ንጉሡ ስለ መላው የእስራኤል ሕዝብ የሚቃጠል መሥዋዕትና ለኃጢአት ስርየት የሚሆን መሥዋዕት እንዲቀርብ አዞ ስለ ነበር፥ ካህናቱ በትእዛዙ መሠረት ፍየሎቹን ዐርደው ደማቸውን መሥዋዕት በማድረግ በመሠዊያው ላይ አፈሰሱ።
ዳንኤል 9:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰባት ጊዜ ሰባ ሳምንት የተባለው እግዚአብሔር ሕዝብህንና የተቀደሰ ከተማህን ከኃጢአትና ከክፋት ነጻ ለማውጣት ውሳኔ ያደረገበት ጊዜ ነው፤ በዚያን ጊዜ በደል ይሰረያል፤ ዘለዓለማዊ ፍትሕ ይሰፍናል፤ ራእይና ትንቢት ይፈጸማል፤ ቤተ መቅደሱም ይታደሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዐመፃን ለማስቆም፣ ኀጢአትን ለማስወገድ፣ በደልን ለማስተስረይ፣ ዘላለማዊ ጽድቅን ለማምጣት፣ ራእይንና ትንቢትን ለማተምና፣ እጅግ ቅዱስ የሆነውን ለመቀባት ስለ ሕዝብህና ስለ ተቀደሰችው ከተማህ ሰባ ሱባዔ ታውጇል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓመፃን ይጨርስ፥ ኃጢአትንም ይፈጽም፥ በደልንም ያስተሰርይ፥ የዘላለምን ጽድቅ ያግባ፥ ራእይንና ትንቢትን ያትም፥ ቅዱሰ ቅዱሳኑንም ይቀባ ዘንድ በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል። |
ንጉሡ ስለ መላው የእስራኤል ሕዝብ የሚቃጠል መሥዋዕትና ለኃጢአት ስርየት የሚሆን መሥዋዕት እንዲቀርብ አዞ ስለ ነበር፥ ካህናቱ በትእዛዙ መሠረት ፍየሎቹን ዐርደው ደማቸውን መሥዋዕት በማድረግ በመሠዊያው ላይ አፈሰሱ።
አንተ መልካሙን ነገር ትወዳለህ፤ ክፉውን ነገር ትጠላለህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ መረጠህ፤ ከሌሎች ነገሥታትም ይበልጥ የደስታን ዘይት ቀባህ።
በምድር ላይ ፍትሕን እስኪመሠርት ድረስ እርሱ አይታክትም፤ ተስፋም አይቈርጥም፤ በሩቅ ያሉ ሕዝቦችም የእርሱን ትምህርት ለመስማት ይናፍቃሉ።”
ቀና ብላችሁ ወደ ሰማያት ወደ ታችም ወደ ምድር ተመልከቱ፤ ሰማያት እንደ ጢስ በነው ይጠፋሉ፤ ምድርም እንደ ልብስ ታረጃለች፤ በእርስዋ የሚኖሩ ሁሉ እንደ ዝንብ ይሞታሉ፤ የእኔ ማዳን ግን ዘለዓለማዊ ነው፤ ለታዳጊነቴም ፍጻሜ የለውም።
እነርሱ ብል እንደ በላው ልብስና ትል እንደበላው ሱፍ ይሆናሉ፤ የእኔ ታዳጊነት ግን ዘለዓለማዊ ነው፤ አዳኝነቴም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል።”
እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “የማድንበት ጊዜ ፈጥኖ ስለሚመጣና እኔ የምታደግበትም ጊዜ ስለ ቀረበ ፍትሕን ጠብቁ ትክክለኛውንም ነገር አድርጉ።
ለተጨቈኑት መልካም ዜናን አበሥር ዘንድ፥ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩት ነጻነትን፥ ለታሰሩት መፈታትን ለማወጅ እግዚአብሔር ቀብቶ ስለ ላከኝ፥ የጌታ እግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው።
የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! የበደላችሁ ቅጣት አብቅቶአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ በስደት እንድትኖሩ አያደርጋችሁም፤ ነገር ግን የኤዶም ሕዝብ ሆይ! የእናንተን በደል ይቀጣል፤ ኃጢአታችሁንም ያጋልጣል።
“የሰው ልጅ ሆይ! የጢሮስ ንጉሥ ስለሚገጥመው መጥፎ ዕድል ሙሾ አውጣ፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለውንም እንዲህ ብለህ ንገረው፦ ‘በጥበብ የተሞላህና እጅግ መልከ ቀና በመሆንህ የፍጹምነት ምሳሌ ነበርክ።
እስራኤላውያን ኃጢአት በሠሩባቸው ዓመቶች ብዛት ቀኖችን መድቤልሃለሁ፤ ይህም አንድ ቀን ለአንድ ዓመት ማለት ነው፤ ስለዚህ ለሦስት መቶ ዘጠና ቀኖች የእስራኤላውያንን ኃጢአት ትሸከማለህ።
ያንንም ከፈጸምክ በኋላ ተዛውረህ በቀኝ ጐንህ በመተኛት እንደገና የይሁዳን በደል አርባ ቀን ትሸከማለህ፤ ይህም እነርሱን በምቀጣበት በእያንዳንዱ ዓመት ልክ ይሆናል ማለት ነው።
ሙሴም ዐረደው፤ ከደሙም ጥቂት በጣቱ ነክሮ የመሠዊያውን አራት ማእዘን ጒጦች በመቀባት አንጽቶ ቀደሰው፤ ከዚያም የተረፈውን ደም በመሠዊያው ሥር አፈሰሰው፤ በዚህም ዐይነት መሠዊያውን ለእግዚአብሔር በመለየት አነጻው፤
በኃጢአታችሁ ምክንያት አርባ ዓመት ሙሉ ትሠቃያላችሁ፤ ይህም ምድሪቱን ለማጥናት በቈያችሁበት አርባ ቀን ልክ አንዲቱ ዕለት አንድ ዓመት ትሆንባችኋለች፤ በዚያን ጊዜ እኔን መቃወም ምን እንደሚያመጣባችሁ ትገነዘባላችሁ።
“የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፥ አንተ ከእኛ ጋር ምን ጉዳይ አለህ? ልታጠፋን መጣህን? አንተ ማን እንደ ሆንክ እኔ ዐውቃለሁ፤ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱስ ነህ።”
መልአኩም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑል እግዚአብሔርም ኀይል በአንቺ ላይ ይሆናል፤ ስለዚህ ከአንቺ የሚወለደው ሕፃን ቅዱስ ነው፤ የእግዚአብሔርም ልጅ ይባላል።
ሙሴም እንዲህ ብሎአል፦ ‘ጌታ አምላክህ እኔን እንዳስነሣኝ እንዲሁ ከወንድሞቻችሁ መካከል ነቢይ ያስነሣላችኋል፤ እርሱ የሚነግራችሁን ሁሉ ስሙ፤
እኛ የእግዚአብሔር ጠላቶች ሆነን ሳለ በልጁ ሞት ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀናል፤ አሁን ከእግዚአብሔር ጋር ከታረቅን በኋላ በልጁ ሕይወት አማካይነት ይበልጡን እንድናለን።
እናንተን ግን እግዚአብሔር ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ አደረገ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ጥበባችን፥ ጽድቃችን፥ ቅድስናችንና ቤዛችን እንዲሆን አደረገው።
ይህንንም የማደርግበት ምክንያት በሕግ ላይ የተመሠረተውን የራሴን ጽድቅ ትቼ በእምነት ላይ የተመሠረተውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ በክርስቶስ በማመን ለማግኘትና ከእርሱም ጋር ለመሆን ነው።
በእርሱም አማካይነት በሰማይም ሆነ በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ ከራሱ ጋር አስታረቀ፤ በመስቀል ላይ በፈሰሰው በልጁ ደምም ሰላምን አደረገ።
ስለዚህ በሁሉም ነገር እንደ ወንድሞቹ መሆን ነበረበት፤ በዚህ ዐይነት የሰዎችን ኃጢአት ለመደምሰስ ብሎ እግዚአብሔርን ለማገልገል ታማኝና መሐሪ የካህናት አለቃ ሆነ።
እንዲህማ ቢሆን ኖሮ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ መቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዘመናት መጨረሻ ኃጢአትን ለማስወገድ ራሱን መሥዋዕት በማድረግ አንዴ በማያዳግም ሁኔታ ተገልጦአል።
የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና ሐዋርያ ከሆነው ከስምዖን ጴጥሮስ፥ ከአምላካችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኘው ጽድቅ አማካይነት እኛ እንዳገኘነው እምነት ያለ የከበረ እምነት ላገኛችሁት፤
ዲያብሎስ ከመጀመሪያው አንሥቶ ኃጢአት ስለሚሠራ ኃጢአትን የሚሠራ ሁሉ የዲያብሎስ ወገን ነው። የእግዚአብሔር ልጅ የተገለጠውም የዲያብሎስን ሥራ ለማፍረስ ነው።
ከዚህ በኋላ በምድር ላይ ለሚኖሩ ሕዝብ፥ ነገድ፥ ልዩ ልዩ ቋንቋዎችን ለሚናገሩና ለተለያዩ ወገኖች ሁሉ ለማብሠር ዘለዓለማዊውን ወንጌል የያዘ ሌላ መልአክ በሰማይ መካከል ሲበር አየሁ።
“ለፊላደልፍያ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ “ይህ፥ ቅዱስና እውነተኛ ከሆነው፥ የዳዊት ቤት ቊልፍ ከያዘው የተነገረ ነው፤ እርሱ የሚከፍተውን ማንም አይዘጋውም፤ እርሱ የሚዘጋውንም ማንም አይከፍተውም።