ኤርምያስ 46:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር” ተብሎ የሚጠራው ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ “እኔ ሕያው ነኝ፤ በተራሮች መካከል ታቦር፥ በባሕር አጠገብ ቀርሜሎስ ከፍ ብለው እንደሚታዩ እንደዚሁ በእናንተ ላይ ከፍ ብሎ የሚታይ፥ ኀይል ይመጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነው ንጉሡ እንዲህ ይላል፤ “በሕያውነቴ እምላለሁ”። በተራሮች መካከል ያለውን የታቦር ተራራ የሚመስል፣ ባሕርም አጠገብ ያለውን የቀርሜሎስ ተራራ የሚመስል አንድ የሚመጣ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ሕያው በመሆኔ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ የተባለው ንጉሥ፥ በተራሮች መካከል እንዳለ እንደ ታቦር፥ በባሕርም አጠገብ እንዳለ እንደ ቀርሜሎስ፥ እንዲሁ በእውነት ይመጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ሕያው ነኝና በተራሮች መካከል እንዳለ እንደ አጤቤርዮን፥ በባሕርም አጠገብ እንዳለ እንደ ቀርሜሎስ፥ እንዲሁ በእውነት ይመጣል፥ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ የሆነ ንጉሥ እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ሕያው ነኝና በተራሮች መካከል እንዳለ እንደ ታቦር፥ በባሕርም አጠገብ እንዳለ እንደ ቀርሜሎስ፥ እንዲሁ በእውነት ይመጣል፥ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የተባለው ንጉሥ። |
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን እውነተኛ አምላክ ነህ፤ አንተ ሕያው አምላክ፥ ዘለዓለማዊ ንጉሥ ነህ፤ አንተ በምትቈጣበት ጊዜ ዓለም ይናወጣል፤ የአሕዛብ መንግሥታትም የአንተን ቊጣ ችለው አይቆሙም።
የያዕቆብ አምላክ ግን እንደ እነርሱ አይደለም፤ እርሱ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው። እስራኤልንም የራሱ ሕዝብ እንዲሆን መርጦታል፤ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
“እነሆ የጠላት ሠራዊት እንደ ደመና አንዣቦአል፤ የጦር ሠረገሎቹ እንደ ዐውሎ ነፋስ ፈጣኖች ናቸው፤ ፈረሶቹም ከንስር ይበልጥ ይበራሉ፤ ለእኛ ወዮልን! ጠፍተናል!
አንበሳ ከተሸሸገበት ደን እንደሚወጣ፥ ሕዝብን ሁሉ የሚያጠፋ ይነሣል፤ እርሱም ይሁዳን ለማጥፋት ይመጣል፤ የይሁዳ ከተሞች ይፈራርሳሉ፤ የሚኖርባቸውም አይገኝም።
ነገር ግን በግብጽ ስለምትኖሩ እስራኤላውያን ሁሉ እኔ እግዚአብሔር በኀያሉ ስሜ በመማል የወሰንኩትን ስሙ፤ ከእናንተ ማንም ሰው ‘ሕያው ልዑል እግዚአብሔርን’ ብሎ በስሜ እንዲምል አልፈቅድም።
ሞአብና ከተሞችዋማ እነሆ ተደምስሰዋል፤ የሚያስደስቱ ወጣቶችዋም ለመታረድ ወርደዋል። እኔ ንጉሡ ይህን ተናግሬአለሁ ስሜም ‘የሠራዊት አምላክ’ ነው።
መሳፍንትዋ፥ የጥበብ ሰዎችዋ፥ መሪዎችዋ፥ የጦር አዛዦችዋና ወታደሮችዋ ጠጥተው እንዲሰክሩ አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ይተኛሉ፤ እስከ ዘለዓለም አይነቁም፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ንጉሡ ነኝ፤ ስሜም የሠራዊት አምላክ ነው።
ተራራዎችን የሠራ፥ ነፋሶችን የፈጠረ፥ ያሰበውን ነገር ለሰው የሚገልጥ፥ የቀኑን ብርሃን ወደ ጨለማ የሚለውጥ፥ በምድር ከፍታዎች ላይ የሚራመድ፥ ስሙ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው።
እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝ፤ ስሜም በሕዝቦች ዘንድ የተከበረስለሆነ፥ ከበግ መንጋዎቹ መካከል አውራ በግ እያለው ለተሳለው ስለት ነውር ያለበትን በግ መሥዋዕት የሚያቀርብልኝ የተረገመ ነው!” ይላል የሠራዊት አምላክ።
ድንበሩም መመለሻው የዮርዳኖስ ወንዝ ሆኖ፥ ከታቦር፥ ከሻሐጹማና ከቤትሼሜሽ ጋር ይዋሰናል፤ እርሱም ዐሥራ ስድስት ከተሞችንና በዙሪያቸው ያሉትን ታናናሽ ከተሞች ሁሉ ያጠቃልላል፤
የአቢኒዓምን ልጅ ባራቅን የንፍታሌም ድርሻ ከሆነችው ከቃዴስ ከተማ አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይህን ትእዛዝ ሰጥቶሃል፦ ‘ከንፍታሌምና ከዛብሎን ነገዶች ዐሥር ሺህ ሰዎች መርጠህ ወደ ታቦር ተራራ ውሰዳቸው፤