እግዚአብሔር የተቀመመ ወይን ጠጅ የተሞላበትን ጽዋ በእጁ ይዞአል፤ በቊጣው ሲያፈስሰው ክፉዎች ሁሉ ይጠጡታል፤ እስከ መጨረሻው ጠብታ ድረስ ይጨልጡታል።
ዕንባቆም 2:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ራስህ ጠጥተህ በመስከር ትንገዳገዳለህ፤ አንተም በተራህ በክብር ፈንታ ውርደትን ትለብሳለህ፤ እግዚአብሔር ኀይለኛ የቅጣት ጽዋ እንድትጠጣ ያደርግሃል፤ ክብርህን ወደ ውርደት ይለውጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በክብር ፈንታ ዕፍረት ትሞላለህ፤ አሁን ደግሞ ተራው የአንተ ነውና ጠጣ፤ ኀፍረተ ሥጋህም ይገለጥ፤ በእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ያለው ጽዋ ይመለስብሃል፤ ክብርህንም ውርደት ይሸፍነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በክብር ፈንታ እፍረት ሞልቶብሃል፤ አንተ ደግሞ ጠጣ፥ እንዳልተገረዘም ተቆጠር፤ የጌታ የቀኙ ጽዋ በአንተ ላይ ይመለስብሃል፥ እፍረትም በክብርህ ላይ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በክብር ፋንታ እፍረት ሞልቶብሃል፣ አንተ ደግሞ ጠጥተህ ተንገድገድ፣ የእግዚአብሔር የቀኙ ጽዋ ይመለስብሃል፥ እፍረትም በክብርህ ላይ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በክብር ፋንታ እፍረት ሞልቶብሃል፥ አንተ ደግሞ ጠጥተህ ተንገድገድ፥ የእግዚአብሔር የቀኙ ጽዋ ይመለስብሃል፥ እፍረትም በክብርህ ላይ ይሆናል። |
እግዚአብሔር የተቀመመ ወይን ጠጅ የተሞላበትን ጽዋ በእጁ ይዞአል፤ በቊጣው ሲያፈስሰው ክፉዎች ሁሉ ይጠጡታል፤ እስከ መጨረሻው ጠብታ ድረስ ይጨልጡታል።
የአሦር ንጉሠ ነገሥት ለግብጻውያን ኀፍረት ይሆን ዘንድ መቀመጫዎቻቸው ሳይሸፈኑ ወጣቶችም ሆኑ ሽማግሌዎች ዕራቊታቸውንና ባዶ እግራቸውን ሆነው ግብጾችንና ኢትዮጵያውያንን በምርኮ ይመራቸዋል።
ጨቋኞችሽ የገዛ ሥጋቸውን እንዲበሉ አደርጋለሁ፤ በወይን ጠጅ እንደሚሰክሩ የገዛ ደማቸውን ጠጥተው እንዲሰክሩ አደርጋለሁ። ከዚህም የተነሣ እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽና ታዳጊሽ የእስራኤል ኀያል አምላክ መሆኔን የዓለም ሕዝብ ሁሉ ያውቃል።”
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ይህን በቊጣዬ ወይን የተሞላ ጽዋ ከእጄ ውሰድ እኔ ወደምልክህ ሕዝቦች ሄደህ ከእርሱ እንዲጠጡ አድርግ።
መሳፍንትዋ፥ የጥበብ ሰዎችዋ፥ መሪዎችዋ፥ የጦር አዛዦችዋና ወታደሮችዋ ጠጥተው እንዲሰክሩ አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ይተኛሉ፤ እስከ ዘለዓለም አይነቁም፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ንጉሡ ነኝ፤ ስሜም የሠራዊት አምላክ ነው።
መላው ዓለም ከእርስዋ ጠጥቶ ይሰክር ዘንድ ባቢሎን በእኔ እጅ እንደ ወርቅ ዋንጫ ነበረች፤ አሕዛብ ሁሉ የእርስዋን ወይን ጠጅ ጠጥተው አእምሮአቸውን ሳቱ።
እናንተ በዑፅ ምድር የምትኖሩ የኤዶም ሕዝብ ሆይ ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ! ይሁን እንጂ የእናንተም ጽዋ ተራውን ጠብቆ በመምጣት ላይ ነው፤ እናንተም ሰክራችሁ ትራቈታላችሁ።
የእነርሱ አምላክ ሆዳቸው ነው፤ አሳፋሪ የሆነ ነገር ለእነርሱ ክብራቸው ነው፤ ሐሳባቸውም የሚያተኲረው በምድራዊ ነገር ላይ ነው፤ ስለዚህ የእነርሱ መጨረሻ ጥፋት ነው።
በሰጠችው መጠን ስጥዋት፤ ባደረገችውም ሥራ እጥፍ ክፈልዋት፤ እርስዋ ልዩ ልዩ መጠጦችን በቀላቀለችበት ጽዋ ውስጥ እጥፍ ኀይለኛ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት፤