚአብሔርንም መታዘዝ እምቢ አላችሁ።
ለራሳችሁ የመንገድ ምልክቶችን አድርጉ፤ መንገድንም የሚመሩ ዐምዶችን ትከሉ፤ የሄዳችሁበትን ዐውራ ጐዳና አተኲራችሁ ተመልከቱ፤ ሕዝቤ እስራኤል ሆይ! ወደ እነዚህ ከተሞቻችሁ ተመለሱ።
ወደ ጽዮን የሚያደርሰውን መንገድ ይጠይቃሉ፤ አቅጣጫውንም ተከትለው ይጓዛሉ፤ ከእኔም ጋር ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፤ ከቶም አያፈርሱትም።
ነገር ግን እኔ አምላካቸው ስሆን እነርሱም ሕዝቤ ይሆኑ ዘንድ ለእኔ መታዘዝ እንደሚገባቸው ብቻ ነገርኳቸው፤ ሁሉ ነገር እንዲከናወንላቸው ከፈለጉም እኔ በሰጠኋቸው ሥርዓት እንዲኖሩ አዘዝኳቸው።
እነርሱ ግን መስማት አልፈለጉም፤ ትኲረትም አልሰጡትም፤ በዚህ ፈንታ በእልኽና በክፋት የተሞላው ልባቸው የመራቸውን አደረጉ፤ ወደ ፊት ሳይሆን ወደ ኋላቸው ሄዱ።
ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “አሁን ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ብርሃን አለ፤ ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማ የሚመላለስ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።
በቤርያ ያሉት አይሁድ በተሰሎንቄ ካሉት ይልቅ ቅን አመለካከት ያላቸው ስለ ነበሩ ቃሉን በታላቅ ደስታ ተቀበሉ፤ የቃሉንም እውነተኛነት ለማረጋገጥ በየቀኑ ቅዱሳት መጻሕፍትን ይመረምሩ ነበር።
እንዲሁም አብርሃም ለተገረዙትም አባት ነው፤ ለተገረዙት አባት የሆነበትም ምክንያት በመገረዛቸው ብቻ ሳይሆን እርሱ ከመገረዙ በፊት የነበረውን እምነት በመከተላቸውም ጭምር ነው።
“የቀድሞውን ዘመን አስታውስ፤ ከዘመናት በፊት የነበረውን አስተውል፤ አባትህን ጠይቅ እርሱም ይነግርሃል፤ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ እነርሱም ይተርኩልሃል።
ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ ለመሪዎቻቸው የማይታዘዙ ሆኑ፤ ለእግዚአብሔርም ያላቸውን ታማኝነት አጓድለው የሌሎች ባዕዳን አማልክት አገልጋዮች ሆኑ፤ አባቶቻቸው የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ያከብሩ ነበር፤ እነርሱ ግን የአባቶቻቸውን ምሳሌ አልተከተሉም።