Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሚልክያስ 1:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የሠራዊት አምላክ ካህናቱን እንዲህ ይላቸዋል፦ “ልጅ አባቱን፥ አገልጋይም አሳዳሪ ጌታውን ያከብራል፤ እነሆ፥ እኔ አባታችሁ ከሆንኩ ለምን አታከብሩኝም? ጌታችሁም ከሆንኩ ለምን ክብር አትሰጡኝም? እናንተ የእኔን ስም ንቃችኋል፤ ነገር ግን ‘ስምህን የናቅነው እንዴት ነው?’ ብላችሁ ትጠይቃላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “ልጅ አባቱን፣ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፤ እኔ አባት ከሆንሁ፣ መከበሬ የት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ የት አለ?” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “ካህናት ሆይ፤ ስሜን የምታቃልሉት እናንተ ናችሁ። “እናንተ ግን፣ ‘ስምህን ያቃለልነው እንዴት ነው?’ ትላላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 “ስሜን የምትንቁ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባርያም ጌታውን ያከብራል፥ እኔ አባት ከሆንሁ መከበሬ የት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ?” ይላችኋል የሠራዊት ጌታ። እናንተም፦ “ስምህን የናቅነው እንዴት ነው?” ብላችኋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፣ እኔስ አባት ከሆንሁ ክብሬ ወዴት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተም፦ ስምህን ያቃለልን በምንድር ነው? ብላችኋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፥ እኔስ አባት ከሆንሁ ክብሬ ወዴት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተም፦ ስምህን ያቃለልን በምንድር ነው? ብላችኋል።

Ver Capítulo Copiar




ሚልክያስ 1:6
52 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! አገልጋዮችና ገረዶች የአሳዳሪዎቻቸውን እጅ እንደሚጠባበቁ ሁሉ እኛም እስክትምረን ድረስ የአንተን ምሕረት ለማግኘት እንጠባበቃለን።


“አባትህንና እናትህን አክብር፤ ይህን ብታደርግ እኔ በምሰጥህ ምድር የረዥም ዘመን ዕድሜ ይኖርሃል።


የሸመገሉ ሰዎች በልጅ ልጆቻቸው እንደሚመኩ ልጆችም በአባቶቻቸው ይመካሉ።


አባቶቻቸውን የሚሰድቡ፥ እናቶቻቸውንም የማያመሰግኑ ሰዎች አሉ።


በአባቱ የሚያፌዝና እናቱ በምታረጅበት ጊዜ የሚንቃት ሰው የሸለቆ ቊራዎች ዐይኖቹን ጐጥጒጠው ያወጡታል፤ ጆፌ አሞራዎችም ይበሉታል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰማያት ሆይ! ስሙ፤ ምድርም አድምጪ፤ ተንከባክቤ ያሳደግኋቸው ልጆች ዐመፀኞች ሆኑብኝ፤


ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆኑ በጎቻችሁን አላቀረባችሁልኝም፤ በመሥዋዕታችሁም አላከበራችሁኝም፤ እኔም መባ እንድታቀርቡልኝ በመጠየቅ ሸክም አልሆንኩባችሁም፤ ‘ዕጣን አቅርቡልኝም’ ብዬ አላሰለቸኋችሁም።።


ወይስ ልጅ ወላጆቹን “ለምን እንዲህ አድርጋችሁ ወለዳችሁኝ?” ብሎ ሊጠይቅ ይችላልን?


በኃጢአታችን ምክንያት ፊትህን ስላዞርክብንና ለበደላችንም ተገዢዎች እንድንሆን ስለ ተውከን ስምህን የሚጠራና አንተን ለማግኘት የሚጥር ማንም የለም።


ሆኖም አምላክ ሆይ! አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ሸክላዎች ስንሆን አንተ ሠሪአችን ነህ፤ ሁላችንም የእጅህ ሥራ ነን።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የነቢያቱና የካህናቱ መንፈሳዊ ሕይወት ተበላሽቶአል፤ ሌላው ቀርቶ በቤተ መቅደስ ውስጥ እንኳ ክፉ ነገርን ያደርጋሉ፤


“አሁን ‘አባቴ፥ የልጅነት ጓደኛዬ’ ብለሽ አልጠራሽኝምን?


እኔ ወደ አገራቸው ስመራቸው ሕዝቤ ከደስታ የተነሣ እያለቀሱና እየጸለዩ ይመለሳሉ። በማይሰናከሉበት የተስተካከለ መንገድ ወደ ጥሩ ውሃ ምንጭ እመራቸዋለሁ። እኔ ለእስራኤል አባት ነኝ፤ ኤፍሬምም የበኲር ልጄ ነው።”


የሬካብ ልጅ የኢዮናዳብ ዘሮች የቀድሞ አባታቸው ያዘዛቸውን ሁሉ ፈጽመዋል፤ እናንተ ሕዝቤ ግን አልታዘዛችሁልኝም።


ካህናቱ ሕጌን ይጥሳሉ፤ ቅዱስ ለሆነ ነገርም አክብሮት የላቸውም፤ ቅዱሱን ከርኩሱ አይለዩም፤ ንጹሕ በሆነና ባልሆነ ነገር መካከል ያለውን አያስተምሩም፤ ሰንበትንም ያቃልላሉ፤ ከዚህ የተነሣ የእስራኤል ሕዝብ እኔን አያከብሩኝም።


‘እስራኤል እኔ ባለጸጋ ሆኛለሁ፤ በሀብቴም ማንም ሰው በእኔ ላይ በደል ወይም ኃጢአት አያገኝብኝም’ ብሎ ይፎክራል።


ሕዝቤ እኔን በሚገባ ካለማወቁ የተነሣ ጠፍቶአል፤ እናንተ እኔን ለማወቅ ስላልፈለጋችሁ እኔም ካህናት ሆናችሁ እንድታገለግሉኝ አልፈልጋችሁም፤ ሕጌንም ስላቃለላችሁና ስለ ረሳችሁ ልጆቻችሁ በእኔ ዘንድ የተረሱ ይሆናሉ።


“ካህናት ሆይ! ይህን ስሙ! እናንተም የእስራኤል ሕዝብ አስተውሉ! እናንተም ንጉሣውያን ቤተሰብ ይህን አድምጡ! እነሆ ፍርድ በእናንተ ላይ መጥቶአል፤ በምጽጳ እንደ ወጥመድ፥ በታቦርም እንደ ተዘረጋ መረብ ሆናችኋል።


ከእናንተ እያንዳንዱ እናትና አባቱን ያክብር፤ እኔ ባዘዝኩት መሠረት ሰንበትን ይጠብቅ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።’


ነቢያትዋ በትዕቢት የተወጠሩና በተንኰል የተሞሉ ናቸው፤ ካህናትዋ የተቀደሰውን ያረክሳሉ፤ በሕግም ላይ ያምፃሉ።


እግዚአብሔር ለካህናቱ እንዲህ ይላል፦ “ካህናት ሆይ! አሁንም ይህ ትእዛዝ ለእናንተ ነው።


ለሁላችንም አንድ አባት ያለን አይደለምን፤ የፈጠረንስ አንድ አምላክ አይደለምን? ታዲያ ለምን የቀድሞ አባቶቻችንን ቃል ኪዳን በማፍረስ እርስ በርሳችን እምነተቢሶች እንሆናለን?


እናንተ ግን ከመንገድ ወጥታችሁ በትምህርታችሁ ብዙዎችን አሰናክላችኋል፤ ከሌዊ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አፍርሳችኋል።


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት መስካሪዎች፥ የቀን ሠራተኞችን ደመወዝ አታለው በሚያስቀሩ አሠሪዎች፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች፥ እናትና አባት የሌላቸው ልጆችንና ስደተኞችን በሚጨቊኑና እኔን በማይፈሩ ሰዎች ላይ ፈጣን ፍርዴን አስተላልፋለሁ።


እግዚአብሔር ‘አባትህንና እናትህን አክብር፤ በአባቱ ወይም በእናቱ ላይ የስድብ ቃል የተናገረ በሞት ይቀጣል’ ብሎ አዞአል።


‘ያ ሰው አባቱን [ወይም እናቱን] ማክበር አያስፈልገውም’ ትላላችሁ፤ ስለዚህ ወጋችሁን ለማጥበቅ ብላችሁ የእግዚአብሔርን ሕግ ታፈርሳላችሁ፤


አባትህንና እናትህን አክብር፤ ጐረቤትህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ፤ የሚሉት ትእዛዞች ናቸው” አለው።


ስለዚህ እናንተ እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፦ ‘በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ! ስምህ ይመስገን፤


‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ!’ የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማይ አይገባም፤ ወደ መንግሥተ ሰማይ የሚገባው በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚፈጽም ነው።


ትእዛዞችን ታውቃለህ፤ እነርሱም ‘አትግደል፤ አታመንዝር፤ አትስረቅ፤ በሐሰት አትመስክር፤ አታታል፤ አባትህንና እናትህን አክብር፤’ የተባሉት ናቸው።”


ሙሴ፦ ‘አባትህንና እናትህን አክብር፤ ደግሞም በአባቱ ወይም በእናቱ ላይ ክፉ የሚናገር ሰው በሞት ይቀጣ፤’ ይላል።


የሕግ መምህሩ ግን ራሱን ጻድቅ ለማድረግ ፈልጎ፥ “ለመሆኑ ባልንጀራዬ ማን ነው?” ሲል ጠየቀው።


ትእዛዞችን ታውቃለህ፤ እነርሱም ‘አታመንዝር፤ አትግደል፤ አትስረቅ፤ በሐሰት አትመስክር፤ አባትህንና እናትህን አክብር’ የተባሉት ናቸው።”


የሰማይ አባታችሁ መሓሪ እንደ ሆነ እናንተም እንዲሁ መሓሪዎች ሁኑ።


“እኔ የምነግራችሁን አትፈጽሙም፤ ታዲያ፥ ስለምን ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! እያላችሁ ትጠሩኛላችሁ?


“አባትህንና እናትህን አክብር” የሚለው ትእዛዝ የተስፋ ቃል ያለበት የመጀመሪያ ትእዛዝ ነው፤


እናንተ ወደዚህ ቦታ እስክትመጡ ድረስ አንድ ሰው ልጁን እንደሚንከባከብ በሄዳችሁበት መንገድ ሁሉ አምላካችሁ እግዚአብሔር በምድረ በዳው እንደ ተንከባከባችሁ አይታችኋል።’


እናንተ ሞኞችና ኅሊና ቢሶች፥ የእግዚአብሔርን ዋጋ የምትከፍሉ በዚህ ዐይነት ነውን? እርሱ የፈጠራችሁ አባታችሁ አይደለምን? የመሠረታችሁስ እርሱ አይደለምን?


“ ‘እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ባዘዝኩህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር፤ ይህን ብታደርግ ሁሉ ነገር ይሳካልሃል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ በምሰጥህ ምድር የረዥም ዘመን ዕድሜ ይኖርሃል።


ለማንም ሳያዳላ ለያንዳንዱ እንደየሥራው የሚፈርደውን እግዚአብሔርን “አባታችን” ብላችሁ የምትጠሩት ከሆነ በዚህ ዓለም በእንግድነት መጻተኞች ሆናችሁ ስትኖሩ እርሱን በመፍራት ኑሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos