ዘፍጥረት 32:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባያቸውም ጊዜ “እግዚአብሔር ከሠራዊቱ ጋር የሚሠፍርበት ቦታ ነው” አለ፤ ስለዚህ ያንን ቦታ ማሕናይም ብሎ ጠራው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም ባያቸው ጊዜ፣ “ይህ የእግዚአብሔር ሰፈር ነው” አለ፤ የዚያንም ቦታ ስም መሃናይም አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም ባያቸው ጊዜ፥ “እነዚህ የእግዚአብሔር ሠራዊት ናቸው!” አለ። የዚያንም ስፍራ ስም ማሃናይም ብሎ ጠራው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም በአያቸው ጊዜ፥ “እነዚህ የእግዚአብሔር ሠራዊት ናቸው” አለ፤ የዚያንም ስፍራ ስም “ተዓይን” ብሎ ጠራው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ባያቸው ጊዜ፦ እነዚህ የእግዚአብሔር ሠራዊት ናቸው አለ የዚያንም ስፍራ ስም መሃናይም ብሎ ጠራው። |
“ከዚህም ጋር መረሳት የሌለበት የብንያም ክፍል በሆነችው በባሑሪም ከተማ ውስጥ የሚኖረው የጌራ ልጅ ሺምዒ አለ፤ እርሱ ወደ ማሕናይም በሄድኩበት ቀን በእኔ ላይ የስድብ ውርጅብኝ አውርዶብኛል፤ ይሁን እንጂ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ባገኘኝ ጊዜ እንደማላስገድለው በእግዚአብሔር ስም ቃል ገብቼለት ነበር፤
ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ “እግዚአብሔር ሆይ! ማየት እንዲችል ዐይኖቹን ክፈትለት!” ሲል ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የኤልሳዕ አገልጋይ ዐይኖቹ እንዲከፈቱለት ስላደረገ፥ በኰረብታው ጐን ብዙ የእሳት ፈረሶችና ሠረገሎች በኤልሳዕ ዙሪያ ተሰልፈው የሚጠብቁት መሆናቸውን ተመለከተ።
አንቺ ሱላማዊት ሆይ! ነዪ ተመለሺ፤ በደንብ አድርገን እንድንመለከትሽ ነዪ ተመለሺ። ሱላማጢስን በሁለት ሠራዊት መካከል እንደሚደረግ ጭፈራ የምትመለከቱአት ለምንድን ነው?
እንደገናም እንዲህ አለኝ፦ “ወደ አንተ የመጣሁት ለምን እንደ ሆነ ታውቃለህን? እኔ ወደ አንተ የመጣሁት በእውነት መጽሐፍ የተጻፈውን ልገልጥልህ ነው፤ አሁንም ተመልሼ የፋርስ መንግሥት አለቃ ከሆነው መንፈስ ጋር ጦርነት አደርጋለሁ፤ እኔ ከሄድኩ በኋላ የግሪክ መንግሥት አለቃ የሆነው መንፈስ ይመጣል፤ ይሁን እንጂ የእስራኤል ጠባቂ መልአክ ከሆነው ከሚካኤል በቀር እኔን የሚረዳ የለም።
ከጋድ ግዛት ተከፍለው ከግጦሽ ምድራቸው ጋር የተሰጡአቸው አራት ከተሞች ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ የሆነችው በገለዓድ ግዛት የምትገኘው ራሞት፥ ማሕናይም፥
ጐልማሳውም “የእናንተም ሆነ የጠላት ወገን አይደለሁም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሠራዊት አዛዥ እንደ መሆኔ መጠን እነሆ፥ መጥቻለሁ” አለ። ኢያሱም ወደ መሬት ወድቆ ሰገደለትና “ጌታዬ ሆይ፥ እኔ አገልጋይህ ምን ልታዘዝ?” አለው።