Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 14:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር ለሕዝቡ ለእስራኤል እንደገና ምሕረትን ያደርጋል፤ የራሱ ወገኖችም አድርጎ ይመርጣቸዋል፤ እንደገናም በአገራቸው እንዲኖሩ ይፈቅድላቸዋል፤ መጻተኞችም እንኳ መጥተው ከእነርሱ ጋር ተስማምተው አብረው ይኖራሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር ለያዕቆብ ይራራለታል፤ እስራኤልን እንደ ገና ይመርጠዋል፤ በራሳቸውም አገር ያኖራቸዋል። መጻተኞች ዐብረዋቸው ይኖራሉ፤ ከያዕቆብም ቤት ጋራ ይተባበራሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ጌታ ግን ያዕቆብን ይምረዋል፥ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፥ በአገራቸውም ያኖራቸዋል፤ መጻተኛም ከእርሱ ጋር ይተባበራል፥ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይተሳሰራል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዕ​ቆ​ብን ይም​ረ​ዋል፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ደግሞ ይመ​ር​ጠ​ዋል፤ በሀ​ገ​ራ​ቸ​ውም ያር​ፋሉ፤ መጻ​ተ​ኞ​ችም ከእ​ነ​ርሱ ጋር አንድ ይሆ​ናሉ፤ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ቤት ጋር ይጨ​መ​ራሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እግዚአብሔርም ያዕቆብን ይምረዋል፥ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፥ በአገራቸውም ያኖራቸዋል፥ መጻተኛም ከእርሱ ጋር ይተባበራል፥ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጣበቃል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 14:1
65 Referencias Cruzadas  

ለጽዮን ምሕረት የምታደርግላት ጊዜ ስለ ተቃረበና ጊዜውም አሁን ስለ ሆነ አንተ ትነሣለህ፤ ለእርስዋም ትራራለህ።


መልአኩም እንደገና “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከተሞቹ ተመልሰው እንደሚበለጽጉና ኢየሩሳሌምንም እንደ ጥንቱ እንደሚረዳ የራሱ ከተማም እንደሚያደርጋት ተናገር” አለኝ።


እነሆ፥ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ዳር እስከ ዳር ለእኔ ክብር ይሰጣሉ፤ በየትኛውም ስፍራ ለእኔ ዕጣን እያጠኑ ንጹሕ መሥዋዕት ያቀርቡልኛል፤ ሕዝቦችም ሁሉ ያከብሩኛል።


የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ ተጨቊነዋል፤ ማርከው የወሰዱአቸውም ሁሉ አጥብቀው ይዘዋቸዋል፤ ሊለቁአቸውም አልፈለጉም።


እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለሚያጽናና እና ለሚሠቃዩትም ስለሚራራ ሰማያት ሆይ! ዘምሩ፤ ምድር ሆይ! ደስ ይበልሽ፤ ተራራዎች ሆይ! እልል በሉ።


በእርግጥ እላችኋለሁ ታገኙኛላችሁ፤ እኔም ወደ ምድራችሁ እመልሳችኋለሁ፤ እናንተን ከበተንኩበት ከየትኛውም አገርና ከየትኛውም ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፤ እኔ እናንተን ነቅዬ እንድትሰደዱ ከማድረጌ በፊት ወደ ነበራችሁበት ምድር መልሼ አመጣችኋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


ወንድሞቻችሁን ሁሉ ኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቅዱስ ተራራዬ በፈረሶች፥ በሠረገሎች፥ በጋሪዎች፥ በበቅሎዎችና በግመሎች አድርገው ከተለያዩ አገሮች ለእግዚአብሔር እንደ መባ ያመጡአቸዋል፤ እነርሱንም የሚያመጡአቸው እስራኤላውያን የእህል ቊርባንን በሥርዓት በነጻ ዕቃ ለእኔ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሚያቀርቡ አድርገው ነው፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


በሕዝቦች ዘንድ በጣም ለተናቅህና ለተጠላህ፥ ለገዢዎችም አገልጋይ ለሆንክ ለአንተ፥ አዳኙ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ነገሥታት ሲያዩህ ይነሡልሃል፤ ልዑላንም ይሰግዱልሃል፤ ይህም የሚሆነው በመረጠህ በታማኙ በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ምክንያት ነው።”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የመረጥኳችሁ አገልጋዮቼ የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ! አድምጡ።


“ነገር ግን አንተ አገልጋዬ እስራኤል ሆይ! ሕዝቤ እንድትሆን የመረጥኩህ የወዳጄ የአብርሃም ዘር ነህ።


በሚመጡት ዘመናት የያዕቆብ ዘር የሆኑ የእስራኤል ሕዝብ እንደ ወይን ግንድ ሥር ይሰዳሉ፤ አብበውም ያፈራሉ፤ ፍሬአቸውም ምድርን ይሞላል።


ዘለዓለማዊ ፍቅርህን ግለጥልኝ፤ ጠላቶቼን አጥፋቸው፤ እኔ አገልጋይህ ስለ ሆንኩ ጥቃት የሚያደርሱብኝን ሁሉ ደምስሳቸው።


ለእስራኤል ሕዝብ የሰጠውን ፍቅርና ታማኝነት አስታውሶአል፤ በየስፍራው ያሉ ሕዝቦች ሁሉ የአምላካችንን ድል አድራጊነት አይተዋል።


በየትኛውም አገርና በማንኛይቱም ከተማ የንጉሡ ዐዋጅ በተነበበበት ስፍራ ሁሉ በአይሁድ ዘንድ ተድላና ደስታ ሆነ፤ በዚሁ ምክንያት አይሁድን ከመፍራት የተነሣ ከሌሎች አሕዛብ ወገኖች ብዙዎቹ የአይሁድን ሃይማኖት ተቀበሉ።


እርሱ ለአሕዛብ እውነትን የሚገልጥ ብርሃን ይሆናል፤ ለሕዝብህም ለእስራኤል ክብር ነው።”


ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘለዓለም ያሳየውን ምሕረት በማስታወስ፥ አገልጋዩን እስራኤልን ረድቶታል። ይህንንም ያደረገው ለቀድሞ አባቶቻችን የሰጠውን የተስፋ ቃል ለመፈጸም ነው።”


ከምድር ዳርቻ አመጣሁህ፥ ከአራቱም ማእዘን ጠራሁህ፤ ‘አገልጋዬ ትሆናለህ’ ብዬ መረጥኩህ እንጂ አልጣልኩህም።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የግብጽ ሀብትና የኢትዮጵያ ሸቀጥ ለእናንተ ተላልፎ ይሰጣል፤ ቁመታቸው ረጃጅም የሆነ የሳባ ሰዎችም በሰንሰለት ታስረው በመምጣት ይከተሉአችኋል፤ እጅ ነሥተውም፦ ‘እግዚአብሔር የሚገኘው በእናንተ ዘንድ ብቻ ነው፤ በሌላ አይደለም፤ ከእርሱም በቀር ሌላ አምላክ የለም’ ይላሉ።”


መራብና መጠማትም አይደርስባቸውም፤ የሚያቃጥል ነፋስ ወይም ፀሐይ አይጐዳቸውም፤ ይህም የሚሆነው የሚራራላቸው እርሱ የውሃ ምንጭ ወደሚገኝበት ቦታ ስለሚመራቸው ነው።


እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ይመልሳል፦ “እናት የምታጠባውን ልጅዋን ልትረሳ ትችላለችን? ወይስ ለወለደችው ልጅ አትራራምን? እርስዋ እንኳ ብትረሳ እኔ ግን እናንተን አልረሳም።


እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፦ “አንቺን የሚቃወሙሽን እኔ ስለምቃወም፥ ጀግና የያዘው ምርኮኛ እንኳ ይወሰዳል፤ ከጨካኝ እጅም ምርኮ ይለቀቃል፤ እኔም ልጆችሽን አድናለሁ።


በሁሉም አቅጣጫ ድንበርሽን ታሰፊያለሽ፤ ዘሮችሽ አሕዛብ የያዙትን ቦታ ያስለቅቃሉ፤ በተለቀቁትም ከተሞች ይሰፍራሉ።


ክፉዎች አካሄዳቸውን፥ ኃጢአተኞች ክፉ ሐሳባቸውን ይተዉ፤ ምሕረቱ ብዙ ስለ ሆነ ይቅር ይላቸው ዘንድ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመለሱ።


ወደ እግዚአብሔር የተጠጋ ባዕድ ሰው “እግዚአብሔር ከራሱ ሕዝብ ይለየኛል” ብሎ አያስብ፤ ጃንደረባ የሆነ ሰው ልጅ ባለመውለዱ፦ “እንደ ደረቅ ዛፍ ነኝ” አይበል።


እኔ በቊጣዬ ቀጥቼሽ ነበር፤ አሁን ግን እራራልሻለሁ። ባዕዳን ሕዝቦች ቅጽሮችሽን ይሠራሉ፤ ንጉሦቻቸውም ያገለግሉሻል።


የጨቋኞችሽ የልጅ ልጆች ወደ አንቺ ሲመጡ እጅ ይነሣሉ፤ የናቁሽም ሁሉ በእግርሽ ሥር ይንበረከካሉ፤ እነርሱም አንቺን “የእስራኤል ቅዱስ የእግዚአብሔር ከተማ የሆነችው ጽዮን” ብለው ይጠሩሻል።


ዘላቂ ርስትም ትሁንላችሁ፤ ልጆች ወልደው በመካከላችሁ የሚኖሩ ባዕዳንም ምድሪቱን በምትካፈሉበት ጊዜ የራሳቸው ድርሻ ይኑራቸው፤ እንደማንኛውም እስራኤላውያን ዜጋ ተቈጥረው ምድሪቱን ከሚካፈሉት ከእስራኤል ነገዶች ጋር ዕጣ እንዲጣልላቸው ያስፈልጋል።


ድንጋዮችዋ በአገልጋዮችህ ዘንድ የተወደዱ ናቸው፤ ለፍርስራሾችዋ እንኳ ይራራሉ።


በዚያን ጊዜ በግብጽ ውስጥ የሚገኙ አምስት ከተሞች የዕብራውያን ቋንቋ ይናገራሉ፤ በዚያም የሚኖሩ ሕዝቦች በሠራዊት አምላክ ስም ይምላሉ፤ ከእነዚህ ከተሞች አንዲቱ “የፀሐይ ከተማ” ተብላ ትጠራለች።


በባሕር አጠገብ ስለሚገኝ ምድረ በዳ የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። ከደቡብ በኩል የሚመጣው ዐውሎ ነፋስ ሁሉን ነገር ጠራርጎ እንደሚወስድ አስፈሪ ከሆነች ከአንዲት አገር ከባድ ጥፋት ይመጣል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አንቺ በማንም ያልተደፈርሽ የባቢሎን ከተማ ሆይ! ወርደሽ በዐቧራ ላይ ተቀመጪ፤ ወርደሽ በዙፋን ላይ ሳይሆን፤ በመሬት ላይ ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ቅምጥልና ለስላሳ መባልሽ ይቀራል።


በዚህ ፈንታ ‘የእስራኤልን ሕዝብ ከሰሜን አገርና ከሌሎችም እነርሱን ከበተነበት አገር ሁሉ ያስወጣ ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው ይምላሉ፤ ወደገዛ አገራቸውና ለቀድሞ አባቶቻቸው ወደ ሰጠኋቸው ምድር መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ያ ቀን በደረሰ ጊዜ በሕዝቤ ጫንቃ ላይ የተጫነውን የአገዛዝ ቀንበር እሰብራለሁ፤ ሰንሰለታቸውንም አስወግዳለሁ፤ ከዚያን በኋላ ለባዕዳን ሕዝብ ባሪያዎች አይሆኑም፤


ሕዝቤ እስራኤል ሆይ፥ እንደገና ትገነባላችሁ፤ ትገነቢአለሽም፥ እንደገና ከበሮ ትይዢአለሽ፤ ከሚደሰቱት ጋር አብረሽ በመውጣት ትጨፍሪአለሽ።


‘ስለ ተሰደብን አፈርን፤ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ወደ ተቀደሱ ስፍራዎች ባዕዳን ሰዎች ስለ ገቡ ተዋርደን አንገታችንን ደፋን።’ በሉ።


ነገር ግን በወጣትነትሽ ወራት ከአንቺ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ። ከአንቺ ጋርም የዘለዓለሙን ቃል ኪዳን አጸናለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios