ዘፍጥረት 35:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ በዚያ ምድር ሲኖር ሳለ፥ ሮቤል ወደ አባቱ ቁባት ወደ ባላ ገባ። ያዕቆብም ይህን ነገር ሰማ። የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤልም በዚያ ምድር ሳለ፣ ሮቤል ከአባቱ ቁባት ከባላ ጋራ ተኛ፤ እስራኤልም ድርጊቱን ሰማ። ያዕቆብ ዐሥራ ሁለት ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም፦ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤልም በዚያች አገር በተቀመጠ ጊዜ ሮቤል ሄደ የአባቱንም ቁባት ባላን ተገናኛት፥ እስራኤልም ሰማ። የያዕቆብም ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የያዕቆብም ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም በዚያች አገር በተቀመጠ ጊዜ ሮቤል ሄደ የአባቱንም ቁባት ባላን ተገናኛት እስራኤልም ሰማ። |
ንጉሥ ዳዊት የሆነውን ነገር በሰማ ጊዜ በብርቱ ተቈጣ፤ [ነገር ግን ይወደው ስለ ነበርና የበኲር ልጁም ስለ ነበረ ልጁን አምኖንን ሊያሳዝነው አልፈለገም።]
ዳዊት በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቤተ መንግሥቱ በደረሰ ጊዜ፥ ቤተ መንግሥቱን እንዲጠብቁለት ትቶአቸው የነበሩትን ዐሥር ቊባቶቹን ወደ ሌላ ወስዶ በዘበኛ እንዲጠበቁ አደረገ፤ የሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ እንዲሰጣቸው አዘዘ፤ ይሁን እንጂ ከእነርሱ ጋር ግንኙነት አልፈጸመም፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞታቸው በቤት ተወስነው እንደ መበለቶች በመሆን ኖሩ።
የያዕቆብ የበኲር ልጅ የሆነው የሮቤል ዘሮች ቀጥሎ የተመለከቱት ናቸው፤ (ሮቤል የአባቱን አልጋ ደፍሮ በማርከሱ የብኲርናውን መብት ስላጣ፥ ያ መብት ለዮሴፍ ተሰጥቶ ነበር፤
የመገረዝንም ኪዳን ሰጠው፤ ስለዚህ አብርሃም ይስሐቅን በወለደ ጊዜ በስምንተኛው ቀን ገረዘው፤ እንዲሁም ይስሐቅ ልጁን ያዕቆብን ገረዘው። ያዕቆብም የነገድ አባቶች የሆኑትን ዐሥራ ሁለቱን ልጆቹን ገረዘ።
በመካከላችሁ አሳፋሪ የዝሙት ሥራ መኖሩ ይወራል፤ እንዲህ ዐይነቱ የዝሙት ሥራ በአሕዛብ ዘንድ እንኳ የማይደረግ ነው፤ ይኸውም የእንጀራ እናቱን እንደ ሚስት አድርጎ የሚኖር አለ ተብሎአል።
“ዮርዳኖስን ከተሻገራችሁ በኋላ ሕዝቡን ለመባረክ በገሪዛን ተራራ ላይ መቆም የሚገባቸው የስምዖን፥ የሌዊ፥ የይሁዳ፥ የይሳኮር፥ የዮሴፍና የብንያም ነገዶች ናቸው።
“ ‘የአባቱ ሚስቶች ከሆኑት ከየትኛዋም ጋር ግንኙነት በማድረግ የአባቱን ክብር የሚያዋርድ ሁሉ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይበሉ።
ቀድሞ ዐማሌቃውያን ይኖሩበት ከነበረው ከኤፍሬም ወታደሮች መጡ፤ ሌሎችም ከብንያም መጡ። ከማኪር መሪዎች፥ ከዛብሎንም በትረ መንግሥትን የሚይዙ መጡ።
እነሆ ዔሊ በዕድሜው አርጅቶ ነበር፤ ልጆቹም በእስራኤላውያን ላይ የሚያደርጉት ክፉ ነገርና በድንኳኑ ደጃፍ ከሚያገለግሉት ሴቶች ጋር እንደሚያመነዝሩ ሰማ።