Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 32:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ያዕ​ቆ​ብም በአ​ያ​ቸው ጊዜ፥ “እነ​ዚህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠራ​ዊት ናቸው” አለ፤ የዚ​ያ​ንም ስፍራ ስም “ተዓ​ይን” ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ያዕቆብም ባያቸው ጊዜ፣ “ይህ የእግዚአብሔር ሰፈር ነው” አለ፤ የዚያንም ቦታ ስም መሃናይም አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ያዕቆብም ባያቸው ጊዜ፥ “እነዚህ የእግዚአብሔር ሠራዊት ናቸው!” አለ። የዚያንም ስፍራ ስም ማሃናይም ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ባያቸውም ጊዜ “እግዚአብሔር ከሠራዊቱ ጋር የሚሠፍርበት ቦታ ነው” አለ፤ ስለዚህ ያንን ቦታ ማሕናይም ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ያዕቆብም ባያቸው ጊዜ፦ እነዚህ የእግዚአብሔር ሠራዊት ናቸው አለ የዚያንም ስፍራ ስም መሃናይም ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 32:2
17 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም ወደ ምና​ሄም መጣ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም፥ ከእ​ርሱ ጋር የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ።


የኔር ልጅ አበ​ኔ​ርና የሳ​ኦል ልጅ የኢ​ያ​ቡ​ስቴ ብላ​ቴ​ኖች ከመ​ሃ​ና​ይም ወደ ገባ​ዖን ወጡ።


የሳ​ኦ​ልም ጭፍራ አለቃ የኔር ልጅ አበ​ኔር የሳ​ኦ​ልን ልጅ ኢያ​ቡ​ስ​ቴን ወስዶ ከሰ​ፈር ወደ መሃ​ና​ይም አወ​ጣው፤


የባ​ው​ሬም ሀገር ሰው የብ​ን​ያ​ማ​ዊው የጌራ ልጅ ሳሚ እነሆ! በአ​ንተ ዘንድ ነው፤ እኔም ወደ መሃ​ና​ይም በሄ​ድሁ ጊዜ ብርቱ ርግ​ማን ረገ​መኝ፤ ከዚ​ያም በኋላ ዮር​ዳ​ኖ​ስን በተ​ሻ​ገ​ርሁ ጊዜ ሊቀ​በ​ለኝ ወረደ፤ እኔም፦ ‘በሰ​ይፍ አል​ገ​ድ​ል​ህም’ ብዬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምየ​ለ​ታ​ለሁ።


በማ​ሃ​ና​ይም የሳዶ ልጅ አሒ​ና​ዳብ ነበረ፤


ኤል​ሳ​ዕም፥ “አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዐይ​ኖ​ቹን፥ እባ​ክህ፥ ግለጥ” ብሎ ጸለየ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የብ​ላ​ቴ​ና​ውን ዐይ​ኖች ገለጠ፤ እነ​ሆም፥ የእ​ሳት ፈረ​ሶ​ችና ሰረ​ገ​ሎች በኤ​ል​ሳዕ ዙሪያ ተራ​ራ​ውን ሞል​ተ​ውት አየ።


እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሠራ​ዊት ታላቅ ሠራ​ዊት እስ​ኪ​ሆን ድረስ ዳዊ​ትን ለመ​ር​ዳት ዕለት ዕለት ይመጡ ነበር።


የአ​ን​በ​ሶች ግል​ገ​ሎች ያገ​ሣሉ፥ ይነ​ጥ​ቃ​ሉም፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምግ​ባ​ቸ​ውን ይሻሉ።


መላ​እ​ክቱ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤ ሠራ​ዊቱ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገድ ሁሉ ይቅ​ር​ታና እው​ነት ነው፤ ቃል ኪዳ​ኑ​ንና ምስ​ክ​ሩን ለሚ​ፈ​ልጉ።


በከ​ንቱ ያጠ​ፉኝ ዘንድ ወጥ​መ​ዳ​ቸ​ውን ሸሽ​ገ​ው​ብ​ኛ​ልና፥ ነፍ​ሴን በከ​ንቱ አበ​ሳ​ጭ​ተ​ዋ​ታ​ልና።


በዚያ ጡቶ​ችን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፥ ሰው​ነ​ቴም አላ​ወ​ቀ​ችም፥ እንደ አሚ​ና​ዳብ ሰረ​ገላ አደ​ረ​ገኝ አለች።


ድን​ገ​ትም ከዚያ መል​አክ ጋር ብዙ የሰ​ማይ ሠራ​ዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገኑ መጡ።


ከጋ​ድም ነገድ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን በገ​ለ​ዓድ ውስጥ ራሞ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቃሚ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤


እር​ሱም፥ “እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠራ​ዊት አለቃ ነኝ፤ አሁ​ንም ወደ አንተ መጥ​ቼ​አ​ለሁ” አለ። ኢያ​ሱም ወደ ምድር በግ​ም​ባሩ ተደ​ፍቶ ሰገ​ደና፥ “በባ​ሪ​ያህ ዘንድ ምን አቁ​ሞ​ሃል?” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos