ኢሳይያስ 1:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰማያት ሆይ! ስሙ፤ ምድርም አድምጪ፤ ተንከባክቤ ያሳደግኋቸው ልጆች ዐመፀኞች ሆኑብኝ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰማያት ሆይ፤ ስሙ! ምድር ሆይ፤ አድምጪ! እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናግሯልና፤ “ልጆች ወለድሁ፣ አሳደግኋቸውም፤ እነርሱ ግን ዐመፁብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰማያት ሆይ፤ ስሙ! ምድር ሆይ፤ አድምጪ! ጌታ እንዲህ ተናግሮአልና፤ “ልጆች ወለድሁ፤ አሳደግኋቸውም፤ እነርሱ ግን ዐመጹብኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአልና፥ “ሰማይ ስማ፤ ምድርም አድምጪ፤ ልጆችን ወለድሁ፤ አሳደግሁም፤ እነርሱም ዐመፁብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ተናግሮአልና ሰማያት ስሙ፥ ምድርም አድምጪ፥ ልጆችን ወለድሁ አሳደግሁም፥ እነርሱም አመጹብኝ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዐመፀኞች ለሆኑ ልጆች ወዮላቸው! እኔ ባላወጣሁላቸው ዕቅድ መመራት ይፈልጋሉ፤ ከእኔም ፈቃድ ውጪ የቃል ኪዳን ውል በመፈጸም በኃጢአት ላይ ኃጢአት ይጨምራሉ።
አብርሃም ባያውቀን፥ እስራኤል ባይቀበለንም እንኳ አንተ አባታችን ነህ፤ አምላክ ሆይ! ስምህ ከጥንት እንደ ሆነ ሁሉ አንተ አባታችን ነህ፤ አንተ ታዳጊአችን ነህ።
እናንተ ከእግዚአብሔር ርቃችሁ የነበራችሁ ሁሉ ተመለሱ፤ እርሱ ይፈውሳችኋል፤ ታማኞችም ያደርጋችኋል። እናንተም እንዲህ ብላችኋል፦ “አዎ! እግዚአብሔር አምላካችን ስለ ሆነ ወደ እርሱ እንመለሳለን፤
እኔ ወደ አገራቸው ስመራቸው ሕዝቤ ከደስታ የተነሣ እያለቀሱና እየጸለዩ ይመለሳሉ። በማይሰናከሉበት የተስተካከለ መንገድ ወደ ጥሩ ውሃ ምንጭ እመራቸዋለሁ። እኔ ለእስራኤል አባት ነኝ፤ ኤፍሬምም የበኲር ልጄ ነው።”
ምድር ሆይ! ስሚ! እነርሱ ያስተማርኳቸውን ሥርዓት ስለ ተቃወሙ፤ ለሕጌም ስላልታዘዙ ስለ ክፉ ሐሳባቸው ሁሉ እቀጣቸው ዘንድ በሕዝቡ ላይ ጥፋትን አመጣለሁ።
እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የመሰልኩትን ይህን ምሳሌ ዐመፀኞች ለሆኑት ሕዝቤ ንገራቸው፤ ‘ድስት በእሳት ላይ ጥደህ ውሃ አድርግበት፤
ስለዚህ እናንተ የእስራኤል ተራራዎች የልዑል እግዚአብሔርን ቃል አድምጡ፦ ለተራሮችና ለኰረብቶች፥ ለወራጅ ውሃዎችና ለሸለቆዎች፥ ባድማና ወና ሆነው ለተለቀቁትና በአካባቢው ላሉ ሕዝቦች ሁሉ የዘረፋ ምንጮችና የመሳለቂያ ርእስ ለሆኑት ከተሞች ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
ኢዮአታም፥ አካዝና ሕዝቅያስ በተከታታይ በይሁዳ በነገሡበት ዘመን እግዚአብሔር ለሞሬታዊው ለሚክያስ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም በራእይ በገለጠለት ጊዜ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦
እኔን ግን እግዚአብሔር በመንፈሱና በኀይሉ ሞልቶኛል፤ የእስራኤል ሕዝብ በደላቸውና ኃጢአታቸው ምን እንደ ሆነ አስታውቃቸው ዘንድ በግልጽ ትክክለኛ ፍርድን ለመስጠት ብርታትን ሰጥቶኛል።
የሠራዊት አምላክ ካህናቱን እንዲህ ይላቸዋል፦ “ልጅ አባቱን፥ አገልጋይም አሳዳሪ ጌታውን ያከብራል፤ እነሆ፥ እኔ አባታችሁ ከሆንኩ ለምን አታከብሩኝም? ጌታችሁም ከሆንኩ ለምን ክብር አትሰጡኝም? እናንተ የእኔን ስም ንቃችኋል፤ ነገር ግን ‘ስምህን የናቅነው እንዴት ነው?’ ብላችሁ ትጠይቃላችሁ።
እናንተ ወደዚህ ቦታ እስክትመጡ ድረስ አንድ ሰው ልጁን እንደሚንከባከብ በሄዳችሁበት መንገድ ሁሉ አምላካችሁ እግዚአብሔር በምድረ በዳው እንደ ተንከባከባችሁ አይታችኋል።’
እነሆ፥ እኔ በሕይወትና በሞት መካከል፥ በእግዚአብሔር በረከትና መርገም መካከል ምርጫ እሰጣችኋለሁ፤ በምታደርጉትም ምርጫ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ ምስክር አድርጌ እጠራለሁ፤ ስለዚህም እናንተና ዘሮቻችሁ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጡ።
ይህን ብታደርጉ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርስዋት ምድር ረጅም ጊዜ እንደማትኖሩባትና በፍጹም እንደምትደመሰሱ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እነግራችኋለሁ።