Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ኢያሱ 12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም


ሙሴ ድል ያደረጋቸው ነገሥታት

1 እስራኤላውያን ከአርኖን ሸለቆ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ በስተምሥራቅ በኩል ወዳለው ወደ አራባ ሁሉ፥ ከዮርዳኖስ ማዶ በስተምሥራቅ በኩል አሸንፈው ምድራቸውን የያዙባቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤

2 በሐሴቦን ሆኖ የሚገዛው የአሞራውያን ንጉሥ ሲሖን ነበር፤ ግዛቱም የገለዓድን እኩሌታ በማጠቃለል፥ በአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ከምትገኘው ከዓሮዔር ተነሥቶ በዚያ ሸለቆ መካከል ያለችውን የዐሞናውያን ወሰን እስከሆነው እስከ ያቦቅ ወንዝ ይደርስ ነበር፤

3 እርሱም በምሥራቅ በኩል ከዮርዳኖስ ሸለቆ የገሊላ ባሕር ድረስ፥ በቤት የሺሞት አቅጣጫ እስከ ጨው ባሕር ድረስ፥ ከጨው ባሕር ወደ ደቡብ እስከ ፒስጋ ተራራ ታች ድረስ ያለውን ያጠቃልላል።

4 እንዲሁም ከረፋያውያን ወገን የቀረው በአስታሮትና በኤድራይ ይኖር የነበረው የባሳን ንጉሥ ዖግ ነበር፤

5 ግዛቱም የሔርሞንን ተራራ፥ ሳለካን፥ እስከ ገሹርና ማዕካ ድንበሮች የሚደርሰውን የባሳንን ምድር ሁሉ ጠቅልሎ፥ የሐሴቦን ንጉሥ የሲሖን ይዞታ እስከሆነው ግዛት የገለዓድን እኩሌታ የሚጨምር ነበር።

6 እንግዲህ እነዚህ ሁለት ነገሥታት በእግዚአብሔር አገልጋይ በሙሴና በእስራኤል ሕዝብ ጦርነት ድል ሆነው ነበር፤ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴም ይህን ምድር ለሮቤልና ለጋድ ነገዶች እንዲሁም ለምናሴ ነገድ እኩሌታ በማከፋፈል ርስት አድርጎ ሰጣቸው።


ኢያሱና ድል የነሣቸው ነገሥታት

7 ኢያሱና የእስራኤል ሕዝብ ከዮርዳኖስ በስተምዕራብ ባለው ምድር የነበሩትን ነገሥታት ሁሉ ድል ነሡ፤ ይህም ምድር በሊባኖስ ሸለቆ ከሚገኘው ከባዓልጋድ ተነሥቶ በደቡብ በኩል በኤዶም አጠገብ እስካለው እስከ ሐላክ ተራራ ይደርስ ነበር፤ ኢያሱም ይህን ምድር በማከፋፈል ለእያንዳንዱ ነገድ ርስት አድርጎ ሰጠ።

8 ይህም የርስት ድርሻ ኮረብታማውን አገር በስተ ምዕራብ ያለውን የኮረብታ ግርጌ፥ የዮርዳኖስን ሸለቆና በእርሱም ኮረብታዎች ግርጌ ያሉትን በስተ ምሥራቅ በኩል የሚገኘውን ረባዳ ቦታና በደቡብ በኩል የሚገኘውን በረሓማ ምድር ሁሉ ያጠቃልል ነበር፤ ይህም ምድር ቀድሞ የሒታውያን፥ የአሞራውያን፥ የከነዓናውያን፥ የፈሪዛውያን፥ የሒዋውያንና የኢያቡሳውያን መኖሪያ ነበር።

9 የእስራኤል ሕዝብ ንጉሦቻቸውን ድል ነሥተው የያዙአቸውም ከተሞች ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፥ ኢያሪኮ፥ በቤትኤል አጠገብ ያለችው ዐይ፥

10 ኢየሩሳሌም፥ ኬብሮን፥

11 ያርሙት፥ ላኪሽ፥

12 ዔግሎን፥ ጌዜር፥

13 ደቢር፥ ጌዴር፥

14 ሖርማ፥ ዐራድ፥

15 ሊብና፥ ዐዱላም፥

16 ማቄዳ፥ ቤትኤል፥

17 ታፑሐ፥ ሔፌር፥

18 አፌቅ፥ ላሻሮን፥

19 ማዶን፥ ሐጾር፥

20 ሺምሮንመሮን፥ አክሻፍ፥

21 ታዕናክ፥ መጊዶ፥

22 ቄዴሽ፥ በቀርሜሎስ የሚገኘው ዮቅነዓም፥

23 በባሕር ጠረፍ የሚገኘው ዶር፥ በጌልገላ የሚገኘው ጎይምና

24 ቲርጻ ሲሆኑ፥ ነገሥታቱም በሙሉ ሠላሳ አንድ ነበሩ።

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos