Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 92:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አቤቱ፥ በሥራህ ደስ አሰኝተኸኛልና፥ በእጅህም ሥራ ደስ ይለኛልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህ እንዴት ታላቅ ነው! ሐሳብህስ ምን ያህል ጥልቅ ነው!

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እግዚአብሔር ሆይ! ሥራህ እንዴት ታላቅ ነው! ሐሳብህስ እንዴት ጥልቅ ነው!

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ምስ​ክ​ርህ እጅግ የታ​መነ ነው፤ አቤቱ፥ እስከ ረዥም ዘመን ድረስ ለቤ​ትህ ምስ​ጋና ይገ​ባል።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 92:5
15 Referencias Cruzadas  

ጌታን የታመነ ወደ ትዕቢተኛና ወደ ሐሰተኛ ያልተመለከተ ሰው ብፁዕ ነው።


አቤቱ፥ ሐሳቦችህ በእኔ ዘንድ እንደምን እጅግ የተከበሩ ናቸው! ቁጥራቸውም እንደምን በዛ!


ለእኛ ግን እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው። መንፈስ፥ የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር፥ ሁሉን ይመረምራልና።


የጌታ ሥራዎች ታላላቅ ናቸው፥ ደስ በሚሰኙባቸው ሁሉ ይፈለጋሉ።


“ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ! የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፤ የጽድቅም ሥራህ ስለ ተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፤ በፊትህም ይሰግዳሉ፤” እያሉ የእግዚአብሔርን ባርያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ።


ይህም ደግሞ በምክሩ ድንቅ በጥበቡ የላቀ ከሆነው ከሠራዊት ጌታ ወጥቶአል።


አቤቱ፥ ሥራህ እጅግ ብዙ ነው፥ ሁሉን በጥበብ አደረግህ፥ ምድርም ከፍጥረትህ ተሞላች።


እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፦ “ሥራህ እንዴት ግሩም ነው፥ ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ።


የጌታ ቁጣ የልቡን አሳብ ሠርቶ እስኪፈጽም ድረስ አይመለስም፤ በኋለኛው ዘመን ፈጽማችሁ ታስተውሉታላችሁ።


የሆነው ነገር ራቀ፥ እጅግም ጠለቀ፥ መርምሮ የሚያገኘውስ ማን ነው?


አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህ በሰማይ ነው፥ ታማኝነትህም ወደ ደመናት ትደርሳለች።


ለእነርሱ ለራሳቸው ክፉ ነገርን አጸኑ፥ ወጥመድን ይሰውሩ ዘንድ ተማከሩ፥ ማንስ ያየናል? ይላሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios