Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ፊልጵስዩስ 3:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 የእነርሱ አምላክ ሆዳቸው ነው፤ አሳፋሪ የሆነ ነገር ለእነርሱ ክብራቸው ነው፤ ሐሳባቸውም የሚያተኲረው በምድራዊ ነገር ላይ ነው፤ ስለዚህ የእነርሱ መጨረሻ ጥፋት ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 መጨረሻቸው ጥፋት ነው፤ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፤ ክብራቸው በነውራቸው ነው፤ ሐሳባቸው በምድራዊ ነገር ላይ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 መጨረሻቸው ጥፋት ነው፤ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፤ ክብራቸው በነውራቸው ነው፤ ሐሳባቸው ምድራዊ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እነ​ዚ​ህም ፍጻ​ሜ​ያ​ቸው ለጥ​ፋት የሆነ፥ ሆዳ​ቸ​ውን የሚ​ያ​መ​ልኩ፥ ክብ​ራ​ቸ​ውም ውር​ደት የሆ​ነ​ባ​ቸው፥ ምድ​ራ​ዊ​ዉ​ንም የሚ​ያ​ስቡ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ፊልጵስዩስ 3:19
52 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሆይ! የሕይወታቸው ድርሻ የዚህ ዓለም ነገር ብቻ ከሆነ ሰዎች በእጅህ አድነኝ፤ ለምትወዳቸው ምግብን ስጣቸው፤ ልጆቻቸው ብዙ ይኑራቸው፤ የልጅ ልጆቻቸውም የተትረፈረፈ ምግብ እንዲኖራቸው አድርግ።


አንተ ብርቱ ሰው፥ በእግዚአብሔር ወገኖች ላይ ክፉ ነገር በማድረግ የእግዚአብሔር ፍቅር ዘለዓለማዊ መሆኑን እያወቅህስ ስለምን ዘወትር ትመካለህ?


እኛ እንፈጽማለን ብለን ያሰብነውን ነገር ሁሉ እናደርጋለን፤ የሰማይ ንግሥት ተብላ ለምትጠራው አምላካችን ዕጣን እናጥናለን፤ እኛና የቀድሞ አባቶቻችን፥ ንጉሦቻችንና መሪዎቻችን በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ስናደርግ በነበረው ዐይነት አሁንም የወይን ጠጅ መባ እናቀርብላታለን። ይህን ሁሉ በምናደርግበት በዚያን ጊዜ ብዙ ሲሳይ ነበረን፤ ባለጸጎችም ስለ ነበርን ምንም ችግር አልነበረብንም።


እፍኝ ገብስ እና ቊራሽ እንጀራ ለማግኘት ብላችሁ ሐሰትን ለሚያዳምጡ ለሕዝቤ ሐሰትን እየተናገራችሁ መሞት የማይገባቸውን ሰዎች በመግደልና መኖር የማይገባቸውን ሰዎች እንዲኖሩ በማድረግ ስሜ በሕዝቤ ዘንድ እንዲሰደብ አድርጋችኋል።”


ወተቱን ትጠጣላችሁ፤ ከጠጒራቸው የተሠራውንም ሱፍ ትለብሳላችሁ፤ የሰባውንም በግ ዐርዳችሁ ትበላላችሁ፤ ነገር ግን በጎችን በማሰማራት አትጠብቁም፤


“እናንተ ካህናት ቊጥራችሁ በበዛ መጠን በደላችሁም በፊቴ እየበዛ ሄዶአል፤ ስለዚህ ክብራችሁን ገፍፌ አዋርዳችኋለሁ።


የከተማይቱም ሹማምንት የሚፈርዱት በጉቦ ነው፤ ካህናቱ ያለ ዋጋ አያስተምሩም፤ ነቢያቱም ያለ ገንዘብ ትንቢት አይናገሩም፤ ይህም ሁሉ ሆኖ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለ ሆነ ምንም ዐይነት ክፉ ነገር አይመጣብንም” በማለት በእግዚአብሔር ይመካሉ።


እግዚአብሔር ስለ ሐሰተኞች ነቢያት እንዲህ ይላል፦ “ጥቅም የሚያገኙበት ሲሆን ‘ሰላም ይወርድላችኋል’ እያሉ ይሰብካሉ፤ ጥቅም በማያገኙበት ጊዜ ‘ጦርነት ይመጣባችኋል’ እያሉ በማወጅ ሕዝቡን ያስታሉ፤


እናንተ ግን ‘የእግዚአብሔር መሠዊያ የረከሰ ነው’ ብላችሁ የተናቀ መሥዋዕት ባቀረባችሁ ጊዜ አረከሳችሁት።


ኢየሱስ ግን ዞር ብሎ ጴጥሮስን፦ “አንተ ሰይጣን! ከኋላዬ ሂድ! አንተ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን ነገር ስለማታስብ ለእኔ እንቅፋት ነህ” አለው።


ከዚህ በኋላ በግራው በኩል ያሉትንም እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለተከታዮቹ መላእክት ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ!


ከዚህም በኋላ ራሴን፦ እነሆ፥ ለብዙ ዓመት የሚበቃህ ብዙ ሀብት አለህ፤ እንግዲህ ዕረፍት በማድረግ ተዝናና! ብላ! ጠጣ! ደስ ይበልህ! እለዋለሁ’ አለ።


ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ቀይ ከፋይና ቀጭን ልብስ የሚለብስ አንድ ሀብታም ሰው ነበር፤ እርሱም በየቀኑ በቅንጦት ይኖር ነበር።


እርሱም ፍርድ ሳይሰጣት ብዙ ጊዜ ቈየ፤ በኋላ ግን እንዲህ ሲል አሰበ፤ ‘ምንም እንኳ እግዚአብሔርን ባልፈራ፥ ሰውንም ባላፍር፥


እንደእነዚህ ዐይነቶቹ ሰዎች ራሳቸውን እንጂ ጌታችንን ክርስቶስን አያገለግሉም። በለዘቡና በሚያቈላምጡ ቃላት የየዋሆችን ልብ ያታልላሉ።


ታዲያ፥ በዚያን ጊዜ ምን ጥቅም አገኛችሁ? አሁን ከሚያሳፍራችሁ ነገር በቀር ምንም ጥቅም አላገኛችሁም፤ የዚህም ነገር መጨረሻ ሞት ነው።


እናንተ አሁንም ገና ሥጋውያን ናችሁ፤ እርስ በርሳችሁ ስለምትቀናኑና ስለምትከራከሩ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን? የምትሠሩትስ እንደ ተራ ሰው አይደለምን?


ታዲያ፥ እንዲህ ያለ አሳፋሪ ነገር በመካከላችሁ እያለ ለምን ትታበያላችሁ? ይልቅስ በዚህ ነገር ማዘን አይገባችሁምን? እንዲህ ዐይነቱን ሥራ የፈጸመውን ሰው ከመካከላችሁ አስወግዱ።


እንግዲህ መመካታችሁ መልካም አይደለም፤ ትንሽ እርሾ ሊጡን ሁሉ እንደሚያቦካው ታውቁ የለምን?


እነዚያ ሌሎች ሐዋርያት “እኛም እንደ እነርሱ እንሠራለን” እያሉ የሚመኩበትን ምክንያት ለማሳጣት አሁን የማደርገውን ወደፊትም ደግሞ አደርጋለሁ።


ስለዚህ እነዚህ የሰይጣን አገልጋዮች የጽድቅ አገልጋዮችን ለመምሰል ራሳቸውን ቢለውጡ አያስደንቅም፤ በመጨረሻ የሥራቸውን ዋጋ ያገኛሉ።


እነርሱ በእናንተ ሥጋ ለመመካት ብለው እንድትገረዙ ይፈልጋሉ እንጂ የተገረዙትም እንኳ ራሳቸው ሕግን አይፈጽሙም።


ሌሎቹ ግን የራሳቸውን ጥቅም ብቻ ያሳድዳሉ እንጂ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ግድ የላቸውም።


ዘወትር በላይ በሰማይ ስላሉት ነገሮች አስቡ እንጂ በምድር ላይ ስላሉት ነገሮች አታስቡ።


እነርሱ ከጌታ ፊትና ከኀያል ክብሩ ተለይተው በዘለዓለም ጥፋት ይቀጣሉ።


ይህም የሚሆነው እውነትን አናምንም ብለው በኃጢአት የሚደሰቱ ሁሉ እንዲፈረድባቸው ነው።


ከዚህ በኋላ ጌታ ኢየሱስ በአፉ እስትንፋስ የሚያጠፋውና በግርማ መምጣቱ የሚደመስሰው የዐመፅ ሰው ይገለጣል።


አእምሮአቸው በረከሰና እውነት በጠፋባቸው ሰዎች የሚደረግ የማያቋርጥ ክርክርን ነው፤ እንደነዚህ ያሉት ሰዎች እግዚአብሔርን ማምለክ የሀብት ማግኛ ዘዴ መስሎ ይታያቸዋል።


ከዳተኞች፥ ጥንቃቄ የሌላቸው፥ በትዕቢት የተነፉ፥ እግዚአብሔርን ከመውደድ ይልቅ ሥጋዊ ደስታን የሚወዱ ይሆናሉ።


እናንተ ግን ይህን በማለት ፈንታ በትዕቢታችሁ ትመካላችሁ፤ እንዲህ ያለው ትምክሕት ሁሉ ክፉ ነው።


ነገር ግን በቀድሞ ዘመን በሕዝቡ መካከል ሐሰተኞች ነቢያት እንደ ነበሩ፥ እንዲሁም በእናንተ መካከል ሐሰተኞች መምህራን ይኖራሉ፤ እነርሱ ጥፋትን የሚያስከትል ሐሰተኛ ትምህርት በስውር እንዲሠራጭ ያደርጋሉ፤ የዋጃቸውንም ጌታ ክደው ፈጣን ጥፋትን በራሳቸው ላይ ያመጣሉ።


በደል ስለ ፈጸሙ ዋጋቸውን ይቀበላሉ፤ የእነርሱ ደስታ በጠራራ ፀሐይ መስከርና ያለ ቅጥ መፈንጠዝ ነው፤ በዚህ ቅጥ ባጣ ፈንጠዝያቸው ከእናንተ ጋር በሚጋበዙበት ጊዜ አታላይ በሆነው ሥጋዊ ድርጊታቸው ነውረኞችና አሳፋሪዎች ናቸው።


እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ ራሳቸው ያዘጋጁትን ታሪክ እያወሩ ይበዘብዙአችኋል። ከብዙ ዘመን በፊት ጀምሮ ፍርድ ተዘጋጅቶላቸዋል፤ ጥፋትም በእርግጥ ይጠብቃቸዋል!


እነዚህ ሰዎች ግን ለማስተዋል ያቃታቸውን ነገር ሁሉ ይሳደባሉ፤ አእምሮ እንደሌላቸው እንስሶች በተፈጥሮ ስሜት የሚያውቁት ነገር ቢኖር እንኳ በእርሱ ይጠፋሉ።


እነዚህ ሰዎች ሁልጊዜ የሚያጒረመርሙና በምንም ነገር የማይደሰቱ ናቸው፤ የራሳቸውን ክፉ ምኞት የሚከተሉ ናቸው፤ አፋቸው በትዕቢት ቃል የተሞላ ነው፤ የራሳቸውን ጥቅም በመፈለግ ሰውን ይለማመጣሉ።


የሚፈረድባቸው መሆኑ ከብዙ ጊዜ በፊት የተጻፈባቸው አንዳንድ ሰዎች ወደ እናንተ ሾልከው ገብተዋል፤ እነርሱ የአምላካችንን ጸጋ በስድነት የሚለውጡ እግዚአብሔርን የማያመልኩ ናቸው፤ እርሱ ብቻ ገዢአችንና ጌታችን የሆነን ኢየሱስ ክርስቶስንም ይክዳሉ።


እርስዋ ለራስዋ ክብርንና ምቾትን የሰጠችውን ያኽል ሥቃይና ሐዘን ስጡአት፤ እርስዋ በልብዋ ‘እንደ ንግሥት ተቀምጬአለሁ፤ መበለትም አይደለሁም፤ ሐዘንም ከቶ አይደርስብኝም’ በማለት ትመካለች።


ነገር ግን አውሬው ተያዘ፤ ከእርሱም ጋር በፊቱ ብዙ ተአምራት ያደርግ የነበረው ሐሰተኛው ነቢይ ተያዘ፤ እርሱ የአውሬው ምልክት የነበረባቸውንና ለአውሬውም ምስል ይሰግዱ የነበሩትን ተአምራት እያደረገ ያስታቸው ነበር፤ እነዚህ ሁለቱ በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር ከነሕይወታቸው ተጣሉ።


ነገር ግን ፈሪዎች፥ እምነተ ቢሶች፥ ርኩሶች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ አመንዝሮች፥ አስማተኞች፥ ጣዖት አምላኪዎች፥ ውሸታሞች ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲን በሚቃጠለው በእሳት ባሕር ውስጥ ይሆናል፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”


እንደ ውሻ የሚልከፈከፉ፥ አስማተኞች፥ አመንዝሮች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ ጣዖት አምላኪዎች፥ ውሸትን የሚወዱና በሐሰት መንገድ የሚሄዱ ሁሉ ከከተማይቱ ውጪ ይሆናሉ።


በትእዛዜ መሠረት የሚቀርብልኝን መሥዋዕትና ቊርባን ለምን ታዋርዳላችሁ? ልጆችህ ለመሥዋዕት ከሚቀርበው ምርጥ የሆነውን እየወሰዱ በመብላት ይወፍሩ ዘንድ እነርሱን ከእኔ ይበልጥ የምታከብራቸው ለምንድነው?’


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos