Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዳንኤል 8:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከሰማይ ሰራዊት አለቃ ጋራ እስኪተካከል ድረስ ራሱን ከፍ ከፍ አደረገ፤ የልዑሉንም የዘወትር መሥዋዕት ወሰደበት፤ የመቅደሱንም ስፍራ አረከሰ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የሰማይ ሠራዊትን አለቃ ሳይቀር ተፎካከረው፤ በየቀኑ ለእርሱ የሚቀርብለትን መሥዋዕት እንዲቀር አደረገ፤ መቅደሱንም አረከሰ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እስከ ሠራዊትም አለቃ ድረስ ራሱን ታላቅ አደረገ፥ ከእርሱም የተነሣ የዘወትሩ መሥዋዕት ተሻረ፥ የመቅደሱም ስፍራ ፈረሰ።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 8:11
28 Referencias Cruzadas  

“የዘወትሩ መሥዋዕት ከተቋረጠበትና ጥፋትን የሚያመጣው የጥፋት ርኩሰት ከተተከለበት ጊዜ ጀምሮ አንድ ሺሕ ሁለት መቶ ዘጠና ቀን ይሆናል።


“የጦር ሰራዊቱም ቤተ መቅደሱንና ቅጥሩን ያረክሳሉ፤ የዘወትሩንም መሥዋዕት ያስቀራሉ፤ በዚያም ጥፋትን የሚያመጣውን የጥፋት ርኩሰት ይተክላሉ።


እያጭበረበረ ይበለጽጋል፤ ራሱንም ታላቅ አድርጎ ይቈጥራል። በሰላም ተደላድለን ተቀምጠናል ሲሉ፣ ብዙዎችን ያጠፋል፤ በልዑላን ልዑልም ላይ ይነሣል፤ ይሁን እንጂ እርሱም ይጠፋል፤ ነገር ግን በሰው ኀይል አይደለም።


ከዚህም ጋራ አንድ ስድስተኛ የኢፍ መስፈሪያ ዱቄት መለወሻም የሚሆን የሂን መስፈሪያ ሢሶ ዘይት አድርገህ በየማለዳው የእህል ቍርባን አቅርብ፤ ይህን የእህል ቍርባን ለእግዚአብሔር ማቅረብም የዘላለም ሥርዐት ነው።


እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉ ግን ድል ይነሣቸዋል፤ ምክንያቱም እርሱ የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ነው፤ ከርሱ ጋራ ያሉ የተጠሩት፣ የተመረጡትና የታመኑትም ዐብረው ድል ይነሣሉ።”


የሰደብኸውና ያቃለልኸው ማንን ነው? ድምፅህንስ ከፍ ከፍ ያደረግኸው፣ ዐይንህን በትዕቢት ያነሣኸው በማን ላይ ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ ነው እኮ!


ሁሉ ነገር ለርሱና በርሱ የሚኖር እግዚአብሔር፣ ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ለማምጣት፣ የድነታቸውን መሥራች በመከራ ፍጹም ሊያደርገው የተገባ ነበር።


በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ወደ አሕዛብም ሁሉ በምርኮ ይወሰዳሉ፤ ኢየሩሳሌምም የአሕዛብ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።


ከዐመፅ የተነሣም የቅዱሳን ሰራዊት ከዘወትሩ መሥዋዕት ጋራ ለርሱ ዐልፎ ተሰጠ፤ የሚያደርገው ሁሉ ተከናወነለት፤ እውነትም ወደ ምድር ተጣለች።


በልዑል ላይ የዐመፅ ቃል ይናገራል፤ የልዑልንም ቅዱሳን ያስጨንቃል፤ ለበዓላት የተመደበውን ጊዜና ሕግን ለመለወጥ ይሞክራል፤ ቅዱሳንም ለዘመን፣ ለዘመናት፣ ለዘመን እኩሌታም ለርሱ ዐልፈው ይሰጣሉ።


ይልቁንም በሰማይ አምላክ ላይ በመታበይ፣ ራስህን ከፍ ከፍ አደረግህ፤ የመቅደሱን መጠጫዎች አስመጣህ፤ አንተና መኳንንትህ፣ ሚስቶችህና ቍባቶችህም የወይን ጠጅ ጠጣችሁባቸው፤ ማየት፣ መስማት፣ ማስተዋልም የማይችሉትን የብርና የወርቅ፣ የናስና የብረት፣ የዕንጨትና የድንጋይ አማልክትን አመሰገንህ። ሕይወትህንና መንገድህን ሁሉ በእጁ የያዘውን አምላክ ግን አላከበርህም።


ሞዓብ እግዚአብሔርን አቃልሏልና ይጠፋል፤ መንግሥትነቱም ይቀራል።


“እግዚአብሔርን ንቋልና፣ ሞዓብን በመጠጥ አስክሩት። ሞዓብ በትፋቱ ላይ ይንከባለል፤ ለመዘባበቻም ይሁን።


በእኔ ላይ በቍጣ ስለ ተነሣሣህ፣ እብሪትህም ወደ ጆሮዬ ስለ ደረሰ፣ ስናጋዬን በአፍንጫህ አደርጋለሁ፣ ልጓሜን በአፍህ አስገባለሁ፤ በመጣህበትም መንገድ እንድትመለስ አደርግሃለሁ።’


ደግሞም እንዲህ በላቸው፤ ‘በእሳት ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት መሥዋዕት ይህ ነው፤ አንድ ዓመት የሆናቸውንና እንከን የሌለባቸውን ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶች መደበኛ የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ በየዕለቱ አቅርቡ።


እርሱም አምላክ ከተባለና ከሚመለከው ነገር ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ተቃዋሚ ነው፤ እርሱም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተቀምጦ፣ “እኔ አምላክ ነኝ” እያለ ዐዋጅ ያስነግራል።


እጅግ ብርቱ ይሆናል፤ ነገር ግን በገዛ ኀይሉ አይደለም። አሠቃቂ ጥፋት ይፈጽማል፤ የሚያደርገው ሁሉ ይከናወንለታል፤ ኀያላን ሰዎችንና ቅዱሳኑን ሕዝብ ያጠፋል።


“ይህን ዕወቅ፤ አስተውለውም፤ ኢየሩሳሌምን ለማደስና ለመጠገን ዐዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ፣ ገዥው መሲሕ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ፣ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል። ኢየሩሳሌም ከጐዳናዎቿና ከቅጥሮቿ ጋራ ትታደሳለች፤ ይህ የሚሆነው ግን በመከራ ጊዜ ነው።


ከፊቱ የሚቆመውን ታላቅ ሰራዊት፣ የቃል ኪዳኑንም አለቃ ሳይቀር ይደመስሳል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios