ሮሜ 11:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔር ባለጸግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው! ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው! መንገዱም የማይታወቅ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር የጥበቡና የዕውቀቱ ባለጠግነት እንዴት ጥልቅ ነው! ፍርዱ አይመረመርም፤ ለመንገዱም ፈለግ የለውም! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ባለጸግነትና ጥበብ ዕውቀትም እንዴት ጥልቅ ነው! ፍርዱ የማይመረመር፥ መንገዱም የማይታወቅ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ባለጠግነት፥ ጥበብና ዕውቀት እንዴት ጥልቅ ነው! ለመንገዱም ፍለጋ የለውም፤ ፍርዱንም የሚያውቀው የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም። |
ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤ እግዚአብሔርም ከጥንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠራውን ሥራ ሰው መርምሮ እንዳያገኝ ዘላለማዊነትን በልቡ ሰጠው።
የእግዚአብሔርንም ሥራ ሁሉ አየሁ፤ እርሱም ከፀሐይም በታች የተደረገውን ሥራ መርምሮ ሰው ማግኘት አለመቻሉን፥ ሰውም በመፈለግ እጅግ ቢደክምም መርምሮ አለማግኘቱን ነው፥ ደግሞም ጠቢብ ሰው አውቀዋለሁ ቢልም እንኳን ይህንን ለማግኘት አይችልም።
በዚህም ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት እንድትታወቅ ነው።
ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለጠግነት ምን እንደሆነ ሊያሳውቅ ወደደ፤ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ የሆነው በእናንተ ያለው ክርስቶስ ነው።