Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 20:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የአሦር ንጉሠ ነገሥት ለግብጻውያን ኀፍረት ይሆን ዘንድ መቀመጫዎቻቸው ሳይሸፈኑ ወጣቶችም ሆኑ ሽማግሌዎች ዕራቊታቸውንና ባዶ እግራቸውን ሆነው ግብጾችንና ኢትዮጵያውያንን በምርኮ ይመራቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እንዲሁ የአሦር ንጉሥ ወጣትና ሽማግሌ የሆኑትን የተማረኩ ግብጻውያንንና የተሰደዱ ኢትዮጵያውያንን ዕርቃናቸውንና ባዶ እግራቸውን ይወስዳቸዋል፤ መቀመጫቸውን ገልቦ በመስደድም ግብጽን ያዋርዳል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እንዲሁ የአሦር ንጉሥ የግብጽንና የኢትዮጵያን ምርኮ፥ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን፥ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ ገላቸውንም ገልጦ፥ ለግብጽ ጉስቁልና ይነዳቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እን​ዲሁ የአ​ሦር ንጉሥ የግ​ብ​ፅ​ንና የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያን ምርኮ፥ ጐበ​ዛ​ዝ​ቱ​ንና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹን ራቁ​ታ​ቸ​ው​ንና ባዶ እግ​ራ​ቸ​ውን አድ​ርጎ፥ ገላ​ቸ​ው​ንም ገልጦ ለግ​ብፅ ኀፍ​ረት ይነ​ዳ​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እንዲሁ የአሦር ንጉሥ የግብጽንና የኢትዮጵያን ምርኮ፥ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን፥ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ ገላቸውንም ገልጦ፥ ለግብጽ ጕስቍልና ይነዳቸዋል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 20:4
18 Referencias Cruzadas  

ሐኑን የዳዊትን መልእክተኞች ይዞ በአንድ በኩል ጺማቸውን ላጨ፤ ልብሳቸውንም በመቊረጥ እስከ ወገባቸው አሳጥሮ አባረራቸው፤


ስለዚህ ሐኑን የዳዊትን መልእክተኞች ይዞ ጢማቸውን ላጨ፤ ኀፍረተ ሥጋቸው እስኪታይ ድረስ ከወገባቸው በታች ያለውን ልብስ ቈረጠና ወደ አገራቸው ሰደዳቸው፤


እነርሱን በጭካኔ ለሚገዛቸው ንጉሥ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እኔ ጌታ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


እኔ በእነርሱ ራስ ላይ የቡሃና የቈረቈር በሽታ አመጣለሁ፤ የውስጥ ገላቸውም ይጋለጣል።”


ሆኖም እግዚአብሔር ጥበበኛ ነው፤ መቅሠፍትንም ያመጣል፤ ቃሉን አያጥፍም፤ በክፉ ሰዎች ቤት ላይና ክፉዎችን በሚረዱ ሰዎች ላይ ይነሣል።


ግብጻውያን ሰዎች ናቸው እንጂ አምላክ አይደሉም፤ ፈረሶቻቸውም ሥጋ ለባሾች እንጂ የተለዩ መናፍስት አይደሉም፤ እግዚአብሔር በቊጣው በሚነሣበት ጊዜ ይህ የሌሎች ረዳት የሆነው መንግሥት ይደናቀፋል፤ እርሱ ይረዳው የነበረውም መንግሥት ተንኰታኲቶ ይወድቃል፤ ሁለቱም በአንድነት ተያይዘው ይጠፋሉ።


እንግዲህ መጅ አንሥተሽ ዱቄት ፍጪ፤ ዐይነ ርግብሽን ግለጪ፤ ካባሽን አውልቂ፤ ቀሚስሽን ከፍ አድርገሽ በተራቈተ ቅልጥም ወንዙን ተሻገሪ።


ሕዝብ ሁሉ ተራቊተሽ ያዩሻል፤ ኀፍረትሽ ይጋለጣል፤ እኔ ማንንም ሳልምር ሁሉን እበቀላለሁ።”


ይህ ሁሉ የደረሰብኝ ለምንድነው? “ልብሴስ ተቀዶ የተደፈርኩት ስለምንድነው?” ብለሽ ብትጠይቂ፤ ይህ ሁሉ የደረሰብሽ ኃጢአትሽ እጅግ የከፋ በመሆኑ ምክንያት እንደ ሆነ ዕወቂ።


እግዚአብሔር ራሱ ልብሳችሁን ገፎ ኀፍረተ ሥጋችሁ እንዲጋለጥ ያደርጋል።


የግብጽ ሕዝብ ሆይ! ተማርካችሁ የምትሄዱ ስለ ሆነ ዕቃችሁን አዘጋጁ፤ ሜምፊስ ፈራርሳ ሰው የማይኖርባት በረሓ ትሆናለች፤


ሊገድሉአቸው ለሚፈልጉ ለባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ለሠራዊቱ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ሆኖም ዘግየት ብሎ ከዚህ በፊት እንደሆነው ሁሉ ግብጽ እንደገና የሰዎች መኖሪያ ትሆናለች፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


የግብጽን ኀይል በመሰባበር የሚመኩበትን ብርታት በማስወግድበት ጊዜ ጣፍናስ በጨለማ ትጋረዳለች፤ ግብጽ በደመና ትሸፈናለች፤ የከተሞችዋ ኗሪዎችም ተማርከው ይወሰዳሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በእኔ ዘንድ ኢትዮጵያውያን ከእናንተ አያንሱም፤ እናንተን ከግብጽ እንዳወጣሁ እንደዚሁም ፍልስጥኤማውያንን ከቀርጤስ፥ ሶርያውያንን ከቂር አላወጣሁምን? አውጥቻለሁ።


እናንተ የሻፊር ሕዝቦች ራቊታችሁን ምርኮኞች ሆናችሁ በዕፍረት ዕለፉ፤ የጻእናን ኗሪዎች ከከተማው ለመውጣት አይደፍሩም፤ ቤትኤጼል ራስዋ የለቅሶ ቦታ ስለ ሆነች ለእናንተ መጠጊያ ልትሆን አትችልም።


ይህም ሁሉ ሆኖ የቴብስ ከተማ በጠላት ተይዛ ሕዝቦችዋ ተማርከዋል፤ ሕፃናትዋም በድንጋይ ተፈጥፍጠው በየመንገዱ ወድቀዋል፤ በልዑላኑ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፤ ሹማምንቱንም በሰንሰለት አሰሩአቸው።


እናንተም ኢትዮጵያውያን በሰይፌ ትገደላላችሁ።


ሀብታም ለመሆን በእሳት የተፈተነውን ወርቅ ከእኔ እንድትገዛ፥ የራቊትነትህን ኀፍረት ለመሸፈን ነጭ ልብስ እንድትለብስ፥ ለማየትም እንድችል የዐይን መድኃኒት ገዝተህ እንድትቀባ እመክርሃለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos