Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 13:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እግዚአብሔር ተናግሮአልና፤ ትዕቢታችሁን አስወግዳችሁ ስሙት፤ በጥንቃቄም አድምጡት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እግዚአብሔር ተናግሯልና፣ ስሙ፤ ልብ በሉ፤ ትዕቢተኛም አትሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ስሙ፥ አድምጡም፤ ጌታ ተናግሮአልና አትታበዩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ስሙ፤ አድ​ምጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና አት​ታ​በዩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ስሙ፥ አድምጡ፥ እግዚአብሔር ተናግሮአልና አትታበዩ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 13:15
11 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ትምክሕተኞችን ሁሉ ይጸየፋል፤ ከቅጣት እንዲያመልጡም አያደርጋቸውም።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰማያት ሆይ! ስሙ፤ ምድርም አድምጪ፤ ተንከባክቤ ያሳደግኋቸው ልጆች ዐመፀኞች ሆኑብኝ፤


ከእናንተ መካከል ለዚህ ትኲረት ሰጥቶ ስለሚመጣው ጊዜ በጥንቃቄ የሚያዳምጥ ማነው?


“የይሁዳን ኲራትና የኢየሩሳሌምን ታላቅ ትዕቢት የማስወግደው በዚህ ዐይነት ነው፤


ነገር ግን አንድ ነገር ብቻ በጥንቃቄ ልታረጋግጡ ይገባል፤ ይኸውም እኔን ብትገድሉኝ፥ እናንተና የዚህ ከተማ ነዋሪ ሕዝብ ሁሉ ንጹሕ ሰው በመግደላችሁ በደለኞች ሆናችሁ ትገኛላችሁ፤ ይህን ማስጠንቀቂያ እንድሰጣችሁ ወደ እናንተ የላከኝ በእርግጥ ራሱ እግዚአብሔር ነው።”


እናንተ ሽማግሌዎች ይህን ስሙ! በይሁዳም ምድር የምትኖሩ ሁሉ ይህን አድምጡ! ለመሆኑ ይህን የመሰለ ነገር በዘመናችሁ ወይም በቀድሞ አባቶቻችሁ ዘመን ተደርጎ ያውቃልን?


ነገር ግን የበግ መንጋ ከምጠብቅበት ቦታ ወስዶ ‘ሂድ፥ ለሕዝቤ ለእስራኤል ትንቢት ተናገር’ ብሎ ያዘዘኝ ራሱ እግዚአብሔር ነው።


በጌታ ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤ እርሱም ከፍ ያደርጋችኋል።


“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ!


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos