Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 33:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 አንተ፦ ‘በፍጹም ለቃሌ መልስ አይሰጥም’ ብለህ፥ ስለምን ከእርሱ ጋር ትከራከራለህ?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የሰውን አቤቱታ እንደማይሰማ፣ ለምን ታማርርበታለህ?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ታዲያ፥ ‘እግዚአብሔር የሰውን አቤቱታ አይሰማም’ በማለት ለምን በእግዚአብሔር ላይ ታማርራለህ?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 አንተ፦ ‘ቃሌን ሁሉ ለምን አይ​ሰ​ማ​ኝም?’ ትላ​ለህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 አንተ፦ ለቃሌ ሁሉ አይመልስልኝም ብለህ፥ ስለ ምን ከእርሱ ጋር ትከራከራለህ?

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 33:13
21 Referencias Cruzadas  

“በውኑ የሚከራከር ሰው ሁሉን የሚችል አምላክን መተቸት ይችላልን? ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋቀስ እርሱ ይመልስለት።”


ከሠሪው ጋር ለሚታገል ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መካከል ያለ ሸክላ ነው። ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? ወይስ ሥራህ እጅ የለውም ይላልን?


ወይስ ጌታን እናስቀናውን? እኛስ ከእርሱ ይልቅ እንበረታለንን?


“የጌታን ልብ የሚያውቅ ማን ነው?” “ወይስ አማካሪው የሆነ ማን ነው?


ከእግዚአብሔር እንደሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም፤ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ።’”


እርሱም “አብ በገዛ ሥልጣኑያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም፤


የራሴ በሆነ ነገር ላይ የወደድሁትን ማድረግ አልችልምን? ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንኩ ትመቀኛለህን?


ከአንቺ ጋር በምነጋገርበት ጊዜ ልብሽ መቋቋም ይችላልን? እጆችሽስ ይጸናሉን? እኔ ጌታ ተናግሬአለሁ፥ አደርገዋለሁም።


ባቢሎን ሆይ! አጥምጄብሻለሁ አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል፤ ከጌታ ጋር ስለ ታገልሽ ተገኝተሻል ተይዘሻልም።


በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እነግራለሁ፤ “ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ” እላለሁ።


ዓመፃን ተስፋ አታድርጉ፥ ቅሚያንም አትተማመኑት፥ ባለጠግነት ቢበዛ ልባችሁ አይኩራ።


ይልቁንስ እመልስለት ዘንድ፥ ቃሌንስ በፊቱ እመርጥ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?


“ምስጢሩ ለአምላካችን ለጌታ ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ እንድንከተል ለዘለዓለም ለእኛና ለልጆቻችን ነው።”


ነገር ግን፥ ሰው ሆይ! ለእግዚአብሔር መልስ የምትሰጥ አንተ ማን ነህ? የተሠራ ነገር የሠራውን “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ይለዋልን?


“የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ልትመረምር ትችላለህን? ሁሉን የሚችል አምላክን ፍጻሜ ልትመረምር ትችላለህን?


እነሆ፥ ፈጥኖ ቢነጥቅ የሚከለክለው ማን ነው? እርሱንስ፦ ምን ታደርጋለህ? የሚለው ማን ነው?”


እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ አትፍረድብኝ፥ የምትከራከረኝ ለምን እንደሆነ ንገረኝ።


ታዲያ ክፋቴን የምትከታተለው፥ ኃጢአቴንም የምትመረምረው ለምንድን ነው?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios