አብርሃምም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ ‘እዚህ ቦታ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው የለም’ ብዬ በማሰብ ‘ሚስቴን ለመውሰድ በመፈለግ ይገድሉኛል’ ብዬ ስለ ሰጋሁ ነው፤
ዘፍጥረት 22:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልአኩም “ልጁን አትንካ፤ ምንም ዐይነት ጒዳት አታድርስበት፤ አንድ ልጅህን እንኳ ለእኔ ከመስጠት ስለ አልተቈጠብክ እነሆ፥ እኔን እግዚአብሔርን የምትፈራ መሆንህን ተረድቼአለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “እጅህን በብላቴናው ላይ አታሳርፍ፤ ምንም ጕዳት አታድርስበት፤ እነሆ፤ እግዚአብሔርን እንደምትፈራ ተረድቻለሁ፤ ልጅህን፣ ያውም አንዱን ልጅህን ለእኔ ለመስጠት አልሣሣህምና” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም “በልጁ ላይ እጅህን አትዘርጋ፤ ምንም ዓይነት ጉዳት አታድርስበት፤ አንድ ልጅህን እንኳ ለእኔ ለመስጠት እንዳልሳሳህ እነሆ አየሁ፥ እኔን እግዚአብሔርን የምትፈራ እንደሆንህ አሁን አውቄአለሁ” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “በብላቴናው ላይ እጅህን አትዘርጋ፤ አንዳችም አታድርግበት፤ ለምትውድደው ልጅህ ከእኔ አልራራህለትምና አንተ እግዚአብሔርን የምትፈራ እንደሆንህ አሁን ዐውቄአለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ፦ እነሆኝ አለ። እርሱም፦ በብላቴናው ላይ እጅህን አትዘርጋ አንዳችም አታድርግበት፤ አንድ ልጅህን ለእኔ አልከለከልህምን እግዚአብሔር የምትፈራ እንደ ሆንህ አሁን አውቄአለሁ አለ። |
አብርሃምም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ ‘እዚህ ቦታ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው የለም’ ብዬ በማሰብ ‘ሚስቴን ለመውሰድ በመፈለግ ይገድሉኛል’ ብዬ ስለ ሰጋሁ ነው፤
አብርሃም ዙሪያውን በተመለከተ ጊዜ ቀንዶቹ በቊጥቋጦ ዛፍ የተያዙ አንድ በግ አየ፤ ሄዶ በጉን አመጣና በልጁ ፋንታ መሥዋዕት አድርጎ አቀረበው።
እግዚአብሔርም “የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፤ እዚያ በማሳይህ አንድ ኮረብታ ላይ እርሱን መሥዋዕት አድርገህ አቅርብልኝ” አለው።
ከእኔ በፊት የሕዝብ ገዢ ሆኖ የተሾመው ሁሉ በሕዝቡ ላይ ከባድ ሸክም በመሆን፥ በየቀኑ ለምግብና ለመጠጥ የሚሆን አርባ ብር ያስከፍላቸው ነበር፤ የገዢዎቹም አገልጋዮች እንኳ በሕዝቡ ላይ ሠልጥነውባቸው ይጨቊኑአቸው ነበር፤ እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለምፈራ እንደዚያ አላደረግሁም።
ዑፅ ተብላ በምትጠራ አገር ኢዮብ የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም ከክፉ ነገር ሁሉ ርቆ እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ምንም ነውር የሌለበት፥ ቅን ሰው ነበር።
እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው፤ ትእዛዙን የሚፈጽሙትን ሁሉ አስተዋዮች ያደርጋቸዋል፤ እግዚአብሔር ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን!
ሙሴም “አይዞአችሁ፥ አትፍሩ፤ እግዚአብሔር በዚህ ሁኔታ ወደ እናንተ የመጣው ሊፈትናችሁና እርሱን በመፍራት ኃጢአት ከመሥራት ርቃችሁ እንድትኖሩ ነው” ሲል መለሰላቸው።
ልጆቻቸውንም መሥዋዕት አድርገው በእሳት ለማቃጠል ለባዓል መሠዊያዎችን ሠርተዋል፤ ይህን እንዲያደርጉ አላዘዝኳቸውም፤ ከቶም ስለዚህ ነገር አላሰብኩም።
ከእነርሱ ጋር የዘለዓለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ ለእነርሱ መልካም ነገር ከማድረግም አላቋርጥም፤ በእውነት እንዲፈሩኝ አደርጋለሁ። ከዚያም በኋላ ፊታቸውን ከእኔ ወደ ሌላ አይመልሱም።
ስለ እኔ ብሎ ቤቶችን፥ ወይም ወንድሞችን፥ ወይም እኅቶችን፥ ወይም አባትን ወይም እናትን፥ ወይም ልጆችን፥ ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል፤ የዘለዓለም ሕይወትንም ያገኛል።
በይሁዳ፥ በገሊላና በሰማርያ ሁሉ ያለችው ቤተ ክርስቲያን ሰላም አገኘች፤ በረታችም፤ ጌታን እያከበረችና በመንፈስ ቅዱስ እየተጽናናች በቊጥር አደገች።
ነገር ግን እኛ ኃጢአተኞች ሆነን ሳለ ክርስቶስ በእኛ ምትክ ሞቶአል፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር ምን ያኽል ታላቅ መሆኑን ያስረዳል።
በሰው ከሚደርሰው ፈተና በቀር ሌላ ፈተና አልደረሰባችሁም፤ እግዚአብሔር ታማኝ ነው፤ ከአቅማችሁ በላይ የሆነ ፈተና እንዲደርስባችሁ አይፈቅድም፤ በምትፈተኑበትም ጊዜ የምትታገሡበትን ኀይል በመስጠት ከፈተናው የምትወጡበትን መንገድ ያዘጋጅላችኋል።
ነገር ግን “አንተ እምነት አለህ፤ እኔም መልካም ሥራ አለኝ” የሚል ቢኖር፥ “እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፤ እኔም በሥራዬ እምነቴን አሳይሃለሁ” እለዋለሁ።
ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር የሚወደው የቱን ይመስልሃል? መታዘዝን ወይስ ቊርባንና መሥዋዕት ማቅረብን? ለእርሱ መታዘዝ ምርጥ የበግ መሥዋዕት ከማቅረብ ይበልጣል፤