ዕንባቆም 2:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 በክብር ፈንታ እፍረት ሞልቶብሃል፤ አንተ ደግሞ ጠጣ፥ እንዳልተገረዘም ተቆጠር፤ የጌታ የቀኙ ጽዋ በአንተ ላይ ይመለስብሃል፥ እፍረትም በክብርህ ላይ ይሆናል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 በክብር ፈንታ ዕፍረት ትሞላለህ፤ አሁን ደግሞ ተራው የአንተ ነውና ጠጣ፤ ኀፍረተ ሥጋህም ይገለጥ፤ በእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ያለው ጽዋ ይመለስብሃል፤ ክብርህንም ውርደት ይሸፍነዋል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 አንተ ራስህ ጠጥተህ በመስከር ትንገዳገዳለህ፤ አንተም በተራህ በክብር ፈንታ ውርደትን ትለብሳለህ፤ እግዚአብሔር ኀይለኛ የቅጣት ጽዋ እንድትጠጣ ያደርግሃል፤ ክብርህን ወደ ውርደት ይለውጣል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 በክብር ፋንታ እፍረት ሞልቶብሃል፣ አንተ ደግሞ ጠጥተህ ተንገድገድ፣ የእግዚአብሔር የቀኙ ጽዋ ይመለስብሃል፥ እፍረትም በክብርህ ላይ ይሆናል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 በክብር ፋንታ እፍረት ሞልቶብሃል፥ አንተ ደግሞ ጠጥተህ ተንገድገድ፥ የእግዚአብሔር የቀኙ ጽዋ ይመለስብሃል፥ እፍረትም በክብርህ ላይ ይሆናል። Ver Capítulo |