እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “ለራስህ ረጅም ዕድሜ ወይም ሀብት ለማግኘት ወይም ጠላቶችህ እንዲጠፉልህ መመኘት ሳይሆን በትክክለኛ ፍርድ ማስተዳደር የምትችልበትን ጥበብ ስለ ጠየቅህ፥
1 ጢሞቴዎስ 2:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ በየስፍራው ያሉ ወንዶች ቊጣንና ጥልን አስወግደው የተቀደሱ እጆቻቸውን ወደ ላይ በማንሣት እንዲጸልዩ እፈልጋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ወንዶች በሁሉም ቦታ ያለ ቍጣና ያለ ክርክር የተቀደሱ እጆቻቸውን ወደ ላይ በማንሣት እንዲጸልዩ እፈልጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ በሁሉ ስፍራ ያሉ ወንዶች ንዴትንና ጥልን አስወግደው የተቀደሱ እጆቻቸውን እያነሡ እንዲጸልዩ ፈቃዴ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ወንዶች በስፍራ ሁሉ አለ ቍጣና አለ ክፉ አሳብ የተቀደሱትን እጆች እያነሡ እንዲጸልዩ እፈቅዳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ወንዶች በስፍራ ሁሉ አለ ቍጣና አለ ክፉ አሳብ የተቀደሱትን እጆች እያነሱ እንዲጸልዩ እፈቅዳለሁ። |
እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “ለራስህ ረጅም ዕድሜ ወይም ሀብት ለማግኘት ወይም ጠላቶችህ እንዲጠፉልህ መመኘት ሳይሆን በትክክለኛ ፍርድ ማስተዳደር የምትችልበትን ጥበብ ስለ ጠየቅህ፥
ዐመፀኞች የሚያቀርቡት መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ አጸያፊ ነው፤ በተለይም በክፉ አሳብ ተነሣሥተው የሚያቀርቡለት መሥዋዕት የበለጠ አጸያፊ ነው።
“እጆቻችሁን ወደ እኔ ለጸሎት ብትዘረጉ፥ ወደ እናንተ አልመለከትም፤ እጆቻችሁ በደም የተበከሉ ስለ ሆኑ የቱንም ያኽል ልመና ብታበዙ አልሰማችሁም፤
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “በእውነት እላችኋለሁ፤ እምነት ቢኖራችሁና ባትጠራጠሩ በበለሲቱ ዛፍ ላይ እንደ ተደረገው ማድረግ ብቻ ሳይሆን ይህንን ተራራ እንኳ ‘ከዚህ ተነሥተህ ወደ ባሕር ተወርወር!’ ብትሉት ይሆንላችኋል።
እኔ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁን መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁ በጎ አድርጉ፤ ክፉ ለሚያደርጉባችሁና ለሚያሳድዱአችሁ ጸልዩ” እላችኋለሁ።
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ፦ “አባት ሆይ! የሚያደርጉትን ስለማያውቁ ይቅር በላቸው!” አለ። ወታደሮቹም ዕጣ ተጣጥለው የኢየሱስን ልብስ ተከፋፈሉ።
እርሱ ከቤተ ሰቡ ሁሉ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክና የሚፈራ ሰው ነበረ፤ ለድኾችም ብዙ ምጽዋት ይሰጥ ነበር፤ ወደ እግዚአብሔርም ዘወትር ይጸልይ ነበር።
ትኲር ብሎ ወደ መልአኩ ተመለከተና በመደንገጥ “ጌታ ሆይ! ምንድን ነው?” አለ። መልአኩም እንዲህ አለው፦ “ጸሎትህና ለድኾች የምታደርገው ምጽዋት መልካም መታሰቢያ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ዐርጓል፤
እዚያ የምንቈይበት ጊዜ ሲያልቅ ተለይተናቸው ጒዞአችንን ቀጠልን፤ ሁሉም ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር ሆነው እስከ ከተማው ውጪ ድረስ ሸኙን፤ በባሕሩም ዳር ተንበርክከን ከጸለይን በኋላ ተሰነባበትን።
በቆሮንቶስ ከተማ ለምትገኘው የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ በውስጥዋም በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱትና ቅዱሳን እንዲሆኑ ለተጠሩት፥ እንደዚሁም በየቦታው ለእነርሱና ለእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ለሚጠሩት ሁሉ።
ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሚስት ሳያገባ ቢኖር በወደድኩ ነበር፤ ነገር ግን ለእያንዳንዱ እግዚአብሔር የተለየ ስጦታ ሰጥቶታል፤ አንዱ አንድ ዐይነት ስጦታ፥ ሌላውም ሌላ ዐይነት ስጦታ አለው።
ነገር ግን እኛን ዘወትር በክርስቶስ ድል አድራጊዎች አድርጎ ለሚመራንና መልካም መዓዛ እንዳለው ሽቶ ስለ ክርስቶስ ያለንን ዕውቀት በየስፍራው ሁሉ እንድናዳርስ ለሚያደርገን አምላክ ምስጋና ይሁን!
የጌታ ቃል ከእናንተ ወጥቶ የተሰማው በመቄዶንያና በአካይያ ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ያላችሁ እምነት በሁሉ ቦታ ታውቆ ነበር፤ በዚህ ምክንያት እኛ ስለዚህ ጉዳይ ምንም መናገር አያስፈልገንም።
ስለዚህ በዕድሜአቸው ያልገፉ መበለቶች እንዲያገቡ፥ ልጆችን እንዲወልዱ፥ ቤታቸውንም በሚገባ እንዲያስተዳድሩ እመክራለሁ፤ በዚህ ዐይነት ጠላት ለስም ማጥፋት ምክንያት ያጣል።
ይህ የታመነ አባባል ነው። በእግዚአብሔር ያመኑ ሰዎች ለመልካም ሥራ እንዲተጉ ይህን ነገር ሁሉ በጥብቅ እንድታስገነዝብ እፈልጋለሁ፤ ይህም ነገር መልካምና ለእያንዳንዱ ሰው ጠቃሚ ነው።
ስለዚህ ከክፉ ኅሊና እንድንነጻ ልባችንን ተረጭተን፥ ሰውነታችንንም በንጹሕ ውሃ ታጥበን፥ ቅን ልብና እውነተኛ እምነት ይዘን ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ።
እናንተም ባሎች! ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ከእናንተ ይልቅ ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑና ከእናንተም ጋር የሕይወትን ጸጋ ስለሚወርሱ አክብሩአቸው፤ በዚህ ዐይነት ለጸሎታችሁ መሰናክል የሚሆን ነገር አይኖርም።