ዘፍጥረት 25:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ዐይነት አብርሃም በቂ ዕድሜ አግኝቶ ካረጀ በኋላ ሞተ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዐረፈ፤ ዕድሜ ጠግቦ በመልካም ሽምግልና ሞተ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመጨረሻዋ እስትንፋሱ አብርሃም ነፍሱን ሰጠ፥ በመልካምም ሽምግልና ሞተ፥ ሸምግሎ፥ ብዙ ዘመንም ጠገበ፥ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም መልካም ሽምግልናን ሸምግሎ፥ ዘመኑንም ፈጽሞ ሞተ፤ ወደ ወገኖቹም ተጨመረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃናም ነፍሱን ሰጠ በመልካም ሽምግልናም ሞተ ሸመገለ፥ ብዙ ዘመንም ጠገበ ወደ ወገኖቹም ተከማቸ። |
ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ሊያጽናኑት ወደ እርሱ መጡ፤ እርሱ ግን “ለልጄ እያለቀስሁ ወደ ሙታን ዓለም እወርዳለሁ” በማለት መጽናናትን እምቢ አለ። ስለዚህ ስለ ልጁ ማዘኑን ቀጠለ።
ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልጆቹን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፤ “እኔ በሞት ወደ ወገኖቼ የምሄድበት ጊዜ ደርሶአል፤ ስለዚህ በሒታዊው በዔፍሮን እርሻ ላይ ባለው ዋሻ ውስጥ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ፤
አስከሬኑን ወደ ከነዓን ወስደው ከመምሬ በስተምሥራቅ በምትገኘው በማክፌላ ዋሻ ቀበሩት፤ ይህም ዋሻ አብርሃም ለመቃብር ቦታ እንዲሆን ከሒታዊው ከዔፍሮን በገዛው እርሻ ውስጥ የሚገኝ ነው።
ጌታ ሆይ! አንተ በእነርሱ ላይ ያለህ ቊጣ በእኔም ውስጥ ይነዳል። ከቶም ልታገሠው አልችልም።” እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ “ቊጣዬን በመንገድ ላይ በሚገኙ ሕፃናትና በተሰበሰቡ ወጣቶች ላይ አፍስሰው፤ ባልና ሚስት በአንድነት ይወሰዳሉ፤ በዕድሜ ለገፉ ሽማግሌዎች እንኳ ምሕረት አይደረግላቸውም።”
“አሮን ለእስራኤላውያን ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር አይገባም፤ እናንተ ሁለታችሁ በመሪባ ውሃ ዘንድ በትእዛዜ ላይ ስላመፃችሁ አሮን ይሞታል።
ነገር ግን ዳዊት በሕይወቱ ዘመን አገልግሎቱን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከፈጸመ በኋላ ሞቶአል፤ ከአባቶቹም ጋር ተቀብሮአል፤ መበስበስም ደርሶበታል።
የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ በአባቱም በኢዮአስ መቃብር ተቀበረ፤ ይህም መቃብር የአቢዔዜር ጐሣ ከተማ በነበረችው በዖፍራ ይገኛል።