Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 47:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 አንቺ ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ በትቢያም ላይ ተቀመጪ፤ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ ከዚህ በኋላ ቅንጡና ቅምጥል አትባይምና ያለ ዙፋን በመሬት ላይ ተቀመጪ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “አንቺ የባቢሎን ድንግል ልጅ ሆይ፤ ውረጂ፤ በትቢያ ላይ ተቀመጪ፤ አንቺ የባቢሎናውያን ልጅ ሆይ፤ ከዙፋንሽ ውረጂ፤ መሬት ላይ ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ ውብ ወይም ለግላጋ፣ ተብለሽ አትጠሪም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አንቺ በማንም ያልተደፈርሽ የባቢሎን ከተማ ሆይ! ወርደሽ በዐቧራ ላይ ተቀመጪ፤ ወርደሽ በዙፋን ላይ ሳይሆን፤ በመሬት ላይ ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ቅምጥልና ለስላሳ መባልሽ ይቀራል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አንቺ ድን​ግል የባ​ቢ​ሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ፤ በት​ቢ​ያም ላይ ተቀ​መጪ፤ የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ ለስ​ላ​ሳና ቅም​ጥል አት​ባ​ዪ​ምና ያለ ዙፋን በመ​ሬት ላይ ተቀ​መጪ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 አንቺ ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ በትቢያም ላይ ተቀመጪ፥ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ ከዚህ በኋላ ቅልጣናምና ቅምጥል አትባይምና ያለ ዙፋን በመሬት ላይ ተቀመጪ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 47:1
36 Referencias Cruzadas  

ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊትም ከእርሱ ጋር በምድር ላይ ተቀመጡ፥ ሕመሙም እጅግ እንደ በዛ አይተው ነበርና ከእነርሱ አንድ ቃል የሚናገረው አልነበረም።


ኢዮብም ሥጋውን ይፍቅበት ዘንድ ገል ወሰደ፥ በአመድም ላይ ተቀመጠ።


አንቺ ፈራሽ የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ስለ ተበቀልሽን የሚበቀልሽ የተመሰገነ ነው።


ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፥ ከጠማማም ጋር ብልህ ሆነህ ትገኛለህ።


የሰይፉንም ረድኤት መለስህ፥ በጦርነትም ውስጥ አልደገፍኸውም።


የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ባቢሎን ያየው ትንቢት፤


ስለዚህ በሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር መዓት፤ ቁጣው በሚነድበት ቀን፤ ሰማያትን እነቀንቃለሁ፤ ምድርንም ከስፍራዋ አናውጣለሁ።


ጌታ ግን ያዕቆብን ይምረዋል፥ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፥ በአገራቸውም ያኖራቸዋል፤ መጻተኛም ከእርሱ ጋር ይተባበራል፥ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይተሳሰራል።


በባሕር አጠገብ ስላለው ስለ ምድረ በዳ የተነገረ ትንቢት። ዐውሎ ነፋስ ከደቡብ እንደሚወጣ፥ እንዲሁ ከሚያስፈራ አገር ከምድረበዳ ይወጣል።


አንቺ የተሰባበርሽ የሲዶና ድንግል ልጅ ሆይ፥ ከእንግዲህ ወዲህ ደስ አይበልሽ፤ ተነሽ ወደ ኪቲም ተሻገሪ፥ በዚያም ደግሞ አታርፊም አለ።


በከፍታ የሚኖሩትን ሰዎች ዝቅ ያደርጋል፤ ከፍ ያለችውን ከተማ ያዋርዳል፥ እስከ መሬትም ድረስ ያወርዳታል፥ እስከ ትቢያም ድረስ ይጥላታል።


የጽዮን ደጆች ያዝናሉ፤ ያለቅሳሉም፤ እርሷም ተረስታ በመሬት ላይ ትቀመጣለች።


ጌታ ስለ እርሱ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ ‘ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ቀላል አድርጋሃለች፥ በንቀትም ስቃብሃለች፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ስትሸሽ ራስዋን ነቅንቃብሃለች።


ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ትቢያን አራግፊ፤ ተነሺ፥ ተቀመጪ፤ ምርኮኛይቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ የአንገትሽን እስራት ፍቺ።


ለንጉሡና ለንጉሥ እናት ለእቴጌይቱ፦ “የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ተዋርዳችሁ ተቀመጡ” በል።


ድንግሊቱ የግብጽ ልጅ ሆይ! ወደ ገለዓድ ውጪ የሚቀባንም መድኃኒት ውሰጂ፤ ብዙ መድኃኒቶችን የተጠቀምሺው በከንቱ ነው፤ ለአንቺ መዳኛ የለሽም።


በዲቦን የምትኖሪ ሆይ! ሞዓብን የሚያጠፋ ወጥቶብሻልና፥ አምባሽንም ሰብሮአልና ከክብርሽ ውረጂ በደረቅም መሬት ላይ ተቀመጪ።


ጌታ ስለ ከለዳውያን ምድር ስለ ባቢሎን በነቢዩ በኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው።


ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ፤ ጨካኞች ናቸው ምሕረትም አያደርጉም፤ ድምፃቸው እንደ ባሕር የሚተምም ነው፤ በፈረሶች ላይ ይቀመጣሉ፤ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ! ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ሰው እያንዳንዳቸው በአንቺ ላይ ተሰለፉ።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በባቢሎን ላይና በሌብ-ቃምያ በሚኖሩት ላይ አጥፊውን ነፋስ አስነሣለሁ።


የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ “የባቢሎን ሴት ልጅ በመረገጥ ላይ እንዳለ ዐውድማ ነች፤ ጥቂት ቈይታ የመከር ጊዜ ይደርስባታል።”


ስድብን ስለ ሰማን አፍረናል፤ ባዕዳን ሰዎችም በጌታ ቤት ውስጥ ወዳሉት ወደ ተቀደሱ ስፍራዎች ገብተዋልና ውርደት ፊታችንን ሸፍኖታል።


ዮድ። የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች ዝም ብለው በመሬት ላይ ተቀምጠዋል፥ ትቢያን በራሳቸው ላይ ነሰነሱ፥ ማቅም ታጠቁ፥ የኢየሩሳሌም ደናግል ራሳቸውን ወደ ምድር አዘነበሉ።


ሳን። ብላቴናውና ሽማግሌው በመንገዶች ላይ ተጋደሙ፥ ደናግሎቼና ጐበዛዝቴ በሰይፍ ወድቀዋል፥ በቁጣህ ቀን ገደልሃቸው፥ ሳትራራ አረድሃቸው።


ሄ። የጣፈጠ ነገር ይበሉ የነበሩ በመንገድ ጠፉ፥ በቀይ ግምጃ ያድጉ የነበሩ የፍግ ክምር አቀፉ።


በዚያን ጊዜ የባሕር አለቆች ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውን ያስቀምጣሉ፥ ወርቀዘቦ ልብሳቸውንም ያወልቃሉ፤ መንቀጥቀጥን ይለብሳሉ፥ በመሬት ላይ ይቀመጣሉ፥ ሁልጊዜም ይንቀጠቀጣሉ፥ በአንቺም ይደነቃሉ።


በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፤ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ፤ በምድር ላይ ጣልሁህ ያዩህም ዘንድ በነገሥታት ፊት ሰጠሁህ።


ይህ ወሬ ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፥ እርሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጐናጸፊያውን አወለቀ፥ ማቅ ለበሶ በአመድም ላይ ተቀመጠ።


የመንግሥታትንም ዙፋን እገለብጣለሁ፥ የአሕዛብ መንግሥታትን ኃይል አጠፋለሁ፤ ሰረገሎችንና ነጂዎቻቸውን እገለብጣለሁ፤ ፈረሶችንና ፈረሰኞቻቸው እያንዳንዱ በወንድሙ ሰይፍ ይወድቃሉ።


እነሆም፥ ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ሌላ መልአክ ሊገናኘው እንደመጣ እርሱም ወጣ፥ እንዲህም አለው፦


ራስዋን በአከበረችበትና በተቀማጠለችበት ልክ ሥቃይንና ኀዘንን ስጡአት። በልብዋ ‘ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ፤ መበለትም አልሆንም፤ ኀዘንም ከቶ አላይም፤’ ስላለች፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos