ዳንኤል 12:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጭን ሐር ለብሶ ከወንዝ በላይ በኩል የቆመው መልአክ ሁለት እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ በዘለዓለማዊው አምላክ ስም በመማል “ሦስት ዓመት ተኩል ይወስዳል፤ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ የሚደርሰው መከራ ሲያከትም እነዚህ ሁሉ ነገሮች ተፈጻሚነት ያገኛሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከወንዙ ውሃ በላይ የነበረው በፍታ የለበሰው ሰው፣ ቀኝ እጁንና ግራ እጁን ወደ ሰማይ አንሥቶ፣ “ለዘመን፣ ለዘመናት፣ ለዘመንም እኩሌታ ይሆናል፤ የተቀደሰው ሕዝብ ኀይል መሰበር ሲያከትም፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ይፈጸማሉ” ብሎ ለዘላለም በሚኖረው በርሱ ሲምል ሰማሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከወንዙም ውኃ በላይ የነበረው በፍታም የለበሰው ሰው ቀኝና ግራ እጁን ወደ ሰማይ አንሥቶ፦ ለዘመንና ለዘመናት ለዘመንም እኵሌታ ነው፥ የተቀደሰውም ሕዝብ ኃይል መበተን በተጨረሰ ጊዜ ይህ ሁሉ ይፈጸማል ብሎ ለዘላለም ሕያው ሆኖ በሚኖረው ሲምል ሰማሁ። |
ሕዝቡ “የተቀደሱና እግዚአብሔር የታደጋቸው ወገኖች” ተብለው ይጠራሉ፤ አንቺም ኢየሩሳሌም “የተፈለገችና ያልተተወች ከተማ” ተብለሽ ትጠሪአለሽ።
እንዲህም በላቸው፦ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘እስራኤልን በመረጥኩ ጊዜ ለያዕቆብ ዘር በግብጽ ምድር ራሴን በማሳወቅ ቃል ገባሁላቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ’ አልኳቸው።
“የሶርያም ንጉሥ ወደ አገሩ ተመልሶ ከበፊቱ የበለጠ የጦር ሠራዊት ያደራጃል፤ ከጥቂት ዓመቶችም በኋላ ሠራዊቱን ከተሟላ ትጥቅ ጋር አሰልፎ ይመጣል።
ከእነርሱ አንዱ ቀጭን ሐር ለብሶ ከወንዙ በላይ በኩል የቆመውን መልአክ “ይህ ሁሉ አስደናቂ ነገር ፍጻሜ እስከሚያገኝ ምን ያኽል ጊዜ ይወስዳል?” ብሎ ጠየቀው።
መልአኩ የተናገረውን ሁሉ ሰማሁ፤ ነገር ግን ሊገባኝ አልቻለም፤ ስለዚህ “ጌታዬ ሆይ! የዚህ ሁሉ የመጨረሻው ውጤት ምን ይሆን?” ብዬ ጠየቅሁት።
ንግግሩን ገና ሳይጨርስ እንዲህ የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ፤ “ንጉሥ ናቡከደነፆር ሆይ! የተላለፈብህን ውሳኔ ስማ! እነሆ፥ መንግሥትህ ከአንተ ተወስዳለች፤
ንጉሡ ናቡከደነፆር እንዲህ አለ፦ “ሰባቱ ዓመቶች ካለፉ በኋላ ቀና ብዬ ወደ ሰማይ ተመለከትኩ፤ አእምሮዬም ተመለሰልኝ፤ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገንኩ፤ ለዘለዓለማዊው አምላክ ክብርና ውዳሴ አቀረብኩ፤ “ግዛቱ ዘለዓለማዊ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም፤
በልዑል እግዚአብሔር ላይ በመታበይ ይናገራል፤ የልዑል እግዚአብሔርንም ቅዱሳን ያስጨንቃል፤ የተቀደሱ በዓላትንና ሕጉን ለመለወጥ ያቅዳል፤ ቅዱሳኑም ለሦስት ዓመት ተኩል በእርሱ ሥልጣን ሥር ይሆናሉ።
የተጠየቀውም ቅዱስ “የጠዋትና የማታ መሥዋዕት የማይቀርብባቸው ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ቀኖች ይሆናሉ፤ ከዚያን በኋላ ቤተ መቅደሱ ይነጻል” ብሎ ሲመልስለት ሰማሁ።
ይህም ንጉሥ እጅግ ብርቱ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ በራሱ ኀይል አይደለም፤ እጅግ አሠቃቂ የሆነ ጥፋት ይፈጽማል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል፤ በኃያላን ሰዎችና በተቀደሱት ሕዝብ ላይ ጥፋትን ያስከትላል።
ከእነርሱም ብዙዎች በሰይፍ ይገደላሉ፤ ሌሎችም ተማርከው ወደየአገሩ ይወሰዳሉ። የአሕዛብ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።”
ይህን ብታደርግ ከፈጠራቸው ሕዝቦች ሁሉ በላይ በምስጋና፥ በስም፥ በክብርም ከፍ ሊያደርግህና በሰጠውም ተስፋ መሠረት ለእርሱ የተለየህ ሕዝብ እንደሚያደርግህ ነግሮሃል።”
አንተ እግዚአብሔር አምላክህ የራሱ ወገን አድርጎ የመረጠህ ቅዱስ ሕዝብ ነህ፤ በምድር ላይ ካሉት ሕዝቦች ሁሉ አንተ ለእርሱ የተለየህ ምርጥ ሕዝብ እንድትሆን አድርጎሃል።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚያስደንቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችኹ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።
ሴቲቱ በበረሓ ወደ ተዘጋጀላት ስፍራ በርራ እንድትሄድ የታላቅ ንስር ክንፎች የሚመስሉ ሁለት ክንፎች ተሰጡአት፤ እዚያም ከእባቡ ፊት ርቃ ሦስት ዓመት ተኩል በእንክብካቤ ተይዛ ትጠበቅ ነበር።
ሴቲቱም ወደ በረሓ ሸሽታ ሄደች፤ እዚያ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሥልሳ ቀን በእንክብካቤ ተይዛ የምትጠበቅበትን ስፍራ እግዚአብሔር አዘጋጅቶላት ነበር።
ኻያ አራቱ ሽማግሌዎች ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሚኖረው፥ በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ፊት በግንባራቸው ተደፍተው ይሰግዳሉ፤ አክሊሎቻቸውንም በዙፋኑ ፊት አኑረው፥ እንዲህ ይላሉ፦