Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዳንኤል 12:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 “የዘወትሩ መሥዋዕት ተቋርጦ አጸያፊ የሆነው የጥፋት ርኲሰት እንዲቆም ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ቀኖች ያልፋሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 “የዘወትሩ መሥዋዕት ከተቋረጠበትና ጥፋትን የሚያመጣው የጥፋት ርኩሰት ከተተከለበት ጊዜ ጀምሮ አንድ ሺሕ ሁለት መቶ ዘጠና ቀን ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የዘወትሩም መሥዋዕት ከቀረ ጀምሮ፥ የጥፋትም ርኵሰት ከቆመ ጀምሮ ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ቀን ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 12:11
14 Referencias Cruzadas  

“በሚመጡት ዘመናት ሁሉ በየዕለቱ አንድ ዓመት የሆናቸው ሁለት ጠቦቶች መሥዋዕት አድርገህ በመሠዊያው ላይ ታቀርባለህ፤


ያንንም ከፈጸምክ በኋላ ተዛውረህ በቀኝ ጐንህ በመተኛት እንደገና የይሁዳን በደል አርባ ቀን ትሸከማለህ፤ ይህም እነርሱን በምቀጣበት በእያንዳንዱ ዓመት ልክ ይሆናል ማለት ነው።


“አትክልት እየተመገብንና ውሃ እየጠጣን እንድንቈይ በማድረግ እኛን አገልጋዮችህን ለዐሥር ቀን ያኽል ፈትነን፤


ሠራዊቱም ቤተ መቅደሱንና አካባቢውን ያረክሳሉ፤ የዘወትር መሥዋዕትም እንዳይቀርብ ያደርጋሉ፤ አጸያፊ የሆነ ርኩስ ነገር በማቆም ጥፋትን ያመጣሉ።


በልዑል እግዚአብሔር ላይ በመታበይ ይናገራል፤ የልዑል እግዚአብሔርንም ቅዱሳን ያስጨንቃል፤ የተቀደሱ በዓላትንና ሕጉን ለመለወጥ ያቅዳል፤ ቅዱሳኑም ለሦስት ዓመት ተኩል በእርሱ ሥልጣን ሥር ይሆናሉ።


ስለ ጠዋትና ስለ ማታ መሥዋዕት የተነገረው ራእይ እውነት ነው፤ አንተ ግን ይህ ራእይ የሚፈጸምበት ጊዜ ሩቅ ስለ ሆነ በምሥጢር ያዘው” አለኝ።


ያም መሪ ለአንድ ሳምንት ከብዙ ሕዝቦች ጋር የጠበቀ ቃል ኪዳን ያደርጋል፤ በሳምንቱም እኩሌታ መሥዋዕቱንና ቊርባኑን ያስቀራል፤ በእነርሱም ፈንታ ጥፋት የሚያስከትለው ርኲሰት እንዲተካ ያደርጋል። ይህም የሚሆነው በዚያ አጥፊ መሪ ላይ የታወጀው ቅጣት እስኪፈጸም ድረስ ነው።”


በዚሁ ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ ያለ ንጉሥ ወይም ያለ መሪ፥ ያለ መሥዋዕት ወይም ያለ ሐውልት፥ ያለ ልብሰ ተክህኖ ወይም የጣዖት ምስል ለብዙ ዘመን ይኖራሉ፤


“ነቢዩ ዳንኤል በተናገረው መሠረት የሚያረክሰውን አጸያፊ ነገር በተቀደሰ ስፍራ ቆሞ ባያችሁ ጊዜ አንባቢው ያስተውል!


“ደግሞ መገኘት በማይገባው ስፍራ የሚያረክሰውን አጸያፊ ነገር ታያላችሁ፤ ይህንንም አንባቢው ያስተውል፤ በዚያን ጊዜ በይሁዳ ምድር ያሉ ወደ ተራራዎች ይሽሹ።


ከቤተ መቅደሱ ውጪ ያለውን ክፍት ቦታ ግን ተወው፤ እርሱ ለአሕዛብ የተሰጠ ስለ ሆነ አትለካው፤ አሕዛብ ቅድስቲቱን ከተማ ለአርባ ሁለት ወር ይረግጡአታል፤


ሴቲቱም ወደ በረሓ ሸሽታ ሄደች፤ እዚያ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሥልሳ ቀን በእንክብካቤ ተይዛ የምትጠበቅበትን ስፍራ እግዚአብሔር አዘጋጅቶላት ነበር።


የትዕቢትና የስድብ ቃል የሚናገርበት አፍ ለአውሬው ተሰጠው፤ አርባ ሁለት ወር በሥልጣን እንዲሠራም ተፈቀደለት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos