መክብብ 8:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 የእግዚአብሔርንም ሥራ ሁሉ አየሁ፤ እርሱም ከፀሐይም በታች የተደረገውን ሥራ መርምሮ ሰው ማግኘት አለመቻሉን፥ ሰውም በመፈለግ እጅግ ቢደክምም መርምሮ አለማግኘቱን ነው፥ ደግሞም ጠቢብ ሰው አውቀዋለሁ ቢልም እንኳን ይህንን ለማግኘት አይችልም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 አምላክ ያደረገውን ሁሉ አየሁ። ከፀሓይ በታች የሚደረገውን ማንም ሊያውቅ አይችልም፤ ሰው ለመመርመር ብዙ ቢጥርም፣ ትርጕሙን ማግኘት አይችልም፤ ጠቢብም እንኳ ዐውቀዋለሁ ቢል፣ ፈጽሞ ሊገነዘበው አይችልም። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ሰው በምርምር ብዛትም እግዚአብሔር የሚያደርገውን ነገር ሁሉ ማወቅ እንደማይችል አረጋገጥኩ፤ ሰው ብዙ ነገር መርምሮ ለማወቅ የቱንም ያኽል ቢደክም አንዳች ነገር ማግኘት አይችልም፤ በእርግጥ ጥበበኞች ሰዎች “ይህንን እናውቃለን” ለማለት ይደፍሩ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ የሚያውቁት ነገር የለም። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ከፀሓይም በታች የተደረገውን ሥራ መርምሮ ያገኝ ዘንድ ለሰው እንዳይቻለው የእግዚአብሔርን ሥራ ሁሉ አየሁ። ሰውም ሊፈልግ እጅግ ቢደክም መርምሮ አያገኘውም፤ ደግሞም ጠቢብ ሰው፥ “ይህን ዐወቅሁ” ቢል እርሱ ያገኘው ዘንድ አይችልም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ከፀሐይም በታች የተደረገውን ሥራ መርምሮ ያገኝ ዘንድ ለሰው እንዳይቻለው የእግዚአብሔርን ሥራ ሁሉ አየሁ። ሰውም ሊፈልግ እጅግ ቢደክም መርምሮ አያገኘውም፥ ደግሞ ጠቢብ ሰው፦ ይህን አወቅሁ ቢል እርሱ ያገኘው ዘንድ አይችልም። Ver Capítulo |