Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 1:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በመ​ጀ​መ​ሪያ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ፈጠረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በመጀመሪያ እግዚአብሔር ስማይንና ምድርን ፈጠረ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 1:1
67 Referencias Cruzadas  

እንዲህ ሲል ጸለየ፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ኪሩቤል ተብለው በሚጠሩ መላእክት ላይ የተቀመጥህ አንተ ብቻ አምላክ ነህ፤ የዓለምንም መንግሥታት የምትመራ አንተ ነህ፤ ሰማይንና ምድርን የፈጠርህ አንተ ነህ፤


ሌሎች ሕዝቦች የሚሰግዱላቸው አማልክት ጣዖቶች ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን የፈጠረ አምላክ ነው።


ንጉሥ ኪራምም ለንጉሥ ሰሎሞን በደብዳቤ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለሚወድ አንተ በእነርሱ ላይ እንድትነግሥ አደረገ።”


ከዚህም ሁሉ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ሲሉ ጸለዩ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ አምላክ አንተ ብቻ ነህ፤ ሰማያትን፥ የሰማያትንም ሰማያት ከነሠራዊታቸው፥ ምድርንና በእርስዋም ላይ የሚገኘውን ሁሉ፥ ባሕሮችንና በእነርሱም ውስጥ የሚገኙትን ሁሉ፥ ፈጠርክ፤ ለሁሉም ሕይወትን ሰጠሃቸው፤ የሰማይ ሠራዊት ይሰግዱልሃል።


በእስትንፋሱ ሰማይን ያጠራል፤ በእጁም ተወርዋሪውን እባብ ይወጋል።


ለመሆኑ ዓለምን ስፈጥር አንተ በዚያ ነበርክን? የምታውቅና የምታስተውል ከሆነ እስቲ ንገረኝ።


ማንም ሳያግዘው ሰማይን የዘረጋ እርሱ ነው፤ እርሱ በባሕር ሞገድ ላይ ይራመዳል።


አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፤ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው።


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ብዙ ነገሮችን ፈጥረሃል፤ ሁሉንም በጥበብ አድርገሃል፤ ምድር አንተ በፈጠርካቸው ነገሮች ተሞልታለች።


እስትንፋስ ስትሰጣቸው ግን ይፈጠራሉ፤ ለምድርም አዲስ ሕይወት ትሰጣለህ።


ሰማይንና ምድርን የፈጠረ እግዚአብሔር ይባርካችሁ!


ርዳታዬ የሚመጣው ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ ከእግዚአብሔር ነው።


ይህንንም ርዳታ ያገኘነው ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።


ሰማይንና ምድርን የፈጠረ እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርካችሁ!


በጥበቡ ሰማያትን ፈጠረ፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።


እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንና በውስጣቸው ያሉትን ሁሉ የፈጠረ ነው። እርሱ ዘወትር ቃል ኪዳኑን ይጠብቃል፤


እግዚአብሔር ሰማያትን በቃሉ፥ በሰማይ የሚገኙትን ፍጥረቶች በትእዛዙ ፈጠረ።


እርሱ በተናገረ ጊዜ ዓለም ተፈጠረ፤ በትእዛዙም ሁሉ ነገር ጸንቶ ቆመ።


አንተ የፈጠርከውን ሰማይ በማይበት ጊዜ፥ በየስፍራቸው አጽንተህ ያኖርካቸውን ጨረቃንና ኮከቦችን በምመለከትበት ጊዜ፥


አንተ እርሱን ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? እርሱንስ ትጐበኘው ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?


ተራራዎችን ከመሥራትህና ዓለምንም ከመፍጠርህ በፊት፥ አንተ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም አምላክ ነህ።


ሌሎች ሕዝቦች የሚሰግዱላቸው አማልክት ጣዖቶች ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን የፈጠረ አምላክ ነው።


በስድስት ቀን እግዚአብሔር ሰማይን፥ ምድርን፥ ባሕርንና በእነርሱ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ሰባተኛውን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም።


እግዚአብሔር ሙሴን በሲና ተራራ ላይ ማነጋገሩን ከፈጸመ በኋላ በእግዚአብሔር ጣት በድንጋይ ላይ የተጻፈባቸውን ሁለቱን የቃል ኪዳን ጽላቶች ሰጠው።


እግዚአብሔር የፈጠረው ነገር ሁሉ ምክንያት አለው፤ የክፉዎችም መጨረሻ ጥፋት ነው።


እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሠረተ፤ በማስተዋልም ሰማያትን አጸና።


በወጣትነትህ ዘመን ፈጣሪህን አስብ፤ ይህን ባታደርግ ግን ክፉ ቀን ይመጣብሃል፤ “ደስ አያሰኙኝም” የምትላቸው ዓመቶች ይደርሳሉ።


“የሠራዊት ጌታ የእስራኤል አምላክ ሆይ! በኪሩቤል ላይ ዙፋን የዘረጋ አምላክ አንተ ብቻ ነህ፤ የዓለምም መንግሥታት ሁሉ አምላክ አንተ ነህ፤ ሰማይና ምድርን የፈጠርክ አንተ ነህ።


ከቶ ይህን አታውቁምን? አልሰማችሁምን? ከመጀመሪያው ጀምሮ አልተነገራችሁምን? ምድር ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ አላስተዋላችሁምን?


ቀና ብላችሁ ወደ ሰማይ ተመልከቱ፤ የምታዩአቸውን ከዋክብት የፈጠረ ማን ነው? እርሱ እንደ ጦር ሠራዊት ይመራቸዋል፤ ምን ያኽል እንደ ሆኑም ቊጥራቸውን ያውቃል፤ እያንዳንዱንም በስሙ ይጠራዋል፤ የእርሱ ሥልጣንና ኀይል እጅግ ታላቅ ነው፤ ስለዚህ ከእነርሱ አንዱ እንኳ አይጠፋም።


ከቶ አታውቅምን? ከቶስ አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘለዓለም አምላክ ነው፤ ዓለምን ሁሉ የፈጠረ እርሱ ነው፤ እርሱ ከቶ አይደክምም ወይም አይታክትም፤ ሐሳቡን መርምሮ ሊደርስበት የሚቻለው የለም።


ሰማይን የፈጠረና ከዳር እስከ ዳር የዘረጋው፥ ምድርንና በውስጥዋ የሚኖሩትን ሁሉ የሠራ፥ ሕይወትንና እስትንፋስንም የሰጣቸው፥ እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ይላል፦


በእናትህ ማሕፀን የፈጠረህ አዳኝህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሁሉን ነገር የፈጠርኩ፥ ሰማያትን ብቻዬን የዘረጋሁ፥ ምድርንም ብቻዬን ያነጠፍኩ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


ሰማያትን የፈጠረው እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ለምድር ቅርጽ ሰጥቶ የሠራት፥ የመሠረታትም እርሱ ነው፤ የፈጠራትም መኖሪያ እንድትሆን ነው እንጂ፥ ቅርጽ የሌላትና ባዶ እንድትሆን አይደለም፤ እርሱ፦ “ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤


ምድርን የመሠረተና ሰማያትን የዘረጋ ፈጣሪአችሁን እግዚአብሔርን ረስታችኋል፤ ሊያጠፉአችሁ ከተዘጋጁ ከጨቋኞቻችሁ ቊጣ የተነሣ፥ ዘወትር በፍርሃት ትኖራላችሁ። የእነርሱስ ቊጣ የት አለ?


ቃሌን በአንደበትሽ አሳድራለሁ፤ አንቺንም በእጄ ጥላ ሥር እጋርድሻለሁ፤ ሰማያትን የዘረጋሁ፥ ምድርንም የመሠረትኩ እኔ ነኝ፤ ጽዮንንም ‘አንቺ ሕዝቤ ነሽ’ እላታለሁ።”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ እኔ አዳዲስ ሰማያትንና አዲስ ምድርን እፈጥራለሁ፤ ከዚህ በፊት የነበሩት ሁሉ ይረሳሉ፤ አይታሰቡምም።


እግዚአብሔር በኀይሉ ምድርን ሠራ፤ በጥበቡም ዓለምን ፈጠረ፤ በማስተዋሉም ሰማያትን ዘረጋ፤


“ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! በታላቁ ሥልጣንህና ኀይልህ ሰማይና ምድርን ፈጥረሃል፤ ከቶም የሚሳንህ ነገር የለም፤


እግዚአብሔር በኀይሉ ምድርን፥ በጥበቡም ዓለምን ፈጠረ፤ በማስተዋሉም ሰማያትን ዘረጋ፤


ሰማይን የዘረጋ፥ ምድርን የመሠረተ፥ ለሰውም የሕይወትን እስትንፋስ የሰጠ እግዚአብሔር ስለ እስራኤል እንዲህ ይላል፦


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ! ይህን ነገር ከጥበበኞችና ከዐዋቂዎች ሰውረህ ለአላዋቂዎች ስለ ገለጥክላቸው አመሰግንሃለሁ፤


በዚያን ወራት እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ታይቶ የማይታወቅ መከራ ይሆናል፤ ወደ ፊትም እሱን የሚመስል ጭንቀት ከቶ አይደርስም።


“እናንተ ሰዎች ለምን ይህን ታደርጋላችሁ? እኛም እንደ እናንተ ሰዎች ነን፤ እኛ እዚህ የመጣነው እናንተ ከዚህ ከከንቱ ነገር ሁሉ ርቃችሁ ሰማይን፥ ምድርን፥ ባሕርንና በውስጣቸው የሚገኙትን ሁሉ ወደ ፈጠረው ወደ ሕያው አምላክ እንድትመለሱ መልካም ዜና ልናበሥርላችሁ ነው፤


እርሱ ዓለምንና በዓለም ያለውንም ሁሉ የፈጠረ ነው፤ የሰማይና የምድርም ጌታ ነው፤ እርሱ በሰው እጅ በተሠራ ቤተ መቅደስ አይኖርም፤


እነርሱም ይህን በሰሙ ጊዜ ድምፃቸውን በአንድነት ከፍ አድርገው ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲሉ ጸለዩ፤ “ሰማይን፥ ምድርን፥ ባሕርን፥ በውስጣቸው የሚኖረውን ሁሉ የፈጠርክ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ!


ሁሉም ነገር የተገኘው ከእርሱ፥ በእርሱና ለእርሱ ነው፤ ለዘለዓለም ክብር ለእርሱ ይሁን! አሜን!


የእኛ አምላክ ግን የሁሉ ነገር ፈጣሪና እኛም የእርሱ የሆንን አንዱ እግዚአብሔር አብ ብቻ ነው፤ እንዲሁም ሁሉ ነገር በእርሱ የተፈጠረና እኛም በእርሱ የምንኖር አንዱ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።


እንዲሁም ባለፉት ዘመናት ሁሉን በፈጠረ በእግዚአብሔር ተሰውሮ ስለ ነበረው ምሥጢር የእግዚአብሔር ዕቅድ ምን እንደ ሆነ ለሁሉ እንድገልጥ ጸጋ ተሰጠኝ።


እንዲሁም፥ “ጌታ ሆይ! አንተ በመጀመሪያ ምድርን መሠረትህ፤ ሰማያት የእጅህ ሥራ ናቸው፤


አሁን ግን በእነዚህ በኋለኞቹ ዘመናት ሁሉን ነገር ወራሽ ባደረገው በልጁ አማካይነት ለእኛ ተናገረን፤ ዓለምንም ሁሉ የፈጠረው በእርሱ ነው።


ዓለም በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተፈጠረ የምንረዳው በእምነት ነው። ስለዚህ የሚታየው ነገር ሁሉ ከማይታየው እንደ ተሠራ እናውቃለን።


በእርግጥ ለእያንዳንዱ ቤት ሠሪ አለው፤ ሁሉን ነገር የሠራ ግን እግዚአብሔር ነው።


እነዚህ ሰዎች ከብዙ ዘመን በፊት ሰማይ በእግዚአብሔር ቃል መፈጠሩን ምድርም የተሠራችው ከውሃና በውሃ መሆኑን ሆን ብለው ይክዳሉ።


ከመጀመሪያው ስለ ነበረው ስለ ሕይወት ቃል እንጽፍላችኋለን፤ ይህ የሕይወት ቃል የሰማነውና በዐይኖቻችን ያየነው፥ የተመለከትነውና በእጆቻችን የዳሰስነው ነው።


ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሚኖረው፥ ሰማይንና በእርሱ ውስጥ ያሉትን፥ ምድርንና በእርስዋ ውስጥ ያሉትን፥ ባሕርንና በእርሱም ውስጥ ያሉትን በፈጠረው አምላክ ስም ምሎ እንዲህ አለ፦ “ከእንግዲህ ወዲህ አይዘገይም!


በታላቅ ድምፅም “እግዚአብሔርን ፍሩ! አክብሩትም! የእርሱ የፍርድ ሰዓት ደርሶአል፤ ሰማይንና ምድርን ባሕርንና የውሃ ምንጮችን ለፈጠረ አምላክ ስገዱ!” አለ።


ከዚህም በኋላ እንዲህ አለኝ፤ “ተፈጸመ! አልፋና ዖሜጋ፥ የመጀመሪያውና የመጨረሻው እኔ ነኝ፤ ለተጠማ ከሕይወት ውሃ ምንጭ ያለ ምንም ዋጋ በነጻ እሰጠዋለሁ፤


አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።”


“ለሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ “ይህ፥ አሜን ከሆነው፥ ታማኝና እውነተኛ ምስክር ከሆነው፥ የእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ መገኛ ከሆነው የተነገረ ነው፤


“ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ ሁሉን ነገር ስለ ፈጠርክ ሁሉም ነገር የተፈጠረውና የሚኖረው (ሕይወትን ያገኘው) በአንተ ፈቃድ ስለ ሆነ ገናናነት፥ ክብርና ኀይልም ለአንተ ይገባል” ይሉ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos