ዘዳግም 28:49 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ቋንቋቸውን የማታውቀውን የሕዝቦች ሠራዊትን ከሩቅ ምድር ያመጣብሃል፤ እነርሱም እንደ ንስር በአንተ ላይ ይወርዱብሃል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንደ ንስር ፈጥኖ የሚወርድንና ቋንቋውን የማታውቀውን ሕዝብ እጅግ ሩቅ ከሆነ፣ ከምድርም ዳርቻ ያስነሣብሃል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንደ ንስር ፈጥኖ የሚወርድንና ቋንቋው የማታውቀውን ሕዝብ እጅግ ሩቅ ከሆነ፥ ከምድርም ዳርቻ ያስነሣብሃል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ንስር እንደሚበርር ከሩቅ ሀገር፥ ከምድር ዳር ቋንቋቸውን የማትሰማውን ሕዝብ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ቍንቍቸውን የማታውቀውን፥ ፊታቸው የደነደነውን፥ ሽማግሌውንም የማያፍሩትን፥ ሕፃኑንም የማይምሩትን ሕዝብ ንስር እንደሚበርር ከሩቅ አገር ከምድር ዳር ያመጣብሃል። |
በዚያም ጊዜ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ሄዶ “እነዚህ ሰዎች ከወዴት መጡ? ምንስ ነገሩህ?” ብሎ ጠየቀው። ሕዝቅያስም “እነርሱ የመጡት ባቢሎን ከሚባል ከሩቅ አገር ነው” ሲል መለሰለት።
“ያም ዘመን በደረሰ ጊዜ ከዓባይ ወንዝ ዳርቻ ርቀት ግብጻውያን እንደ ዝንብ መንጋ፥ አሦራውያንም ከአገራቸው እንደ ንብ ሠራዊት እየተመሙ ይመጡ ዘንድ እግዚአብሔር ምልክት ይሰጣቸዋል።
“እነሆ የጠላት ሠራዊት እንደ ደመና አንዣቦአል፤ የጦር ሠረገሎቹ እንደ ዐውሎ ነፋስ ፈጣኖች ናቸው፤ ፈረሶቹም ከንስር ይበልጥ ይበራሉ፤ ለእኛ ወዮልን! ጠፍተናል!
ጠላት በቦጽራ ላይ ክንፉን በስፋት ዘርግቶ ወደ ታች እንደሚወርድ ንስር በመሆን ጉብ ይልባታል፤ በዚያን ጊዜ የኤዶም ወታደሮች በምጥ ተይዛ በፍርሃት እንደምትጨነቅ ወላድ ሴት ይሆናሉ።
“የምሳሌውን ትርጒም ያውቁ እንደ ሆነ እስቲ እነዚህን ዐመፀኞች ጠይቃቸው፤ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ንጉሡንና መሳፍንቱን ወደ ባቢሎን የወሰዳቸው መሆኑን ንገራቸው፤
እኔ ልዑል እግዚአብሔር ለእነርሱ የምለውን ያውቁ ዘንድ ይህን ንገራቸው፤ የተዋቡ ላባዎችና ታላላቅ ክንፎች ያሉት አንድ ግዙፍ ንስር ነበረ፤ ይህም ንስር ወደ ሊባኖስ ተራራዎች በረረ፤ በአንድ የሊባኖስ ዛፍ ላይ አርፎም ጫፉን በመቊረጥ የንግድ ሥራ ወደ ተስፋፋበት ወደ አንድ አገር አምጥቶም ነጋዴዎች በበዙባት ከተማ አኖረው።
ንግግራቸው ግራ የሚያጋባ፥ ቋንቋቸው ወደማይታወቅና የቃላቸውን ትርጒም ልታስተውለው ወደማትችል ታላላቅ ሕዝቦች ልኬህ ቢሆን ኖሮማ በሰሙህ ነበር።
የመጀመሪያው አውሬ አንበሳ ይመስል ነበር፤ እርሱም እንደ ንስር ያሉ ክንፎች ነበሩት፤ እኔም እየተመለከትኩት ክንፎቹ ተነቃቀሉ፤ አውሬውም ቀና ብሎ እንደ ሰው በሁለት እግሮቹ ቆመ፤ ሰብአዊ አእምሮም ተሰጠው።
ከስድሳ ሁለት ሳምንት በኋላ መሲሑ ያለ ፍትሕ ይገደላል፤ የሚገደለውም ለራሱ አይደለም፤ የሚመጣው መሪ ወታደሮች ቤተ መቅደሱንና ከተማይቱን ይደመስሳሉ፤ መጨረሻውም እንደ ጐርፍ ይመጣል፤ ውድመት ስለ ታወጀ ጦርነት እስከ መጨረሻ ይቀጥላል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ቃል ኪዳኔን ስላፈረሱና ሕጌን ስለ ተላለፉ በቤቴ ላይ ጠላት እንደ ጆፌ አሞራ ያንዣበበ ስለ ሆነ የማስጠንቀቂያ መለከት ንፉ!”
ይህም፦ “ ‘በተለያዩ ቋንቋዎች በሚናገሩ ሰዎችና በባዕድ ሰዎች አፍ ለዚህ ሕዝብ እናገራለሁ፤ ይህም ሆኖ አይሰሙኝም’ ይላል ጌታ እግዚአብሔር” ተብሎ በሕግ ተጽፎአል።