1 ሳሙኤል 20:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጁም ከሄደ በኋላ ዳዊት ከድንጋዩ ቊልል በስተኋላ ከተደበቀበት ስፍራ ወጥቶ በጒልበቱ በመንበርከክ ሦስት ጊዜ ወደ መሬት ሰገደ፤ እርሱና ዮናታን በሚሳሳሙበት ጊዜ ሁለቱም ያለቅሱ ነበር፤ ከዮናታንም ይልቅ የዳዊት ሐዘን የበረታ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጁ ከሄደ በኋላ፣ ዳዊት ከድንጋዩ በስተ ደቡብ ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ በዮናታን ፊት ሦስት ጊዜ በምድር ላይ ተደፍቶ ሰገደለት፤ ከዚያም ተሳሳሙ፤ ተላቀሱም፤ በይበልጥ ያለቀሰው ግን ዳዊት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጁ ከሄደ በኋላ፥ ዳዊት ከድንጋዩ በስተ ደቡብ ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ በዮናታን ፊት ሦስት ጊዜ በምድር ላይ ተደፍቶ ሰገደለት፤ ከዚያም ተሳሳሙ፤ ተላቀሱም፤ በይበልጥ ያለቀሰው ግን ዳዊት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብላቴናውም በሄደ ጊዜ ዳዊት ከኤርገብ ተነሣ፤ በምድርም ላይ በግንባሩ ተደፋ፤ ሦስት ጊዜም ሰገደ፤ እርስ በእርሳቸውም ተሳሳሙ፤ ለረዥም ሰዓትም ተላቀሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብላቴናውም በሄደ ጊዜ ዳዊት ከስፍራው በደቡብ አጠገብ ተነሣ፥ በምድርም ላይ በግምባሩ ተደፋ፥ ሦስት ጊዜም ለሰላምታ ሰገደ፥ እየተላቀሱም እርስ በእርሳቸው ተሳሳሙ፥ ይልቁንም ዳዊት እጅግ አለቀስ። |
ላባም የእኅቱ ልጅ ያዕቆብ መምጣቱን በሰማ ጊዜ ሊቀበለው ፈጥኖ ሄደ፤ ዐቅፎ ከሳመውም በኋላ ወደ ቤት አመጣው፤ ያዕቆብ የሆነውን ሁሉ ለላባ ነገረው፤
ዮሴፍ የግብጽ ምድር አስተዳዳሪ በመሆኑ ከዓለም ዙሪያ ለሚመጡ ሰዎች ሁሉ እህል እንዲሸጥላቸው ያደርግ ነበር፤ ስለዚህ የዮሴፍ ወንድሞች ወደ እርሱ መጡና ግንባራቸው መሬት እስኪነካ ዝቅ ብለው እጅ ነሡት።
በሦስተኛው ቀን አንድ ወጣት ከሳኦል ሰፈር መጣ፤ ልብሱን ቀዶ በራሱ ላይ ትቢያ ነስንሶ ነበር፤ ወደ ዳዊትም ቀርቦ በአክብሮት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ፤
“ወንድሜ ዮናታን ሆይ! እኔ ስለ አንተ በጣም አዘንኩ፤ አንተ ለእኔ በጣም ተወዳጅ ነበርክ። ፍቅርህ ለእኔ አስደናቂ ነበር፤ ይኸውም ከሴት ፍቅር የበረታ ነበር።
የሳኦል የልጅ ልጅ፥ የዮናታን ልጅ መፊቦሼት በመጣ ጊዜ በዳዊት ፊት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት አክብሮቱን ገለጠ። ዳዊትም “መፊቦሼት!” ሲል ጠራው። መፊቦሼትም “ጌታ ሆይ! እነሆ አገልጋይህ ነኝ!” ሲል መለሰ።
ሳሙኤል የወይራ ዘይት መያዣውን ቀንድ ወስዶ በሳኦል ራስ ላይ አፈሰሰው፤ ሳመውም። ከዚያም በኋላ “እግዚአብሔር በሕዝቡ በእስራኤል ላይ መሪ እንድትሆን ቀባህ፤ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ነግሠህ በዙሪያቸው ካሉ ጠላቶች ታድናቸዋለህ እግዚአብሔር በርስቱ ላይ የሾመህ ለመሆኑ ይህ ማስረጃ ነው፤