ዐይንህን በትዕቢት አቅንተህ፥ ድምፅህን ከፍ አድርገህ በመጮኽ የተዳፈርከውና የተሳደብከው ማንን ይመስልሃል? የእስራኤልን ቅዱስ አይደለምን?’
ዳንኤል 8:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰማይ ሠራዊትን አለቃ ሳይቀር ተፎካከረው፤ በየቀኑ ለእርሱ የሚቀርብለትን መሥዋዕት እንዲቀር አደረገ፤ መቅደሱንም አረከሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰማይ ሰራዊት አለቃ ጋራ እስኪተካከል ድረስ ራሱን ከፍ ከፍ አደረገ፤ የልዑሉንም የዘወትር መሥዋዕት ወሰደበት፤ የመቅደሱንም ስፍራ አረከሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስከ ሠራዊትም አለቃ ድረስ ራሱን ታላቅ አደረገ፥ ከእርሱም የተነሣ የዘወትሩ መሥዋዕት ተሻረ፥ የመቅደሱም ስፍራ ፈረሰ። |
ዐይንህን በትዕቢት አቅንተህ፥ ድምፅህን ከፍ አድርገህ በመጮኽ የተዳፈርከውና የተሳደብከው ማንን ይመስልሃል? የእስራኤልን ቅዱስ አይደለምን?’
በእኔ ላይ ስለ መቈጣትህና ስለ ልብህ ትዕቢት ሁሉ ሰምቼአለሁ፤ ስለዚህ አሁን በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህም ልጓም አግብቼ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።”
ከእርሱም ጋር በየማለዳው ሳያስታጒል ሁለት ኪሎ ያኽል የእህል ቊርባንና ለምርጡ ዱቄት መለወሻ እንዲሆን አንድ ሊትር ዘይት ያዘጋጃል። ይህም የዘወትር ሥርዓት ይሆናል።
ሠራዊቱም ቤተ መቅደሱንና አካባቢውን ያረክሳሉ፤ የዘወትር መሥዋዕትም እንዳይቀርብ ያደርጋሉ፤ አጸያፊ የሆነ ርኩስ ነገር በማቆም ጥፋትን ያመጣሉ።
ይልቁንም በሰማይ አምላክ ላይ በመታበይ ራስህን ከፍ ከፍ አደረግህ፤ ከቤተ መቅደሱ ተዘርፈው የመጡትን የወርቅ ዕቃዎች አስመጥተህ አንተና መኳንንቶችህ፥ ሚስቶችህና ቁባቶችህ የወይን ጠጅ መጠጫ አደረጋችኋቸው፤ ከጠጣችሁም በኋላ ማየት ወይም መስማት የማይችሉትንና ምንም ነገር የማያውቁትን ከወርቅ፥ ከብር፥ ከነሐስ፥ ከብረት፥ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን አማልክት አመሰገናችሁ፤ መግደል ወይም ማዳን የሚችለውንና አካሄድህን የሚቈጣጠረውን ሕያው አምላክ ግን አላከበርከውም።
በልዑል እግዚአብሔር ላይ በመታበይ ይናገራል፤ የልዑል እግዚአብሔርንም ቅዱሳን ያስጨንቃል፤ የተቀደሱ በዓላትንና ሕጉን ለመለወጥ ያቅዳል፤ ቅዱሳኑም ለሦስት ዓመት ተኩል በእርሱ ሥልጣን ሥር ይሆናሉ።
በክፋት ምክንያት ሠራዊቱና መደበኛው የሚቃጠል መሥዋዕት ለእርሱ ተሰጠ፤ እርሱም እውነትን ወደ መሬት ጣለ፤ የሚያደርገውም ነገር ሁሉ እየተሳካለት ሄደ።
ይህም ንጉሥ እጅግ ብርቱ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ በራሱ ኀይል አይደለም፤ እጅግ አሠቃቂ የሆነ ጥፋት ይፈጽማል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል፤ በኃያላን ሰዎችና በተቀደሱት ሕዝብ ላይ ጥፋትን ያስከትላል።
እጅግም ተንኰለኛ ስለ ሆነ በማታለል ይበለጽጋል፤ ራሱንም ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ብዙ ሰዎችን ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ ይገድላል፤ የልዑላንን ልዑል እንኳ ይፈታተናል፤ በመጨረሻም እርሱ ራሱ ይጠፋል፤ የሚጠፋውም በሰው ኀይል አይደለም።
ይህን ልብ ብለህ አስተውል፤ ኢየሩሳሌም እንድትታደስ ትእዛዝ ከወጣበት ጊዜ አንሥቶ መሲሕ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ ሰባት ሳምንቶች ያልፋሉ፤ እንዲሁም ለሥልሳ ሁለት ሳምንት በችግር ጊዜ ኢየሩሳሌም፥ መንገዶችዋና የመከላከያ ጒድጓድዋ ይገነባሉ። ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ የመከራ ዘመን ይሆናል።
“ለእኔ የሚቀርበውም በእሳት የሚቃጠል የምግብ ቊርባን የሚከተለው ነው፦ በየቀኑ ለሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት አንድ ዓመት የሞላቸውና ምንም ነውር የሌለባቸው ሁለት የበግ ጠቦቶች ይሁኑ፤
ከእነርሱም ብዙዎች በሰይፍ ይገደላሉ፤ ሌሎችም ተማርከው ወደየአገሩ ይወሰዳሉ። የአሕዛብ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።”
ይህ የዐመፅ ሰው አማልክት ተብለው ከሚመለኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ያደርጋል፤ “እግዚአብሔር ነኝ” እያለም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንኳ ለመቀመጥ ይደፍራል።
ሁሉ ነገር በእርሱና ለእርሱ የተፈጠረው እግዚአብሔር ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ለማምጣት የመዳናቸውን መሪ ኢየሱስን በመከራ ፍጹም እንዲሆን እንዲያደርገው ተገባው።
እነርሱ በበጉ ላይ ጦርነት ይከፍታሉ፤ ነገር ግን በጉ የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ ድል ይነሣቸዋል፤ ከእርሱ ጋር ያሉት የተጠሩ የተመረጡና የታመኑ ናቸው።”