ኤርምያስ 49:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶም የተናገረው ይህ ነው፦ “የቴማን ከተማ ሕዝብ ከዚህ በፊት የነበራቸውን ጥበብ አጥተዋልን? አማካሪዎቻቸውስ ምክር መስጠት አቅቷቸዋልን? የነበራቸውስ ጥበብ የት ደረሰ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ኤዶም፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጥበብ ከቴማን ጠፍቷልን? ምክር ከአስተዋዮች ርቋልን? ጥበባቸውስ ተሟጧልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ኤዶምያስ፤ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “በውኑ በቴማን ጥበብ የለምን? ከብልሃተኞችስ ምክር ጠፍቶአልን? ጥበባቸውስ አልቆአልን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ኤዶምያስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በውኑ በቴማን ጥበብ የለምን? ከብልሃተኞችስ ምክር ጠፍቶአልን? ጥበባቸውስ አልቆአልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ኤዶምያስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውኑ በቴማን ጥበብ የለምን? ከብልሃተኞችስ ምክር ጠፍቶአልን? |
አባቱ ስለ መረቀው ዔሳው ያዕቆብን አጥብቆ ጠላው፤ በልቡም “አባቴ በቅርብ ቀን ይሞታል፤ ከዚያ በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ” ብሎ አሰበ።
የቴማን አገር ሰው የሆነው ኤሊፋዝ፥ የሹሐ አገር ሰው የሆነው ቢልዳድና የናዕማ አገር ሰው የሆነው ጾፋር፥ እነዚህ ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ነበሩ። እነርሱም በኢዮብ ላይ የደረሰውን ሥቃይ በሰሙ ጊዜ ሐዘናቸውን ሊገልጹለትና ሊያጽናኑት ከየአገራቸው ተጠራርተው በአንድነት ወደ ኢዮብ መጡ።
እግዚአብሔር ሆይ! ኢየሩሳሌም በተያዘችበት ቀን ኤዶማውያን ያደረጉትን አስብ፤ “እስከ መሠረትዋ አፈራርሳችሁ ጣሉአት!” እያሉ መጮኻቸውንም አስታውስ።
ስለ ኤዶም የተነገረ ቃል ይህ ነው፤ አንድ ሰው ከኤዶም በኩል ሆኖ “ዘብ ጠባቂ ሆይ! ሌሊቱ መቼ ይነጋ ይሆን? ሌሊቱ ሊነጋ ምን ያኽል ጊዜ እንደ ቀረው ንገረኝ” ይላል።
አስደናቂ ተአምርን አከታትዬ በማምጣት ይህ ሕዝብ እንዲገረም አደርገዋለሁ፤ የጥበበኞች ጥበብ ትሰወራለች፤ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትረሳለች።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ለሕዝቤ ለእስራኤል የሰጠኋቸውን ምድር ስላጠፉት ስለ እስራኤል ጐረቤቶችም የምናገረው ነገር አለኝ፤ እነዚያን ክፉ ሕዝቦች ከየአገራቸው ነቃቅዬ እወስዳቸዋለሁ፤ የይሁዳንም ሕዝብ ከመካከላቸው መንጥቄ አወጣቸዋለሁ።
ከሕዝቡ መካከል አንዳንድ ሰዎች፦ “ኑ በኤርምያስ ላይ ዕቅድ እናውጣ! የእግዚአብሔርን ሕግ የሚያስተምሩ ካህናት፥ ምክር የሚሰጡ ጥበበኞች፥ የእግዚአብሔርን መልእክት የሚናገሩ ነቢያት ሁልጊዜ እናገኛለን፤ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ ኤርምያስን ከማድመጥ ይልቅ በንግግሩ አጥምደን በወንጀል እንክሰሰው ተባባሉ።”
‘እነሆ በስተሰሜን ወዳሉት ነገዶችና አገልጋዬ ወደ ሆነው ወደ ባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር መልእክተኛ እልካለሁ፤ ይሁዳንና በውስጥዋ የሚኖሩትን፥ እንዲሁም በጐረቤት ያሉትን ሕዝቦች ይወጉ ዘንድ አመጣቸዋለሁ፤ ይህችን አገር ከነጐረቤቶችዋ አጠፋለሁ፤ ለማየት የሚያስፈሩና መሳለቂያ እስኪሆኑ ድረስ ለዘለዓለም ፍርስራሽ ሆነው እንዲቀሩ አደርጋቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
ስለዚህም በኤዶም ሕዝብ ላይ ያቀድኩትንና በቴማን ከተማ ሕዝብ ላይ ላደርግ የፈለግኹትን ስሙ፤ ልጆቻቸው እንኳ እንደ በግ ግልገሎች እየተጐተቱ ይወሰዳሉ፤ በእነርሱም ምክንያት የሚያያቸው ሁሉ ይደነግጣል።
ጥበበኞቻችሁ ኀፍረት ደርሶባቸዋል፤ በወጥመድ ተይዘውም ግራ ገብቶአቸዋል፤ እነርሱ ቃሌን ትተዋል፤ ታዲያ ምን ዐይነት ጥበብ ሊኖራቸው ይችላል?
እናንተ በዑፅ ምድር የምትኖሩ የኤዶም ሕዝብ ሆይ ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ! ይሁን እንጂ የእናንተም ጽዋ ተራውን ጠብቆ በመምጣት ላይ ነው፤ እናንተም ሰክራችሁ ትራቈታላችሁ።
“የኤዶም ነገሥታትና የመሪዎችዋ መቃብር እዚያ ናቸው፤ በአንድ ወቅት እነርሱ ኀያላን ነበሩ፤ አሁን በጦርነት ከተገደሉት በእግዚአብሔር ከማያምኑት ጋር በሙታን ዓለም ተጋድመዋል።
ውብ የሆነችውንም የተስፋይቱን ምድር ይወራል፤ ብዙ አገሮችም በእርሱ እጅ ይወድቃሉ፤ ነገር ግን የኤዶም፤ የሞአብና የዐሞን አገሮች ከወረራው ያመልጣሉ።
“የግብጽና የኤዶም ሰዎች በይሁዳ ሕዝብ ላይ ግፍ ስለ ፈጸሙና ንጹሑንም ሕዝብ ስለ ገደሉ፥ ‘ግብጽ ወደ በረሓነት ትለወጣለች፤ ኤዶምም ሰው የማይኖርባት ምድረ በዳ ትሆናለች።’
እግዚአብሔር በቅድስናው ከቴማን አገርና፥ ከፋራን ተራራ እንደገና ይመጣል፤ መለኮታዊ ክብሩ ሰማያትን ሸፍኖአል፤ ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል።