ኢሳይያስ 47:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አንቺ በማንም ያልተደፈርሽ የባቢሎን ከተማ ሆይ! ወርደሽ በዐቧራ ላይ ተቀመጪ፤ ወርደሽ በዙፋን ላይ ሳይሆን፤ በመሬት ላይ ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ቅምጥልና ለስላሳ መባልሽ ይቀራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንቺ የባቢሎን ድንግል ልጅ ሆይ፤ ውረጂ፤ በትቢያ ላይ ተቀመጪ፤ አንቺ የባቢሎናውያን ልጅ ሆይ፤ ከዙፋንሽ ውረጂ፤ መሬት ላይ ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ ውብ ወይም ለግላጋ፣ ተብለሽ አትጠሪም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንቺ ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ በትቢያም ላይ ተቀመጪ፤ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ ከዚህ በኋላ ቅንጡና ቅምጥል አትባይምና ያለ ዙፋን በመሬት ላይ ተቀመጪ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንቺ ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ፤ በትቢያም ላይ ተቀመጪ፤ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ ለስላሳና ቅምጥል አትባዪምና ያለ ዙፋን በመሬት ላይ ተቀመጪ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንቺ ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ በትቢያም ላይ ተቀመጪ፥ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ ከዚህ በኋላ ቅልጣናምና ቅምጥል አትባይምና ያለ ዙፋን በመሬት ላይ ተቀመጪ። |
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ለእስራኤል እንደገና ምሕረትን ያደርጋል፤ የራሱ ወገኖችም አድርጎ ይመርጣቸዋል፤ እንደገናም በአገራቸው እንዲኖሩ ይፈቅድላቸዋል፤ መጻተኞችም እንኳ መጥተው ከእነርሱ ጋር ተስማምተው አብረው ይኖራሉ።
በባሕር አጠገብ ስለሚገኝ ምድረ በዳ የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። ከደቡብ በኩል የሚመጣው ዐውሎ ነፋስ ሁሉን ነገር ጠራርጎ እንደሚወስድ አስፈሪ ከሆነች ከአንዲት አገር ከባድ ጥፋት ይመጣል።
“አንቺ የሲዶን ከተማ ሆይ! የደስታሽ ዘመን አክትሞአል፤ ሕዝብሽ ተጨቊነዋል፤ ወደ ቆጵሮስ ሸሽተው ቢያመልጡ እንኳ እዚያ በሰላም አይኖሩም” ብሎአል።
ስለ እርሱም እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፥ ‘ሰናክሬም ሆይ! የኢየሩሳሌም ሕዝብ አንተን በመናቅ ያፌዙብሃል፤ በምትሸሽበትም ጊዜ ከበስተኋላህ ሆነው ራሳቸውን ይነቀንቁብሃል።
ምርኮኛይቱ ኢየሩሳሌም ሆይ! ተነሥተሽ ትቢያሽን አራግፊ፤ በዙፋን ላይም ተቀመጪ፤ እናንተም የጽዮን ምርኮኞች ሆይ! የታሰራችሁበትን ሰንሰለት ከአንገታችሁ ፍቱ።
እንደ ድንግል የምትታዪ ግብጽ ሆይ! ወደ ገለዓድ ሄደሽ የሚቀባ መድኃኒት ፈልጊ፤ የአንቺ መድኃኒት ሁሉ ከንቱ ነው፤ ሊፈውስሽ የሚችል ነገር ከቶ የለም።
ምሽጎችዋም ፍርስራሽ ሆነው እንዲቀሩ የሚያደርግ ሞአብን የሚደመስሳት እነሆ እዚህ ስለ አለ፥ በዲቦን ከተማ የምትኖሩ ሁሉ ከክብር ቦታችሁ ወርዳችሁ በምድር ትቢያ ላይ ተቀመጡ፤
ቀስታቸውንና ሰይፋቸውን ይዘዋል፤ እነርሱ ምሕረት የሌላቸው ጨካኞች ናቸው፤ ፈረሶቻቸውን ሲጋልቡ፥ ድምፃቸው እንደሚተም ባሕር ነው፤ ባቢሎን ሆይ! እነርሱ በአንቺ ላይ አደጋ ለመጣል ለዘመቻ ተዘጋጅተው እንደሚመጡ ሰዎች ወደ አንቺ እየመጡ ነው።
ባቢሎን እንደ እህል መውቂያ አውድማ ትሆናለች፤ ሕዝብዋንም እንደሚወቃ እህል ጠላት ያበራያቸዋል። እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።”
‘ስለ ተሰደብን አፈርን፤ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ወደ ተቀደሱ ስፍራዎች ባዕዳን ሰዎች ስለ ገቡ ተዋርደን አንገታችንን ደፋን።’ በሉ።
የኢየሩሳሌም ከተማ ሽማግሌዎች ጸጥ ብለው በምድር ላይ ተቀመጡ፤ እነርሱ በራሳቸው ላይ ትቢያ ነስንሰው ማቅ ለበሱ፤ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች አንገታቸውን ደፉ።
ወጣቶችና ሽማግሌዎች በተመሳሳይ ሁኔታ ሞተው በየመንገዱ ዳር ወደቁ፤ ወጣቶች ወንዶችና ሴቶች በጠላት ሰይፍ ተጨፈጨፉ፤ በቊጣህ ቀን ያለ ምሕረት እንዲታረዱ አደረግህ።
ቀደም ብለው ምርጥ ምግብ ይመገቡ የነበሩት፥ አሁን በመንገድ ላይ ወድቀዋል። ሐምራዊ ልብስ ለብሰው ያደጉት አሁን በዐመድ ክምር ላይ ተጋደሙ።
በባሕር አጠገብ ያሉ አገሮች ነገሥታት ሁሉ ከዙፋናቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውንና በእጅ ሥራ ጥልፍ ያጌጠ ልብሳቸውን አውልቀው በፍርሃት እየተንቀጠቀጡ መሬት ላይ ይቀመጣሉ፤ በአንቺ ላይ የደረሰውን አሠቃቂ ሁኔታ እያሰቡ በብርቱ ይሸበራሉ፤ በአንቺም ሁኔታ ይደነግጣሉ።
መልከ ቀና በመሆንህ እጅግ ታብየህ ነበር፤ ክብር በመፈለግህም ጥበብን አቃለልክ፤ ከዚህም የተነሣ አምዘግዝጌ ወደ መሬት ጣልኩህ፤ ለሌሎች ነገሥታትም የመቀጣጫ ምልክት አደረግሁህ።
በዚያን ጊዜ፥ የመንግሥታትን ዙፋን እገለብጣለሁ፤ ኀይላቸውንም እንዳልነበረ አደርጋለሁ፤ ሠረገላ ነጂዎችን ከነሠረገሎቻቸው እገለብጣለሁ፤ ፈረሶቻቸው ያልቃሉ፤ ፈረሰኞቻቸውም እርስ በርሳቸው ይጋደላሉ፤
እርስዋ ለራስዋ ክብርንና ምቾትን የሰጠችውን ያኽል ሥቃይና ሐዘን ስጡአት፤ እርስዋ በልብዋ ‘እንደ ንግሥት ተቀምጬአለሁ፤ መበለትም አይደለሁም፤ ሐዘንም ከቶ አይደርስብኝም’ በማለት ትመካለች።