“ከሞት ጋር ስምምነት አድርገናል፤ ከሙታንም ዓለም ጋር ቃል ኪዳን ገብተናል” እያላችሁ ትመካላችሁ፤ እንዲሁም “ማታለልን እንደ መጠለያ፥ ሐሰትንም እንደ መጠጊያ አምባ ስላደረግን መቅሠፍት በሚመጣበት ጊዜ ሳይነካን ያልፋል” ብላችሁ ተስፋ ታደርጋላችሁ።
ዳንኤል 9:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያም መሪ ለአንድ ሳምንት ከብዙ ሕዝቦች ጋር የጠበቀ ቃል ኪዳን ያደርጋል፤ በሳምንቱም እኩሌታ መሥዋዕቱንና ቊርባኑን ያስቀራል፤ በእነርሱም ፈንታ ጥፋት የሚያስከትለው ርኲሰት እንዲተካ ያደርጋል። ይህም የሚሆነው በዚያ አጥፊ መሪ ላይ የታወጀው ቅጣት እስኪፈጸም ድረስ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አለቃው ከብዙዎች ጋራ ለአንድ ሱባዔ ቃል ኪዳኑን ያጸናል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕትና ቍርባን ማቅረብን ያስቀራል። የታወጀው ፍርድ በርሱ ላይ እስኪፈስስ ድረስ፣ ጥፋትን የሚያመጣ የጥፋት ርኩሰት በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያቆማል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፥ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፥ በርኵሰትም ጫፍ ላይ አጥፊው ይመጣል፥ እስከ ተቈረጠውም ፍጻሜ ድረስ መቅሠፍት በአጥፊው ላይ ይፈስሳል። |
“ከሞት ጋር ስምምነት አድርገናል፤ ከሙታንም ዓለም ጋር ቃል ኪዳን ገብተናል” እያላችሁ ትመካላችሁ፤ እንዲሁም “ማታለልን እንደ መጠለያ፥ ሐሰትንም እንደ መጠጊያ አምባ ስላደረግን መቅሠፍት በሚመጣበት ጊዜ ሳይነካን ያልፋል” ብላችሁ ተስፋ ታደርጋላችሁ።
“ጆሮአችሁን አዘንብላችሁ ወደ እኔ ቅረቡ፤ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ቃሌን አድምጡ፤ ዳዊትን እንደ ወደድኩት እናንተን በታማኝነት ለመውደድ ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን እገባለሁ።
ሠራዊቱም ቤተ መቅደሱንና አካባቢውን ያረክሳሉ፤ የዘወትር መሥዋዕትም እንዳይቀርብ ያደርጋሉ፤ አጸያፊ የሆነ ርኩስ ነገር በማቆም ጥፋትን ያመጣሉ።
“የሶርያ ንጉሥ የፈለገውን ሁሉ ይፈጽማል፤ ራሱንም ከአማልክት ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ከአማልክት ሁሉ በላይ ባለው አምላክ ላይ ከዚህ በፊት ተሰምቶ የማይታወቅ የስድብ ቃል ይናገራል፤ የታቀደው ሁሉ መደረግ ስላለበት የእግዚአብሔር የቊጣው ቀን እስኪደርስ ድረስ ይሳካለታል።
በልዑል እግዚአብሔር ላይ በመታበይ ይናገራል፤ የልዑል እግዚአብሔርንም ቅዱሳን ያስጨንቃል፤ የተቀደሱ በዓላትንና ሕጉን ለመለወጥ ያቅዳል፤ ቅዱሳኑም ለሦስት ዓመት ተኩል በእርሱ ሥልጣን ሥር ይሆናሉ።
ከዚያ በኋላ አንድ ቅዱስ ሲናገር ሰማሁ፤ ሌላው ቅዱስ ደግሞ ለተናገረው ቅዱስ እንዲህ አለው፦ “እነዚህ በራእዩ የታዩት ነገሮች የሚፈጸሙበት ጊዜ መቼ ነው? ጥፋትን የሚያስከትለው ዐመፅና የዘወትርን መሥዋዕት ተክቶ የሚቈየው እስከ መቼ ነው? ቤተ መቅደሱና የሰማይ ሠራዊት ተላልፈው በመሰጠት ተረግጠው የሚቈዩትስ እስከ መቼ ነው?”
በዚሁ ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ ያለ ንጉሥ ወይም ያለ መሪ፥ ያለ መሥዋዕት ወይም ያለ ሐውልት፥ ያለ ልብሰ ተክህኖ ወይም የጣዖት ምስል ለብዙ ዘመን ይኖራሉ፤
“ደግሞ መገኘት በማይገባው ስፍራ የሚያረክሰውን አጸያፊ ነገር ታያላችሁ፤ ይህንንም አንባቢው ያስተውል፤ በዚያን ጊዜ በይሁዳ ምድር ያሉ ወደ ተራራዎች ይሽሹ።
ከእነርሱም ብዙዎች በሰይፍ ይገደላሉ፤ ሌሎችም ተማርከው ወደየአገሩ ይወሰዳሉ። የአሕዛብ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።”
እንግዲህ በዚህ ዐይነት እስራኤላውያን ሁሉ ይድናሉ። ስለዚህም እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፦ “አዳኝ ከጽዮን ይመጣል፤ ከያዕቆብም ዘር ሁሉ ክፋትን ያስወግዳል፤
ነገር ግን የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታው እንደ ሰው ኃጢአት አይደለም፤ በአንድ ሰው ኃጢአት ምክንያት ብዙዎች እንደ ሞቱ እንዲሁም በእግዚአብሔር ጸጋና በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት የተገኘው የጸጋ ስጦታ ለብዙዎች ተትረፍርፎ ተሰጥቶአል።
እንዲሁም ክርስቶስ የብዙዎችን ኃጢአት ለማስወገድ አንድ ጊዜ ተሠውቶአል፤ ደግሞም ኃጢአትን ለመሸከም ሳይሆን እርሱን የሚጠባበቁትን ለማዳን ሁለተኛ ጊዜ ይገለጣል።