Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 31:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እግዚአብሔር ሆይ! ወደ አንተ በምጣራበት ጊዜ አታሳፍረኝ፤ ክፉዎች ግን ይፈሩ፤ ጸጥ ብለውም ወደ ሲኦል ይውረዱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጮኻለሁና አልፈር፤ ክፉዎች ግን ይፈሩ፤ ሲኦል ገብተውም ጸጥ ይበሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ፊትህን በባርያህ ላይ አብራ፥ ስለ ምሕረትህም አድነኝ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 31:17
25 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ግን እንደ ጀግና ወታደር ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ በመደናቀፍ ኀይል አጥተው ይወድቃሉ። በሚወድቁበትም ጊዜ ክፉኛ ይዋረዳሉ፤ ውርደታቸውም ለረጅም ጊዜ ይታወሳል።


ወደ ዝምታ ዓለም፥ ወደ መቃብር የወረዱ ሙታን እግዚአብሔርን ሊያመሰግኑት አይችሉም።


በእኔ መከራ ተደስተው ትኲር ብለው በንቀት የሚመለከቱኝ ሁሉ ይፈሩ፤ ግራም ይጋቡ፤ በእኔ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ሁሉ ኀፍረትንና ውርደትን ይልበሱ።


ወደ እርሱ የሚመለከቱ ሁሉ ፊታቸው ይበራል፤ ፊታቸውም ከቶ በኀፍረት አይሸፈነም።


እግዚአብሔር ባይረዳኝ ኖሮ፥ ፈጥኜ ወደ ሙታን ዓለም በወረድኩ ነበር።


ሊጐዱኝ የሚፈልጉ ስላፈሩና ግራ ስለ ተጋቡ አንደበቴ ቀኑን ሙሉ ስለ እውነተኛ ርዳታህ ይናገራል።


እኔን ለመግደል የሚፈልጉ ሁሉ ኀፍረትና ውርደት ይድረስባቸው! በእኔ ላይ የሚያሤሩም ሁሉ ተዋርደው ወደ ኋላቸው ይመለሱ!


“ሰው ድልን የሚያገኘው በኀይሉ ስላልሆነ እግዚአብሔር የታማኞቹን እርምጃዎች ይጠብቃል፤ ክፉዎች ግን ወደ ጨለማ ይጣላሉ።


ሞተው ዐፈር የበላቸው ሁሉ ይነሣሉ፤ ከእነርሱም ከፊሎቹ ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ሲገቡ ከፊሎቹ ደግሞ ወደ ዘለዓለማዊ ኀፍረትና ውርደት ይላካሉ።


እግዚአብሔር ሆይ! መጠጊያ እንድትሆነኝ ወደ አንተ መጥቻለሁ፤ ስለዚህ እንዳፍር አታድርገኝ፤ በጽድቅህም አድነኝ።


ጠላቶቼ ሁሉ ያፍራሉ፤ በድንገትም ተዋርደው ወደ ኋላቸው ይሸሻሉ።


ሌሎች ከእህልና ከወይን ከሚያገኙት ደስታ ይልቅ አንተ በልቤ ያኖርከው ደስታ ይበልጣል።


የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! የሕዝብህን ጸሎት ባለመቀበል ቊጣህን የምትገልጠው እስከ መቼ ነው?


የወይን ሐረግን ከግብጽ አመጣህ፤ ሌሎች ሕዝቦችን አስወግደህ በምድራቸው እርስዋን ተከልክ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios