2 ተሰሎንቄ 2:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! እኛ ግን በእናንተ ምክንያት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ማመስገን ይገባናል፤ የምናመሰግነውም እናንተ በመንፈስ ቅዱስ በመቀደሳችሁና እውነትን በማመናችሁ እንድትድኑ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ስለ መረጣችሁ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፤ እኛ ግን ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ልናመሰግን ይገባናል። ምክንያቱም እግዚአብሔር እናንተን ከመጀመሪያ አንሥቶ በመንፈስ ተቀድሳችሁና በእውነትም አምናችሁ እንድትድኑ መርጧችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! እኛ ግን ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ልናመሰግን ይገባናል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ከመጀመሪያው አንሥቶ በመንፈስ በመቀደስና በእውነት በማመን እንድትድኑ መርጦአችኋልና፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛ ግን በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ልናመሰግን ግድ አለብን፤ እግዚአብሔር በመንፈስ መቀደስ እውነትንም በማመን ለመዳን እንደ በኵራት መርጦአችኋልና፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛ ግን፥ በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ልናመሰግን ግድ አለብን፥ እግዚአብሔር በመንፈስ መቀደስ እውነትንም በማመን ለመዳን እንደ በኵራት መርጦአችኋልና፤ |
በመጨረሻ የሚሆነውን ነገር ከመጀመሪያው ጀምሬ ተናግሬአለሁ፤ ወደፊት ምን እንደሚሆን ከጥንት ጀምሬ ገልጬአለሁ፤ ዓላማዬ የጸና ይሆናል፤ የምፈቅደውንም አደርጋለሁ።
እኔ ለእነርሱ ከሩቅ ተገለጥኩላቸው፤ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፥ እነሆ እናንተን ለዘለዓለም ወደድኳችሁ፤ ዘለዓለማዊ ቸርነቴም ለእናንተ የጸና ይሆናል።
“እንደገናም በአጠገብሽ ሳልፍ ጊዜሽ የፍቅር ዕድሜ ነበር፤ የተራቈተውን ሰውነትሽንም በመጐናጸፊያዬ ሸፍኜ ቃል ገባሁልሽ፤ ከአንቺም ጋር እንደ ጋብቻ ያለ ቃል ኪዳን ገብቼ የእኔ የግሌ አደረግሁሽ፤” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።
መልአኩም “በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ የተወደድክ ዳንኤል ሆይ! እነሆ፥ እኔ ወደ አንተ ተልኬ መጥቼአለሁ፤ ባለህበት ቀጥ ብለህ ቁም፤ የምነግርህንም በጥንቃቄ አስተውል!” አለኝ። ይህን በነገረኝ ጊዜ እየተንቀጠቀጥኩ ቆምኩ።
እርሱም “አንተ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደድክ ሰው ሆይ! መልካም ይሆንልሃል፤ አትፍራ! አይዞህ በርታ!” አለኝ። እርሱም በተናገረኝ ጊዜ ብርታት አገኘሁና “ጌታዬ ሆይ፥ ብርታት ስለ ሰጠኸኝ እነሆ፥ ተናገር” አልኩት።
ገና መጸለይ ስትጀምር እግዚአብሔር ልመናህን ሰምቶአል፤ አንተ በእርሱ ዘንድ የተወደድክ ስለ ሆነ የጸሎትህን መልስ ልነግርህ መጥቼአለሁ፤ እንግዲህ የምነግርህን አዳምጠህ የራእዩን ትርጒም ተረዳ።
የዚህ ዓለም ሰዎች በገዛ ጥበባቸው እግዚአብሔርን ማወቅ እንዳይችሉ እግዚአብሔር በጥበቡ ዘጋባቸው፤ ነገር ግን እንደ ሞኝነት በሚቈጠረው እኛ በምናስተምረው ወንጌል የሚያምኑትን ለማዳን የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖአል።
እናንተ ሞኞች የገላትያ ሰዎች! ማን አፍዝ አደንግዝ አደረገባችሁ? ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ ተሰቅሎ በፊት ለፊታችሁ በግልጥ ይታይ ነበር።
ስለ ብንያምም ነገድ እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር የሚወደው ያለ ስጋት ይረፍ፤ ኀያሉ አምላክ ቀኑን ይጠብቀዋል። በእግዚአብሔር ጥበቃም ሥር ይኖራል።”
የእውነት ቃል የሆነው ወንጌል በመጀመሪያ ወደ እናንተ በደረሰ ጊዜ በእርሱ ያለውን ተስፋ ሰምታችኋል፤ ስለዚህ እምነታችሁና ፍቅራችሁ የተመሠረተው በሰማይ ተዘጋጅቶ በሚቈያችሁ በዚህ ተስፋ ላይ ነው።
እንግዲህ የእግዚአብሔር ምርጦችና ቅዱሳን፥ የተወደዳችሁም እንደ መሆናችሁ መጠን ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትሕትናን፥ ገርነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ።
ዘወትር እየመከርናችሁና እያበረታታናችሁ መንግሥቱንና ክብሩን እንድትካፈሉ የጠራችሁ አምላክ ደስ በሚሰኝበት ሁኔታ እንድትኖሩ ዐደራ እንዳልናችሁ ታውቃላችሁ።
ወንድሞች ሆይ! በእናንተ ምክንያት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤ ማመስገንም ተገቢያችን ነው፤ የምናመሰግነውም እምነታችሁ ይበልጥ እያደገና የእያንዳንዳችሁ የእርስ በርስ ፍቅር እየጨመረ በመሄዱ ነው።
እንዲሁም የሚጠፉትን ሰዎች የሚያታልሉት ማናቸውንም ክፉ ነገሮችን በማድረግ ነው። እነዚህ ሰዎች የሚጠፉትም ለመዳን የሚያበቃቸውን እውነት ወደው ስላልተቀበሉ ነው።
እርሱ እኛ ስላደረግነው መልካም ሥራ ሳይሆን በራሱ ፈቃድና በጸጋው አዳነን፤ ለቅድስናም ጠራን፤ ይህንንም ጸጋ ከዘመናት በፊት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሰጠን።
የእውነትን ቃል በትክክል እንደሚያደርስና በሥራውም እንደማያፍር ሠራተኛ ሆነህ ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብና ተቀባይነትን ለማግኘት ጥረት አድርግ።
ፍቅር ማለት እንዲህ ነው፤ እኛ እግዚአብሔርን ስለ ወደድነው ሳይሆን እርሱ ስለ ወደደንና ኃጢአታችንን እንዲደመስስ ልጁን ስለ ላከልን ነው።