ሐዋርያት ሥራ 1:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም፥ በይሁዳ ምድር ሁሉ፥ በሰማርያ፥ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በሚወርድበት ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳና በሰማርያ ሁሉ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ፤” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፥ በሰማርያና እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም ምስክሮች ትሆኑኛላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ” አለ። |
ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩ! የዓለም ሕዝቦች ሁሉ የምስጋና መዝሙር አቅርቡ! በባሕሩ ውስጥ ያሉት ሁሉ፥ የጠረፍ አገሮችና በእነርሱም የሚኖሩ ሁሉ ያመስግኑ!
እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “የያዕቆብን ነገዶች ክብር እንደገና ለማንሣትና የተረፉትን እስራኤላውያን ለመመለስ አገልጋዬ ሆነህ መሥራት ብቻ አይበቃም። ከዚህ የበለጠ ግን አዳኝነቴ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርስ ዘንድ አንተ ለሕዝቦች ሁሉ ብርሃን እንድትሆን አደርግሃለሁ።” ይላል።
በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፤ ከሞት ከተረፉት መካከል ስለ እኔ ወዳልሰሙትና ክብሬንም ወዳላዩት ወደ ተለያዩ ሕዝቦች ወደ ተርሴስ፥ ወደ ሊብያውያን ቀስት ወደሚያስፈነጥሩ ወደ ሊድያውያን፥ ወደ ቱባል፥ ወደ ግሪክ፥ ራቅ ብለው ወደሚገኙት ደሴቶችም እልካቸዋለሁ፤ እነርሱም በሕዝቦች መካከል ክብሬን ይገልጣሉ።
እግዚአብሔር ሆይ! የምትጠብቀኝና ብርታትን የምትሰጠኝ አንተ ነህ፤ በመከራም ጊዜ መጠጊያ አምባዬ ነህ፤ ሕዝቦች ከምድር ዳርቻ ሁሉ ወደ አንተ መጥተው እንዲህ ይላሉ፦ “የቀድሞ አባቶቻችን ከሐሰተኞች አማልክት በቀር ምንም አልነበራቸውም፤ ጣዖቶቻቸው ሁሉ የማይጠቅሙ ከንቱዎች ነበሩ፤
እኔን ግን እግዚአብሔር በመንፈሱና በኀይሉ ሞልቶኛል፤ የእስራኤል ሕዝብ በደላቸውና ኃጢአታቸው ምን እንደ ሆነ አስታውቃቸው ዘንድ በግልጽ ትክክለኛ ፍርድን ለመስጠት ብርታትን ሰጥቶኛል።
ለዘሩባቤል እንዳስታወቀው መልአኩ የነገረኝ የሠራዊት አምላክ ቃል ይህ ነው፤ “ድል የምትነሣው በመንፈሴ እንጂ በኀይልና በብርታት አይደለም።
መልአኩም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑል እግዚአብሔርም ኀይል በአንቺ ላይ ይሆናል፤ ስለዚህ ከአንቺ የሚወለደው ሕፃን ቅዱስ ነው፤ የእግዚአብሔርም ልጅ ይባላል።
እነርሱ ግን “ቀኑ መሽቶአል፤ ፀሐይም መጥለቅዋ ነው፤ ስለዚህ ከእኛ ጋር እዚህ ዕደር” ብለው አጥብቀው ለመኑት፤ በዚህ ምክንያት ከእነርሱ ጋር ሊያድር ወደ ቤት ገባ።
እንዲሁም ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ጌታ ኢየሱስ ወደ ሰማይ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ አብረውን ከነበሩት ከነዚህ ሰዎች አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር እንዲሆን ያስፈልጋል።”
ሳውልም በእስጢፋኖስ መገደል ተስማምቶ ነበር፤ እስጢፋኖስ በሞተበት ቀን በኢየሩሳሌም በምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ተነሣ፤ ከሐዋርያት በቀር አማኞች ሁሉ ወደ ይሁዳና ወደ ሰማርያ ምድር ተበተኑ።
እስቲ ልጠይቅ፤ ታዲያ፥ ቃሉን አልሰሙም ማለት ነውን? በቅዱስ መጽሐፍ፥ “ድምፃቸው በዓለም ሁሉ ተሰማ፤ ቃላቸውም እስከ ምድር ዳርቻ ደረሰ” ተብሎ እንደ ተጻፈው፥ በእርግጥ ሰምተዋል።
እንዲሁም በታላላቅ ተአምራትና በድንቅ ሥራዎች፥ በመንፈስ ቅዱስም ኀይል ከኢየሩሳሌምና ከአካባቢዋ ጀምሮ እስከ እልዋሪቆን ድረስ የክርስቶስን ወንጌል አስተምሬአለሁ።
ይህም የሚሆነው ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በወንጌሉ ከተገኘው ተስፋ ሳትናወጡ በእምነት ጸንታችሁ ስትኖሩ ብቻ ነው፤ ይህም ወንጌል እናንተ የሰማችሁትና በዓለም ላይ ላሉት ሰዎች ሁሉ የተሰበከ ነው፤ እኔ ጳውሎስም አገልጋይ የሆንኩት ለዚሁ ወንጌል ነው።