Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 27:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 “ ‘የአባቱ ሚስቶች ከሆኑት ከየትኛዋም ጋር ግንኙነት በማድረግ የአባቱን ክብር የሚያዋርድ ሁሉ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይበሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 “ከአባቱ ሚስት ጋራ የሚተኛ የተረገመ ይሁን፤ የአባቱን መኝታ ያረክሳልና።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 “‘ከአባቱ ሚስት ጋር የሚተኛ የአባቱን ሚስት ገልቧልና የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 “ከእ​ን​ጀራ እናቱ ጋር የሚ​ተኛ የአ​ባ​ቱን ኀፍ​ረት ገል​ጦ​አ​ልና ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ከአባቱ ሚስት ጋር የሚተኛ የአባቱን ልብስ ገልጦአልና ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 27:20
12 Referencias Cruzadas  

“ማንም ሰው የአባቱ ሚስት ከሆነችው ከማንኛይቱም ሴት ጋር ግንኙነት በማድረግ አባቱን አያሳፍር።


ከሌሎቹ ሚስቶቹም ፍትወታዊ ግንኙነት በማድረግ አባትህን አታዋርድ።


በመካከላችሁ አሳፋሪ የዝሙት ሥራ መኖሩ ይወራል፤ እንዲህ ዐይነቱ የዝሙት ሥራ በአሕዛብ ዘንድ እንኳ የማይደረግ ነው፤ ይኸውም የእንጀራ እናቱን እንደ ሚስት አድርጎ የሚኖር አለ ተብሎአል።


አንድ ሰው የአባቱ ሚስት ከሆነችው ሴት ጋር ቢተኛ፥ የአባቱን ኀፍረተ ሥጋ ስለ ገለጠ እርሱና ሴትዮዋ ሁለቱም በሞት ይቀጡ፤ የተፈረደባቸውም በራሳቸው በደል ነው።


ደካሞችንና ረዳት የሌላቸውን በትቢያ ላይ ጥለው ራስ ራሳቸውን ይረግጣሉ፤ የተዋረዱ ምስኪኖችንም ገፍትረው ከመንገድ ያስወጣሉ፤ አባትና ልጅ ሁለቱም ከአንዲት ሴት ጋር ያመነዝራሉ፤ በዚህም ሥራቸው የተቀደሰውን ስሜን ያረክሳሉ።


አንዳንዶቹ ከእንጀራ እናታቸው ጋር በመተኛት የአባታቸውን አልጋ ይደፍራሉ፤ አንዳንዶቹ በወር አበባ ጊዜ ውስጥ ያሉትን ሴቶች በማስገደድ ግንኙነት ይፈጽማሉ።


የያዕቆብ የበኲር ልጅ የሆነው የሮቤል ዘሮች ቀጥሎ የተመለከቱት ናቸው፤ (ሮቤል የአባቱን አልጋ ደፍሮ በማርከሱ የብኲርናውን መብት ስላጣ፥ ያ መብት ለዮሴፍ ተሰጥቶ ነበር፤


ስለዚህ በቤተ መንግሥቱ ጣራ ላይ ለአቤሴሎም ድንኳን ተከሉለት፤ ሰውም ሁሉ እየተመለከተው ወደ ድንኳኑ ገብቶ ከአባቱ ቊባቶች ጋር ተገናኘ።


ይሁን እንጂ እንደ ውሃ የምትዋልል ስለ ሆንክ፥ የበላይ አለቅነት ለአንተ አይገባም፤ ወደ አባትህ አልጋ ወጥተሃል፤ የአባትህንም ቁባት ደፍረሃል።


ያዕቆብ በዚያ ምድር ሲኖር ሳለ፥ ሮቤል ወደ አባቱ ቁባት ወደ ባላ ገባ። ያዕቆብም ይህን ነገር ሰማ። የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው።


ከእናትህ ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት በማድረግ የአባትህን ክብር አታዋርድ፤ እናትህ ስለ ሆነች የእርስዋን ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ።


“የተኰላሸ ወይም የተሰለበ ሰው የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ አባል አይሁን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios