Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዳንኤል 10:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 መልአኩም “በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ የተወደድክ ዳንኤል ሆይ! እነሆ፥ እኔ ወደ አንተ ተልኬ መጥቼአለሁ፤ ባለህበት ቀጥ ብለህ ቁም፤ የምነግርህንም በጥንቃቄ አስተውል!” አለኝ። ይህን በነገረኝ ጊዜ እየተንቀጠቀጥኩ ቆምኩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እርሱም፣ “እጅግ የተወደድህ ዳንኤል ሆይ፤ አሁን ወዳንተ ተልኬአለሁና፣ የምነግርህን አስተውል፤ ቀጥ ብለህም ቁም” አለኝ። ይህን ሲለኝም፣ እየተንቀጠቀጥሁ ተነሥቼ ቆምሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እርሱም፦ እጅግ የተወደድህ ሰው ዳንኤል ሆይ፥ እኔ ዛሬ ወደ አንተ ተልኬአለሁና የምነግርህን ቃል አስተውል፥ ቀጥ ብለህም ቁም አለኝ። ይህንም ቃል ባለኝ ጊዜ እየተንቀጠቀጥሁ ቆምሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 10:11
15 Referencias Cruzadas  

“በውሽንፍሩም ኀይል ልቤ ተንቀጠቀጠ፤ በፍርሃትም ተርበደበደ።


በውበትሽ ንጉሡ ይወድሻል፤ ሆኖም ጌታሽ በመሆኑ እጅ በመንሣት አክብሪው።


እኔ የውዴ ነኝ፤ የእርሱም ምኞት ወደ እኔ ነው።


እነዚያ ሦስት ሰዎች ማለትም ኖኅ፥ ዳንኤልና ኢዮብ በውስጥዋ ቢገኙ እንኳ በደግነታቸው ማትረፍ የሚችሉት የራሳቸውን ሕይወት ብቻ ነው፤ ይህን የተናገረ ጌታ እግዚአብሔር ነው።


ከዚያም በኋላ “የሰው ልጅ ሆይ! ተነሥተህ በእግርህ ቁም፤ እኔም አነጋግርሃለሁ” አለኝ።


እርሱም “አንተ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደድክ ሰው ሆይ! መልካም ይሆንልሃል፤ አትፍራ! አይዞህ በርታ!” አለኝ። እርሱም በተናገረኝ ጊዜ ብርታት አገኘሁና “ጌታዬ ሆይ፥ ብርታት ስለ ሰጠኸኝ እነሆ፥ ተናገር” አልኩት።


ሥጋም ሆነ ሌላ ጥሩ ምግብ አልተመገብኩም፤ የወይን ጠጅም ፈጽሞ አልቀመስኩም፤ ሦስቱ ሳምንቶች እስኪያልፉ ድረስ ራሴን ቅባት አልተቀባሁም።


ሴቶቹም በፍርሃት እየተንቀጠቀጡ ከመቃብሩ ቦታ ወጥተው ሸሹ፤ እጅግ ፈርተው ስለ ነበር ምንም ነገር ለማንም አልተናገሩም። [


ኢየሱስ ይወደው የነበረው፥ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ በኢየሱስ ጐን ተቀምጦ ነበር።


ጴጥሮስ ዘወር ብሎ ኢየሱስ የሚወድደው ደቀ መዝሙር ሲከተለው አየ፤ ይህ ደቀ መዝሙር በእራት ጊዜ ወደ ኢየሱስ ተጠግቶ፥ “ጌታ ሆይ፥ አሳልፎ የሚሰጥህ ማን ነው?” ብሎ የጠየቀው ነው።


አሁን ግን ተነሥና በእግርህ ቁም፤ እኔ የተገለጥኩልህ አሁን እኔን ባየህበትና ወደፊትም እኔ ለአንተ በምገለጥበት ነገር አገልጋይና ምስክር እንድትሆነኝ ልሾምህ ፈልጌ ነው።


አሁን ግን ተነሥና ወደ ከተማ ግባ፤ ልታደርገው የሚገባህም እዚያ ይነገርሃል” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos