1 ሳሙኤል 2:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰው ድልን የሚያገኘው በኀይሉ ስላልሆነ እግዚአብሔር የታማኞቹን እርምጃዎች ይጠብቃል፤ ክፉዎች ግን ወደ ጨለማ ይጣላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ የታማኝ አገልጋዮቹን እግር ይጠብቃል፤ ክፉዎች ግን በጨለማ ውስጥ ይጣላሉ። “ሰው በኀይሉ ድል አያደርግም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ የታማኞቹን እግር ይጠብቃል ሰው በኃይሉ አይበረታምና፥ ኃጥአን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይጣላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሚጸልይ ጸሎቱን ይሰጠዋል፤ የጻድቃንን ዘመን ይባርካል፤ የሰው ኀይል ጽኑዕ አይደለምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ የቅዱሳኑን እግር ይጠብቃል ኃጥአን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይቀመጣሉ፥ ሰው በኃይሉ አይበረታምና። |
በዚህ ዓለም የተመለከትኩት ሌላም ነገር አለ፤ ይኸውም ፈጣን ሯጮች በአሸናፊነት አይወጡም፤ ጀግኖችም በጦርነት ድል አያደርጉም፤ ጠቢባን የዕለት እንጀራን፥ ብልኆች ሀብትን አያገኙም፤ ችሎታ ያላቸውም ሰዎች በማዕርግ አያድጉም፤ ነገር ግን ሁሉንም ጊዜና ዕድል ያጋጥማቸዋል፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ባቢሎን ሆይ! በጨለማ ውስጥ ጸጥ ብለሽ ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ‘የመንግሥታት ንግሥት’ ብለው አይጠሩሽም፤
የእግዚአብሔር ሕዝብ እንዲህ ይላሉ፦ “ዝም ብለን መቀመጣችን ለምንድን ነው? አምላካችን እግዚአብሔር ሞት ፈርዶብናል፤ እርሱን ስለ በደልን የተመረዘ ውሃ እንድንጠጣ አድርጎናል። ኑ! ወደተመሸጉ ከተሞች ሮጠን እዚያ እንሙት፤
ለዘሩባቤል እንዳስታወቀው መልአኩ የነገረኝ የሠራዊት አምላክ ቃል ይህ ነው፤ “ድል የምትነሣው በመንፈሴ እንጂ በኀይልና በብርታት አይደለም።
የሕግ ትእዛዝ የሚመለከተው ከሕግ በታች ያሉትን እንደ ሆነ እናውቃለን፤ በዚህ ምክንያት ሰዎች የሚያመካኙት አጥተው ዝም ይላሉ፤ ዓለሙም ሁሉ በእግዚአብሔር ፍርድ ሥር ይሆናል።
የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና የያዕቆብ ወንድም ከሆነው ከይሁዳ፥ ለተጠራችሁት፥ በእግዚአብሔር አብ ለተወደዳችሁት፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለተጠበቃችሁት ሁሉ፥
የአሳፋሪ ድርጊታቸውን ዐረፋ የሚደፍቁ፥ እንደ ተቈጣ የባሕር ማዕበል ናቸው፤ ድቅድቅ ጨለማ ለዘለዓለም እንደሚጠብቃቸውና፥ እንደሚንከራተቱ ኮከቦች ናቸው።
ወዳጆች ሆይ! ስለ ጋራ መዳናችን ልጽፍላችሁ በብርቱ ፈልጌ ነበር፤ አሁን ግን በማያዳግም ሁኔታ እግዚአብሔር ለሕዝቡ አንድ ጊዜ ስለ ሰጠው እምነት በብርቱ እንድትጋደሉ ለመምከር ልጽፍላችሁ ግድ ሆነብኝ።
የበቀል እርምጃ በመውሰድ ጠላቶችህን እንዳትገድል የጠበቀህ ራሱ እግዚአብሔር ነው፤ እነሆ፥ እኔ አሁን በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ፤ ጠላቶችህና አንተን ለመጒዳት የሚፈልጉ ሁሉ እንደ ናባል ቅጣታቸውን ይቀበሉ፤