Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 8:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ለመስጠት መልካም ፈቃድ ካለ የሰው ልግሥና ተቀባይነት የሚያገኘው ባለው መጠን ሲሰጥ እንጂ በሌለው መጠን ሲሰጥ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ለመስጠት በጎ ፈቃድ ካለን ስጦታው ተቀባይነት የሚያገኘው ባለን መጠን ስንሰጥ እንጂ፣ በሌለን መጠን ለመስጠት ስንሞክር አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በጎ ፈቃድ ቢኖር፥ ባለው ባለው መጠን ተቀባይነት ይኖረዋል እንጂ የሌላውን አይጠበቅበትም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ፈቃድ ካለም፥ ሰው በሚ​ቻ​ለው መጠን ቢሰጥ ይመ​ሰ​ገ​ናል፤ በማ​ይ​ቻ​ለ​ውም መጠን አይ​ደ​ለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በጎ ፈቃድ ቢኖር፥ እንዳለው መጠን የተወደደ ይሆናል እንጂ እንደሌለው መጠን አይደለም።

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 8:12
21 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ግን ‘ለእኔ ቤተ መቅደስን ለመሥራት በመፈለግህ መልካም አድርገሃል፤


“ስጦታን ያመጡልኝ ዘንድ ለእስራኤላውያን ንገር፤ ማንኛውም ሰው በፈቃዱ የሚያመጣውን መባ ሁሉ ተቀበል።


ብር ወይም ነሐስ ለማቅረብ ችሎታ ያላቸውም ሁሉ ስጦታቸውን ለእግዚአብሔር አመጡ፤ ለማንኛውም አገልግሎት የሚውል የግራር እንጨት ያለውም አመጣ።


ወንዶችና ሴቶች የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እግዚአብሔር ሙሴን ላዘዘው ሥራ የሚውል ልባቸው የፈቀደውን ስጦታ ለእግዚአብሔር አመጡ።


ለእግዚአብሔር መባ አቅርቡ፤ መባ ለማቅረብ የፈለገ ሁሉ እያንዳንዱ ልቡ የፈቀደውን ያኽል የወርቅ፥ የብር፥ ወይም የነሐስ


ከሰው የሚፈለገው ታማኝነት ነው፤ ሐሰተኛ ከመሆን ይልቅ ድኻ መሆን ይሻላል።


ሁለት መክሊት የተቀበለውም እንዲሁ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፈ።


ሁለት መክሊት የተቀበለው ቀርቦ ‘ጌታ ሆይ! ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ ሌላ ሁለት መክሊት አትርፌአለሁ!’ አለ።


በትንሽ ነገር የታመነ ሰው በትልቅ ነገርም የታመነ ይሆናል፤ በትንሽ ነገር የማይታመን ሰው ግን በትልቅ ነገርም አይታመንም።


ስለዚህ የመስጠት ፈቃደኛነታችሁ አሳብ በሥራ ላይ ውሎ ወደ ፍጻሜ እንዲደርስ ባላችሁ መጠን ያንን ያሰባችሁትን አሁን አድርጉ።


ይህንንም ስል ሁላችሁም እኩል እንድትሆኑ እንጂ እናንተ በመስጠት ስትቸገሩ ሌሎች እንዲያርፉ ብዬ አይደለም።


ከዚህም በላይ ይህ ወንድም እኛ ይህን በጎ ሥራ ለጌታ ክብር ስንፈጽምና ለማገልገል ያለንንም መልካም ፈቃድ ስንገልጥ አብሮን በመሄድ የሥራ ተካፋያችን እንዲሆን በአብያተ ክርስቲያን የተመረጠ ነው።


ስለዚህ እግዚአብሔር የሚወደው በደስታ የሚሰጠውን ሰው ስለ ሆነ እያንዳንዱ ለመስጠት የፈለገውን በልቡ ፈቅዶ በደስታ ይስጥ እንጂ እያመነታ ወይም በግዴታ አይስጥ።


የተለያዩትን የእግዚአብሔርን የጸጋ ስጦታዎች በታማኝነት በማስተዳደር ከእናንተ እያንዳንዱ በተሰጠው የጸጋ ስጦታ ሌላውን ያገልግል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos